የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ውህደት ፈጠሩ

የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ውህደት ፈጠሩ

የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ኅዳር 29/2017 ዓ.ም በሁለቱ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም በበላይ ጠባቂ አባቶች አማካይነት በይፋ አንድ ለመሆን ከስምምነት ላይ መድረስ መቻላቸውን ከገለጡ በኋላ በርካታ ሥራዎች ተከናውነው እነሆ ዛሬ መዋቅራዊ ውሕደትና አንድነት ተፈጥሮ ለሕዝባችን፣ ለሠራዊታችን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ይህ ተቋማዊ አንድነት የአማራ ፋኖ በጎንደርም ሆነ የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ከዚህ በፊት የሚጠሩበትን ስም አክስመው ከዛሬ ጀምሮ “የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር” በሚል የተቋም ስም የሚጠራ ይሆናል። የተቋሙን ሎጎ በተመለከተ በቀጣይ ይፋ እናደርጋለን።

በዚህ መሠረት የተቋሙን አወቃቀርና አመራሮች እንደሚከተለው ሰይመናል።

አርበኛ ሐብቴ ወልዴሰብሳቢ
አርበኛ ባዬ ቀናውም/ሰብሳቢ
አርበኛ ሳሙኤል ባለእድልም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
አርበኛ ሸጋ ጌታቸውም/ወታደራዊ አዛዥ
አርበኛ ማንደፍሮ ተሠማየጽ/ቤት ኃላፊ
አርበኛ ማሩ ጥሩነህም/ጽ/ቤት ኃላፊ
አርበኛ ያለው አዱኛየዘመቻ መምሪያ አዛዥ
አርበኛ ዮናስ አያልቅበትም/ዘመቻ መምሪያ አዛዥ
አርበኛ ግዛቸው አሌየልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ አዛዥ
አርበኛ ሻምበል መሳፍንትም/የልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ አዛዥ
ብ/ጄኔራል ተዘራ ንጉሤየወታደራዊ እቅድና እስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ጌጡ ድረስም/ወታደራዊ እቅድና እስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ አስቻለው በለጠም/ ሰብሳቢና የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ አራጋው እንዳለም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ
ሻምበል አምሳሉ ማዘንጊያየሎጀስቲክስ አቅርቦትና ሥርጭት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ስጦታው መልኬ..ም/የሎጀስቲክስ አቅርቦትና ስርጭት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ደምሰው አባተየአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ አንድነት አማረም/የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ አበበ ብርሐኑየውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ሸርብ አሸነፍ .የሕዝብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ታደሠ ወርቁም/የሕዝብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ጸዳሉ ሙላትየማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ዓለሙ መለሰም/የማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ቢኒያም አለምነውም/የገንዘብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ በዬነ አለማውየቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ አያናው አዱኛም/የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ሲሳይ አሸብርየሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ተመስገን ውባንተም/የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ዮሐንስ ንጉሡየሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ድረስ ሞላም/የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ባሻ ስጦታውየሰው ሀብት አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ማንዴላ እያዩም/የሰው ሀብት አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ዶ/ር አታለለ ሰጠኝየጤና መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ እያቸው ብርሐኑም/የጤና መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ በላይ ዘለቀ ሕግና ሥነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ ማሩ ቢተውም/የሕግና ሥነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ...የመረጃና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ
አርበኛ...ም/የመረጃና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ

መሆናቸውን ለሠራዊታችን እንዲሁም የኅልውና ትግላችንን በስስት ለሚመለከተው በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም ለሚኖረው ሕዝባችን መግለጽ እንወዳለን። ከዚህ በተጨማሪም የበላይ ጠባቂ አርበኞች ምክር ቤት አባላትንም እንደሚከተለው ሰይመናል።

አርበኛ መሣፍንት ተስፉሰብሳቢ
አርበኛ አረጋ አለባቸውም/ሰብሳቢ
አርበኛ ሻምበል መሠረት ዓለሙፀሐፊ
አርበኛ ሠፈር መለሰአባል
አርበኛ ሻምበል ገብሩ ልይህአባል
አርበኛ ደስታው ደመላሽ .አባል
አርበኛ እሸቴ ባዬአባል ሆነው ተሰይመዋል

 

– Mulugeta Anberber