Gojam Fano

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈ መመሪያ

የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት በመደበኛ ጦርነት በህዝብ ላይ ከሚያደርሰው እልቂት ባሻገር በርካታ የውንብድና እና የሽብር ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል።
በከተሞች አካባቢ በየዕለቱ ወጣቶችን ይረሽናል፤ በየማጎሪያ ካምፖች ያጠራቅማል፤ ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች ያግዛል። ከዚህ ጎንለጎንም የፋኖ ቤተሰቦችን ያስራል፤ ይረሽናል፤ ንብረት ያወድማል።
በማንኛውም ፀያፍ መንገድ የአብይ አህመድን ስልጣን ማስቀጠልን የመረጠው ወራሪ ሰራዊት ባንኮችን፣ ጤና ጣቢያወችን ዘርፏል፤ አውድሟል። በርካታ ትምህርት ቤቶችንም በመድፍ፣ በሮኬት፣ በድሮን እና በጀት አውድሟል። የገበያ ቀናትን እየመረጠ በሚያደርገው የወረራ ዘመቻ የማህበረሰባችንን ደህንነት ከባድ አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል።
ከሰሞኑም በሚተኩሳቸው መሳሪያወች በህዝብ ላይ ከባድ እልቂት እያስከተለ ነው። በመሆኑም እነዚህን እና መሰል ጉዳቶችን ለመከላከል በምናደርገው ተጋድሎ ምክንያት የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ከመጭው ሰኞ ሕዳር 30/ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ:-
1) ከአምቡላንሶች በስተቀር መንገዶች ለሁሉም ተሽከርካሪወች ዝግ እንዲደረጉ መመሪያ ተሰጥቷል።
2) ለህዝብ ደህንነት ሲባል ከጤና ተቋማት በስተቀር ባንኮችን እና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ዝግ እንዲሆኑ ታዟል።
3) በመጨረሻም ሰራዊታችን እና መላው ህዝብ ወራሪውን ሰራዊት ለመመከት ለምናደርጋቸው ተከታታይ ወታደራዊ ጥሪወች በወትሮ ዝግጁነት እንዲጠብቅ እናሳስባለን

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

የአማራ ፋኖ በጎጃም!