የብልጽግና ወንጌል ተከታዮችና የብልጽግና ፓርቲ አባላት፣ ከዲያብሎስ አምልኮ እራሳችሁን አግልሉ

ሰይፈ ስላሴ
ክፍል አንድ

መጽሐፍ ቅዱስንና ቁራንን ያጠኑ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ አሉ። ይሁንና እነዚህ ሰዎች አለማዊውን የአዲሱ ዘመን የስነልቦና መጽሀፍትን አላነበቡም። ስለዚህ ብዙ ክርስቲያኖችና እስላሞች ሀይማኖታቸውን ቀይረው የአብይና የሱን ዲያብሎስን እምነት ተከታዮች ሆነዋል።

አብይ 14 ሚሊዮን ተከታዮች እንዳሉት ባለፈው ሳምንት ነግሮናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ የስነልቦናውን (The New Age Movement) እና አለማዊውን መጽሀፍ ያነበበቡ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ ይሁንና እነሱ መጽሐፍ ቅዱሱንና ቁራኑን አያውቁም። ስለዚህ ሁለቱን የማዛመድና የመመርመር አቅም የላቸውም። የዚህ ጽሁፍ አላማ የዲያብሎስ እምነት እንዴት የበግ ለምድ ለብሶ ክርስቲያኑንና እስላሙን ሀይማኖቱን እንዳስቀየረው ለማሳየት ነው።

አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በሰይጣን አምልኮ ንዋይ ተታለው14 ሚሊዮን ሰዎች ሀይማኖታቸውን ቀይረው የዲያብሎስ ተከታዬች ሆነዋል ፡ ኮሎኔል አብይ ነግሮናል።

እኔ አለማዊውንም መንፈሳዊውንም አነባለሁ። ይሄንንም የጻፍኩት የፕሮቴስታንትም የኦርቶዶክስ የእምነት አባቶች ገና ስለ ስለ ብልጽግና ወንጌል ምንጭና ግብ አላነበቡም። ምን እንደሆነም ገና አላወቁም። ብዙዎች አብይን እንደ ክርስቶስ አስተምህሮ ቆጥረው ከሱ ጋር ህብረት ለመፍጠር ሲሞክሩ ይታያሉ። አብይ እራሱ እንዳለው ጳጳሳቱና ወንጌላውያን ብርሀንና ጨለማን ለማስታረቅ
እየሞከሩ ነው።

ስለዚህ ክርስቲያኖች፣ ፕሮቴስታንቶችና እስላም የብልጽግና ሀይማኖት ተከታዮች በጽሞና አንብቡ። ምክንያቱም እናንተ ሀይማኖት ቀየራችሁ እንጂ የፓለቲካ ፓርቲ አባል አልሆናችሁም።

ዛሬ በዝርዝር የምጽፈው ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖችና ለፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ነው።

የብልጽግና ወንጌል አስተምህሮ በ1950ዎቹ የተፈጠረ ሀይማኖት ቢሆንም ዛሬ በአሜሪካ ትልቁ ተከታይ ያለው ሀይማኖት ለመሆን በቅቷል።

የብልጽግና ወንጌልን ማን ጻፈው?

የብልጽግና ወንጌል የተጻፈው መጀመሪያ በስነ ልቦና አነቃቂዎች ነው። እነ ናፖሊዮን ሂል “Think and Grow Rich”  እነ ኖርማን አንስት  “The Power of Positive Thinking”, The Secret, by Byrne የተጻፏት መጽሀፍት ናቸው። እነዚህ መጽሀፍት በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ እየተሸጡ ነው። እነዚህ በራሳቸው እንደ ስነልቦና ማነቃቂያ ችግር የላቸውም።

ይሁንና እነዚህን “የብልጽግና ወንጌል ብሎ ማምለክ ግን ክርስትና አይሆንም። አሁን በአሜሪካ ያሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን እያጠፋ ያለው የብልጽና ወንጌል ነው። ይሄንን ትችት ራሳቸው ፕሮቴስታንቶቹ ጽፈዋል።

“The Word of Faith Movement, often termed “the prosperity gospel.”  This group has been infiltrating evangelicalism for decades and is now the fastest growing segment of Christianity in the world.  Some have estimated that up to 90 percent of those claiming to be Christians in Africa are of the prosperity gospel variety”

ይሄንን በቀላሉ ለሰባኪዎች ሀብት ማፍሪያ ካደረጉት ውስጥ Kenneth Hagin, Kenneth Copeland, Robert Tilton, Paul Yonggi Cho, Benny Hinn, Marilyn Hickey, Frederick Price, John Avanzini, Charles Capps, Jerry Savelle, Morris Cerullo, Joyce Meyer and Paul and Jan Crouch. ይገኙበታል።

አብይ አህመድ በድህነት ያደገ ልጅ ነው። ሁላችንም የድሀና የገበሬ ልጆች ነን ይሁንና ብር ለማግኘት ሀይማኖታችንን አልቀየርንም። አብይ ኦርቶዶክስ፣ሙስሊምም ነበር። መጨረሻ ሀብትና ጉልበት የሚሰጠው የብልጽግና ወንጌል ሆኖ ስላገኘው ክርስትናውንም እስልምናውንም ትቶ የብልጽግና ሀይማኖት ተከታይ ሆነ። አሁን እሱ የዚህ እምነት ሰባኪ፣ አጥማቂና ጳጳስ ሆንዋል። አላማውም እስላሙንም ክርስቲያንም ወደ የብልጽግና ቤተ አምልኮ ማስገባት ነው። የዚህም ቤተ አምልኮ አላማ በጥቅም የብልጽግና ፓርቲ/ቤተ እምነት ተከታይ ማድረግ ነው።

ይህን የስነ ልቦና አስተምህሮ ወስደው ወደ ክርስትና እምነት የቀየሩት ደግሞ  Joel Osteen, በአሜሪካ የትልቁ ቤተ እምነት Lakewood Church ባለቤት እና መስራች ነው። ሁለተኛው ደግሞ Oral Roberts, a pioneering televangelist ነው። ሁለቱም ብዙ መጽሀፍ ጽፈውል ፈልጋችሁ አንብቡት።

የብልጽግናን ወንጌል ክርስቲያኖችን የሚያስክድ ነው ብለው ብዙ ሰዎች ጽፈዋል። ለምሳሌ Joel Osteen And The Prosperity Gospel በሚል የተፃፈውን አንብቡ

አስተምህሮውም ሀብታም እንድትሆኑ መጀመሪያ ለፓስተራችሁ ለዘር የሚሆን ብር (ሴድ መኒ) ስጡንና በሱ ላይ ጸልየን ወደ ሚሊዮን ይባዛላችሀል እያሉ ይዘርፋሉ። ድሮ ብር ስጠኝ ብሎ ሰው ጠንቋይና ቃልቻ ቤት ነበር የሚሄደው ዛሬ ደግሞ እስራኤል ዳንሳ፣ አዩ ጩፋ እና ዮናታን አክሊሉ እንግዳ ማረፍያ ነው የሚሄደው። ይህ ነው የአብይ አህመድ ክርስትና የሚለው።

የብልጽግና እና የጤና መጽሀፍ ቅዱስ የሚባለው በእንግሊዘኛ (The prosperity gospel, also known as the health and wealth gospel or name it and claim it, is a teaching within Protestant Christianity”. ነው ብለው እንዲያምኑ ስለተደረጉ ብዙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አብይ ሺ አመት ንገስ ብለው በአደባባይ ጸለዩለት. አብይ የሚከተለው እምነት ከነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አንድ  እንዳልሆነ አያውቁም። ይህ የብልጽግና ወንጌላውያንን ማታለል በአደባባይ እየታየ ነው።

አሁን በሞባዬላችሁ ከንግድ ባንክ ሚሊዮን ብር እንዲገባ ያላችሁን ሁሉ ለኔ ስጡና  ልጸልይላችሁ የሚሉት እስራኤል ድልንሳና የአብይ አስተምህሮ አንድ ነው።
prosperity

የብልጽግና እምነት የዲያብሎስ አምልኮ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች።

አብይ የዲያብሎስ እምነት ተከታይ እንጂ የክርስቶስ ተከታይ አይደለም የምለው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። በመጀመሪያ  ክርስቲያን ማለት የክርስቶስን ቃል የሚቀበል ማለት ነው። ቃሉን ሳይቀበሉ ክርስቲያን መሆን አይቻልም።
አለማወቅ ችግር የለውም ይሁንና አውቀን አለመቀበል ግን ክርስቲያን አያደርገንም።

የብልጽግና ፍቅረ ንዋይ የክርስቶስ አስተምህሮ አይደለም
በማቲዎስ ወንጌል ም4 ቁ 1-11 ይሄንን ይላል ። “ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተም ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። አርባ ቀን አርባ ሌሊት ከጦመ በኋላ ተራበ።ፈተኙም ቀርቦ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆን በል አለው።  እርሱም መልሶ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል አለው። ……ከዛም ዲያቢሎስ እጅግ ረዥም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፣ የዓለምን መንግስታት ሁሉ ከክብራቸው  አሳይቶ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ  እሰጥካለሁ አለው። ያን ግዜ ኢየሱስ ሒድ አንተ ሰይጣን ከፊቴ ለአምላክህ ስገድ እሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፏልና አለው።”

ይህ ቃል የተጻፈው ዲያቢሎስ እንዴት የሰው ልጅን በጥቅምና በዝና እንደሚፈትሸውና የሰው ልጅም ለሀብትና ጥቅም ብሎ ለሰይጣን መስገድ እንደማይገባው ለማስተማር ነበር። ይሁንና በ20ኛው ክፍለዘመን ብዙ የአነቃቂ ንግግር ጸሀፊዎች የሰው ልጅ እንዴት ሀብታም ይሆናል የሚለውን መጻፍ ጀመሩ። ይህም  የአዲሱ ዘመን ንቅናቄን ፈጠረ (The New Age Movement) ተወለደ። ይህ ስነ ልቦና መሆኑ ቀርቶ ሀይማኖት ወይም እምነት ሆነ አሁን አብይ፣ ክርስቲያኑንም እስላሙንም የዚህ እምነት ተከታይ አድርጎ ብዙውን ሀይማኖቱን አስቀይሮታል።

የብልጽግና ወንጌል የፍቅረ ንዋይ በክርስቶስ የተወገዘ ነው።

በሉቃስ ወንጌል ደግሞ ም6: 20-26. ይህንን ይላል “እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና። እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና። እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና ታለቅሱማላችሁ።  ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።”

የብልጽና ወንጌል ከላይ የተጠቀሱትን የክርስቶስ ቃል አይቀበልም። ሳትሰራ፣ ሳትጥር፣ ሳትደክም ሀብት በሞባዬልህ ይገባል። ለድሆች አታስብ፣ በመንገድ ላይ ወንበዴዎች ደብድበው የጣሉትን አትመልከት፣  ለሚሞቱት ለሚሰቃዩት አታስብ። አንተ ደግ ደጉንና  ሀብትና ንብረት ብቻ ተመኝ። እሱን ታገኛለህ።  መስረቅ፣ መዋሸት፣ ጉቦ መብላት ፣ ድሆችን ለማየት መጠየፍ፣ ቤታቸውን ማፍረስ የብልጽግና ወንጌል መገለጫ ነው። ዛሬ እነ ሽመልስና ወንድሙ በቢሊዮን ብር በጉቦና በሲሚንቶ ንግድ ከብረዋል። እነ አዳነች አቤቤ ሰርቀው ልጆቻቸውን በዶላር ያስተምራሉ፣ ግን ማታ ተሰብስበው ተንበርክከው ለአባታቸው ይጸልያሉ።  ይህ የሌብነት፣ የጥላቻ፣ የግድያ አባታቸው ክርስቶስ አይደለም። አፋቸው እንጂ ተግባራቸው የዲያብሎስ ነው። በማቲዎስ ወንጌል ም4:8-11 ላይ እኮ ዲያቢሎስ በምድር ላይ ሀብትና ንብረት መስጠት እንደሚችል ተጽፏል።

ስለዚህ የብልጽግና ፓርቲ ተከታይ በተለይ የፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ንቁ። የኦርቶዶክሱና የእስላም የአብይ ቤተ እምንነት አባላት አብይ ክርስቲያን እንዳልሆነ ያውቃሉ። እነሱ ሌብነትንና ጥቅም ፈልገው ነው የመረጡት።

ብዙዎቻችሁ የተቀላቀላችሁት እምነት እንጂ የምድራዊ ፓለቲካ ፓርቲ እንዳልሆነ አታውቁም። ከላይ አርማውን ተመልከቱ ከአሜሪካ የብልጽግና ወንጌል አርማ የተቀዳ ነው። እንዴት ይሄንን አርማ የመምረጥና የማጽደቅ መብት የላችሁም፧ የማን ብልጽግና ብላችሁ እንኳን አትጠይቁም፧ የኢትዮጵያ ብልጽግና ወይስ የሰይጣን ተከታዮች ብልጽግና?

ዘጠና ዘጠኝ (99)% የሚሆነው የብልጽግና አባል የሆነው መንግስት ተጠግቶ ለመዝረፍና ለመክበር ነው። ይህ የንዋይ ፍቅር ግን ወደ ገሀነም እያሳሳቀ እየወሰደው መሆኑን አያውቅም ብልጽግናዎች  እበላለሁ ብላችሁ በዘላለማዊ እሳት እንዳትበሉ። የማቲዎስ ወንጌል 6:24 “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው አገልጋይ የለም፣ አንዱን ይወዳል ሁለተኛውንም ይጠላል፣ ወይንም አንዱን ይታዘዛል፣ ለሁለተኛውም አይታዘዝም፣ እንግዲህ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም” ይላል።

ብዙዎች የብልጽግና አባላት ክርስቲያን፣ እስልምና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ናቸው። ከዘማሪ ዶ/ር ደረጄ ከበደ ውጪ ይሄንን የክህደት የዲያቢሎስ መንገድ የተረዳ ያለ አይመስልም።

ሙስሊሞችም የተቀላቀላችሁት የብልጽግና ”መጽሐፍብ ቅዱስ”  እንጂ አለማዊ ፓርቲ አይደልም። እራሳችሁን በረመዳን ጦም አታታትሉ። አናውቅም ነበር እንዳትሉ ይሄው ተነግሯችሀል። አብይ Charismatic የሆነና ብዙ ተከታዮችን ማሳሳት የሚያስችል የክፏ መንፈስ ጸጋ ያለው ሰው ነው። 14 ሚሊዮን ሰው አስክዶ ዛሬ ለሰይጣን ግብር የሚታረዱ ህጻናትን እንዳያወግዙ አፋቸውን ለጉምዋል። በመጨረሻው ስታረድ፣ ስገደል፣ ምን አላችሁ ተብለን ሁላችንም እንጠይቃለን። መቼ አየንና ማለት አይቻልም።

የዛሬ አምስት አመት የአብን ጨቅላዎች የፈረንጆቹን ፍሪ ሜሴኖች እምነት ሁለት ጭንቅላት ያለውን አርማ ይዘው ወጡ። ይህ ከኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና እምነት ጋር ይጋጫል የሰይጣን እምነት 32 ዲግሪ አርማ ነው ተዉ ብንላቸው በድንቁርነታቸው ተቸንክረው እንቢ አሉ። መጀመሪያ አጫፍሮ በመጨረሻ ያጠፋችሀል አልን። አልሰማ አሉ። አሁን በየ እስር ቤቱ እየሰቃዩ ነው።

prosperity

የኦርቶዶክስና የብልጽግና ወንጌል ግጭት

አብይ ከልጅነቱ ጀምሮ ሀብት ንብረት ዝናን ለማግኘት እንደተጋ ነግሮናል። በማቲዎስ ወንጌል 4:8-11 እንደተጻፈው ዲያቢሎስ ከሰገዱለት በምድር ላይ ስልጣንና ሀብትም ይሰጣል። እናቱም ነግራዋለች። ነብይ አይደለችም ስለዚህ ጥንቆላ ነው። ስለዚህ በድህነት ሰቀቀን ስነ ልቦና የሚሰቃይ ሰው ሀብት ስጠኝ እንጂ እሰግድልሀለሁ ይላል። እነ መንግስቱ ማርክስ፣ ኤንግልስና ሌኒንን ብታምኑ በምድር ገነት ትገባላችሁ ብለው ብዙ ደሀና በድህነት ያደገ ምሁር አሳምነዋል። እግዚአብሔር የለም እያሉ አሳምነውት ነበር። ይህ ከድህነት ሽሽት ዛሬ ደግሞ 14 ሚሊዮን በድህነት ሰቀቀን ያደገ ክርስቲያንን ሙስሊምና ፕሮቴስታንት ግልብጥ ብሎ ሰርቆ ድህነቱን ለማራገፍ የብልጽግና ቤተ እምነቱን ተቀላቅሎ ክርስቶስን ጥሎ አብይን አምላኪ ሆንዋል።  ብልጭልጭ ህንጻ ውስጥ እንኖራለን፣ ገነት ማለት የአበቦች ቦታ ናት ብለው ብዙ ክርስቲያንና ብዙ የእስልምና ተከታዮችን ወደ ገሀነም አስከትለው እየሄዱ ነው።

ዲያቢሎስ ግብር ይጠይቃል። ይህም ሀጥያትን መስራት ነው። ይሄም ሀጥያት ነፍስ ማጥፋት ነው፣ የንጹሀንን ደም ማፍሰስ ነው። ወይን መጠጣት ሀጥያት ነው የሚሉት የብልጽግና አማኞች ግን የሰው ደም ማፍሰስ ሀጥያት መስሎ አይታያቸውም። በየሬስትራንቱ እና ሰዎች ፊት ቅዱስ መስለው ለመታየት ወይን ቢራ ባፋችን አይገባም የሚሉት ፕሮቴታንቶች ጻድቅ መስለው የሚታዩት በጭለማ ደግሞ የአብይ እምነት ተከታዬች ህጻናትን ሲያሳርዱ፣ እናቶችን ሲያስገድሉ፣ በሰራዊታቸው ሴቶችን ሲደፍሩ፣ ዘር ለማጥፋት ሲተጉ። ደሆችን ሲያሳድዱ ዝም በማለት ልክ እንደ ቃዬል እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን በማለት ፈጣሪን ሊሸውዱ ያስባሉ። ግን ፈተናውን እየወደቁ ነው። ማቲዎስ 2:16-18 ላይ ሄሮድስ ከሁለት አመት በታች ከሆኑት ውስጥአንድ ሕፃን አድጎ ስልጣንን ይቀማኛል ብሎ ስለፈራ ሁሉንም አስገደለ።

“ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተዘባበቱበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣና ጭፍራዎቹን ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸውን፥ ከዚያም የሚያንሱትን፥ በቤተ ልሔምና በአውራጃዎችዋ ሁሉ የነበሩትን ሕፃናት አስገደለ።”
አሁንስ ልጅ ተወልዶ አድጎ አማራ ይሆናል ተብሎ ከናት ሆድ ተቀዶ ወጥቶ ሲገደል የትኛው የፕሮቴስታንት፣ ወይን አልጠጣም፣ ጻድቅ ነኝ ባይ ወጥቶ ይሄንን ሀጥያት አቁሙ ያለው? የትኛው ሼክና ጳጳስ ነው ያወገዘው? ለግል ሀብትና ክብር የተሰባሰቡት ጳጳስ፣ ሼኮችና ወንጌላውያን ነን የሚሉ ግብዞች ወድቀው ታዩ።

ሰይጣን ክርስቶስን ሲፈትነው የአለምን ሀብት ሁሉ አሳይቶ ለኔ ብትሰግድልኝ ይሄንን ሁሉ እሰጥሀለሁ እንዳለው አብይና ሽመልስም ሀብት ለማግኘት የማያደርጉት ነገር የለም።

አብይ ላይ የተዳበለውም የክርስቲያንን ደም የሚጠጣው ዲያብሎስ ኑና ለሰይጣን እንስገድ ሀብትና ብልጽግና ይሰጠናል ሲባሉ እሺ ብለው የሚከተሉት ክርስቲያንና እስላም ነን የሚሉ ብዙ ናቸው።
ክርስቶስ ለደቀ መዝሙሮች የሰጠው ማስጠንቀቂያ ደግሞ  በመንገዳችሁ ላይ ወርቅና ብር አትያዙ ነበር ።

ክርስቶስ  በማቲዎስ ወንጌል 10:7-10 “ሄዳችሁም። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትን አውጡ፣ በከንቱ የተቀበላችሁ፣ በከንቱ ስጡ። ወርቅ ወይንም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፣ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይንም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ”

ይህ ቃል ሁሉ በሁሉም ወንጌሎች ውስጥ ተደጋግሟል። ይሁንና የብልጽግና የዲያቢሎስ ወንጌል ደግሞ ሀብትን፣ ሞገስን እሹ፣ ወርቅና ዶላርን አጋብሱ ነው የሚላቸው። ዲያቢሎስ ለኔ ስገዱ ብልጽግናን እሰጣችሀለሁ ነው የሚላቸው። ይሄንን ባለማውገዛቸውና ባለ መለየታቸው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ፈተናውን ወድቀው ለሀብት ስገዱ ለሚለው እየጸለዩ ነው። ሎጂክ ስንማር A ከ B ጋር እኩል ከሆነና B ደግሞ ከ C ጋር እኩል ከሆነ A ደግሞ ከ C ጋር እኩል ይሆናል።

አሁን ያለውን ፍቅረ ንዋይ ወዳጅና በንጹሀን ደም የሚታጠበውን አለማውገዝ ከተጠያቂነት አያድንም። መደገፍ ደግሞ እጅን በደም ማነካካት ነው። ይህ ደግሞ የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ጳጳሳትንና የሙስሊሞችም የሀይማኖት አባቶች ያካትታል።

ሀጥያትን አውግዙ። ሰውን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ ተብሏል።

በክፍል ሁለት የሁለት ሺ ዘመኑን የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ፈተና እናያለን ።

 

 

The opinion expressed in this article is that of the author