ጎጃም ዕዝ

ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ !!

የአማራ ህዝብ እየታገለ ያለው ለህልውናው ነው። ይህን ስንል በአማራ ህዝብ ላይ በአለም ታይቶ ማይታወቁ አሰቃቂ ግፎች ተፈጽመውበታል። ለምሳሌ ያክል፦ ከነፍስ ወከፍ እስከ ጅምላ የዶዘር ቀብር፤ ህፃናትን ከመቆራረጥ እስከ የእናት ሆድ መሰንጠቅ፤ ከእምነት ተቋማት መውደም እስከ አባቶች መቃጠል፤ ከተማሪዎች መታገት፣ ሰነድ መቃጠል፣ መደፈር፣ ከፎቅ መወርወር እስከ አሰቃቂ ግድያዎች፣ ተንቀሳቅሶ መስራት ማይቻልበት፣ ሾፌሮች የሚታገቱበት አለፍ ሲልም በአማራነታቸው የሚታረዱበት፣ በአማራነቱ በየቦታው የሚፈናቀልበት፣ የልማት ጥያቄና መማር ቅንጦት የሆነበትና እንደህዝብ መጥፋት አለበት ተብሎ ተፈርጆ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ለመጨፍጨፍ የተዘመተበት ህዝብ ነው። ስለዚህ የአማራ ህዝብ የሚታገልለት ጽኑ የሆነ አላማና ግብ አለው።

የጎጃም ዕዝ ያወጣውን ሶስተኛውን መግለጫ ዕዙ ሳይሆን ከዕዙ ውጭ የሆነ አካል ፅፎ የላከው ነው በማለት የሚዲያ ዘመቻ የከፈቱና ያስከፈቱ አካላት መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነት ያልተረዱ መሆናቸውን የተገነዘብን ሲሆነ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን የጎጃም ዕዝ በውጭም ሆነ በውስጥ የራሱ ባልሆኑ ሀይሎች የማይዘወር እና የአማራ ህዝብ ትግል በወለዳቸው፤ ከጎጃም ማህፀነ ለምለም እናቶች በተገኙ፤ በእሳት ቀለበት እየተራመዱ ትግሉን በሚመሩ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የሚመራ መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን። በመሆኑም የተወሰኑ ውይይቶች ጥሪያችንን ከተቀበሉ የቀድሞ አደረጃጄቶች ጋር የተጀመረ ሲሆን ችግር ፈቺ የሆነ ቀጠሮ የተያዘ መሆኑን እየገለጽን ዉጤታማ እንዲሆ የተለያዩ ስራዎች ተጀምረዋል። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ይህን ጨፍጫፊ ስርዓት ማስወገድ የመጀመሪያ መፍትሄ አድርጎ አገረ መንግስትን የመስራት ጥበብ ከሌላ አጋር ኢትዮጵያውያን ጋር የራሱን አሻራ እንደሚያስቀምጥ ጥርጥር የለንም እያልን ዕዙ ባንዳንድ ጉዳዮች ከተወያዬ በኋላ ይህን ባለ 3 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ, እጃችሁን እንድትሰጡ ብሎ አሸባሪውና ጨፍጫፊው መንግስት በሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ ይህ የሀይል ሚዛንን ለይቶ የማያውቅ፣ ለአማራ ህዝብ ያለውን ንቀትና የአማራ ፋኖ የሚታገልለትን አላማና ግብም ለወንበራቸውና ለእኩይ አላማቸው ፈፅሞ ጠር እንደሆነባቸው ያሳዬ መግለጫ ነው። በመሆኑም ከአማራ ፋኖ ጋር የገጠማችሁ እና ከሞት የተረፋችሁ በየቦታው በግዴታ ታፍሳችሁ የመጣችሁ እና በሙስናና በማጭበርበር የተዘፈቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምክንያት በድህነት የጣራ ወለል በታች ሁናችሁ እንደ ስራ እድል ቆጥራችሁና አላማው አገርን መጠበቅ ነው በሚል ቅንነት ተቀላቅላችሁ የነበርና በሴራ ውጊያ ከሞት የተረፋችሁ ውስን ሃይሎች የጨፍጫፊው መንግስት ስልጣን አስጠባቂ ከመሆን ወጥታችሁ ብሄር ሳይመርጥ ምርኮኞችን ለሚንከባከበው ፍኖ እጃችሁን እንድትሰጡ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

2ተኛ, የሀገሪቱ ከፍተኛው የጦር ባለስልጣን የሰጠው መግለጫ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ ያሳየበት ንግግር ከበቂ በላይ ነው። ድሮኑን ከበቂ በላይ እንደተጠቀመበት በበቂ ሁኔታ ባልተጠበቁ የከሰሩ የመዘለባበድ ንግግሮቹ አስቀምጧል። አሸባሪው ሀይል ፋኖን በድሮን ደበደበ የሚል መግለጫም አላወጣንም ትጥቅ ይዞ እየተዋጋ ያለውን የአማራ ፋኖ አንገት ማስደፋት የሚችል አቅምም ስነልቦናም የላቸውም። ይህ ደግሞ ከክላሽኮቭ እስከ ዙ-23 ያስታጠቀን የአሸባሪው ስልጣን አስጠባቂ መሆኑ በቂ ምስክር ነው። የአማራ ፋኖ በድሮንና ከባድ መሳሪያ ህፃናትን፣ አዛውንቶቾን፣ የእምነት ተቋማት አባቶችንና ሰብል በመሰብሰብ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን በአጠቃላይ ንፁሃንን እየደበደበ መሆኑን ብናሳውቅም አማራ እንደ ህዝብ መጥፋት አለበት የሚለውን እቅድ በአደባባይ ምስክርነት የሰጠበትን እና አቅም ያነሰው ይህ ቡድን ንፁሃንን መጨፍጨፉን እንደሚቀጥል በአደባባይ ምስክርነት ሰጥቷል።
ሚዲያ የሌለው ህዝብ ሰሚም ሆነ አልቃሽ እንደሌለው ጠንቅቀን እናውቃለን። በመሆኑም የትግሉ አጋር የሆናችሁ የሀገራችን ህዝቦች እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሙሉ በህዝባችን ላይ የተቃጣውን ጥቃት እንዲያውቅልን ስንል እያሳሰብን ይህን አለም አቀፍ የጦር ወንጀል በማሳወቅ ከጎናች እንድትሆኑ ስል እውነትን ለሚደፍር ሚዲያዎች፣ የሰባዊ መብት ተሟጋቾች እና ለሁሉም ማህበረሰብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

3ተኛ, የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በተመለከተ የለት ጉርሳቸውን በዚህ እንቅስቃሴ ላይ ላደረጉነ ሰብል ለመሰብሰብ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑና መንገድ ላይ የቆሙ መኪኖችን ግምት ውስጥ በማስገባት ላልተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴ የተፈቀደ መሆኑን እየገለጽን የጨፍጫፊው ሃይል ሸቀጣሸቀጦች ስንዴን ጨምሮ መድሃኒቶች ወደ አማራ *ክልል እንዳይገባ ትእዛዞች መሰጣታቸው ይታወቃል። ስለዚህ በተቃራኒው ከክሰል እስከ ማርና ቅቤ፣ ከስንዴ እስከ ጤፍ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየገዙ ሲሆን አላማውም ጦርነትን በማራዘም የአማራን ህዝብ በርሃብ አለንጋ እንዲገረፍና በኢኮኖሚው እንዲዳከም በመዋቅራዊ መንገድ ታቅዶበት እየሰሩ መሆናቸውን በባለፈው መግለጫችን ማስታወቃችን አይዘነጋም።

ስለሆነም የጨፍጫፊው ስልጣን ጠባቂ የሆነው ሀይል እጁን መስጠት የሚፈልግ እጁን እስኪሰጥ እና የተራረፈው በአማራ ፋኖ እስኪደመሰስ ድረስ ምንም አይነት ጭነት ከአማራ *ክልል ወደሌላ ቦታዎች ጭኖ መውጣት የማይቻል መሆኑን እያሳሰብን ይህን አድርጎ በተገኜ ግለሰብም ሆነ ተቋም በየትኛውም የጎጃም አካባቢ በሚገኙ ለዕዙ አደረጃጀቶች ውርስ ተደርጎ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማከፋፈል የተተኳሽ መግዣና ለትግሉ እንዲውል ትእዛዝ የተላለፈ መሆኑን በአፅኖት እንገልፃለን።

ከእውነት ጋር የቆመ ህዝብ ያሸንፋል!!
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!!
ድል ለፋኖ!!

የጎጃም ዕዝ ፋኖ!
ታህሳስ 08 ቀን 2016 ዓ.ም