Dec 31, 2023
የምስራቅ አማራ ፋኖ ጀብዱ!
በዋርካዉ ምሬ ወዳጆ የተመራዉ “ዘመቻ ጃዉሳ” የአማራ ፋኖ ታላቅ ጀብድ የፈጸመበት፤ ትጥቁን ያጠናከረባት፤ የበላይነቱን ያረጋገጠበት፣ አማራ ከዉጭ እስከ ሃገር ዉስጥ አንድነቱን ያሳየበት፣
የአማራ ብርቱ ክንድ የታየበት፣ እስረኞች የተፈቱበት፣ ፋኖ መቻሉን ያረጋገጠበት፣ ጀግንነቱን ያስመሰከረበት ነው።
የምስራቅ አማራ ፋኖ በዋርካዉ ምሬ ወዳጆ በሚመራው ዘመጃ ጃዉሳ ድልና ተጋድሎ በወሎ ግንባር ከሰሞኑም ቀጥሏል።
ዛሬም ግራና ዙሪያ ፋጂ ሊብሶ ቦከክሳ ጃራ ዲልድይ የምስራቅ አማራ ፋኖ ባለሽርጡ ብርጌድ የፋሽስቱ አብይ አህመድን ሰራዊት ድባቅ መትቶታል።
በዚህም ግንባር የጠላት ሃይል 7 የተማረከ ሲሆን ከ20 የሚበልጥ ከጥቅም ዉጭ ሁኗል። በጠቅላላው 22 የጦር መሳሪያ ገቢ ሲሆን ጠላትም 1 ኮር ወይም ሶስት ክፍለ ጦር ካልተጨመረልን አንችልም በማለት ወደ ጭፍራ እየፈረጠጠ ይገኛል።
የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝም
– አሳምነው ብርጌድ
– ሃውጃኖ ብርጌድ
– ወርጌሳ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው ታጠቅ ብርጌድ
– ቆቦ ዙሪያ የሚንቀሳቀስዉ ዞብል አንባ ብርጌድ እና ግዳን
– ተኩለሽ የሚንቀሳቀሰው በረኽኛዉ ብርጌድ
– የጊራና እና አካባቢው ባለ ሽርጡ ብርጌድ በጋራ በመሆን የጠላትን ኃይል እየለበለቡት ይገኛሉ።
ድል ለፋኖ!
ሙሉጌታ አንበርብር