የፋኖ አንድነት ምክር ቤት መግለጫ ክፍል አምስት፣ ስድስት እና ሰባት

ክፍል አምስት

ከወለጋ አልሞት ባይ ተጋዳይ ፋኖዎች ጋር ጭውውት

የወለጋ ችግር የአማራውን ስነልቦና ስለሚገልጽ ከሶስት የወለጋ ፋኖዎች ጋር የተደረገ ወግ በዚህ ውስጥ ለማካተት ወደድን።

ሁሉም እንደሚያውቀው የወለጋ ስዎች ለረጅም ግዚ ሲታረዱ፣ በዶዘር ሲቀበሩ፣ አባካችሁ አድኑን እያሉ ይጮሀሉ ነበር። የአማራ ስነልቦናቸው ‘መንግስት አባት ነው፣ ጠባቂ ነው፣ ፈሪሀ እግዚአብሄር አለው፣ ለምን ደሀን ይሙት ይላል፣ እነሱም እንደኛው ጡርንና ሀጥያት ያውቃሉ’ በሚል የስነ ልቦና እስር ውስጥ ሆነው ይሞቱ ነበር። ለአብይ አህመድ፣ ለሺመልስ አብዲሳ፣ ለተመስገን ጡሩነህ፣ ለአገኘሁ ተሻገር፣ ለዶ/ር ይልቃል ከፍ ያለ፣ ለደመቀ መኮንን
መልዕክት እየላኩ ይማጸኑ ነበር።

አንዳንዶቹ ደግሞ ተስፋ ሲቆርጡ ስልክ አፈላልገው ለፋኖ አደራጆች እየደወሉ እባካችሁ ድረሱልን፣ ፋኖን ላኩልን ይሉ ነበር። ምን ልብ ቢነድ ምን ያህል ቁጭት ቢፈጠር ከሸዋ ጠመንጃ ይዞ ኦሮምያን አቋርጦ ቄሌም ወለጋ መድረስ
አይቻልም ነበር።

በጎጃም ደግሞ የነ ይልቃል ከፍያለና የነአገኘሁ ጥሩነህ በየ መቶ ሜትሩ የልዩ ኃይል ኬላ አቋቁመው ከጎጃም ጥይት ቀርቶ ኪኒንና ፋሻ እንዳይገባ እየፈተሹ ይቀሙ ነበር። ስለዚህ ገና በመደራጀት ላይ ያለው ፋኖ ከምክር በቀር ምንም ማድረግ አይችልም ነበር።

እናንተው ተደራጅታችሁ እራሳችሁን ለመከላከል ሞክሩ። መንግስትም አለማቀፍ ድርግቶች አያተርፉዋችሁም የሚል ምከር ነበር። ልብ የሚሰብር ቢሆንም መሞታችሁ ላይቀር እየተፍጨረጨራችሁ ሙቱ የሚል ነበር። ከኦሮሙማ መንግስት ህይወት አዳኝ ኃይል ይመጣል ብላችሁ በጭራሽ አትጠብቁ የሚል ነበር። ቁርጡን ሲያውቁ በር ዘግተው እንደሚደበድቧት ድመት ነብር መሆን ጀመሩ። ሊገላቸው የመጣውን መንጋ ዘነዘናቸውንም መጥረቢያቸውንም የደበቁዋትን ጠመንጃቸውን ይዘው መግጠም ጀመሩ።

እንደምናየው ዛሬ ተሰልፈው አይታረዱም፣ አራት ገለው ይሞታሉ እንጂ እየተነዱ አይሞቱም። ይህ እንዲህ እንዳለ ሶስት የወለጋ መሪዎች አባይን አቋርጠው በመምጣት ከፋኖ መሪዎችን ጋር ለመገናኘት እድል ነበር። አንድ ቀን ምሽት ላይ አንዱ መሪ እንደው የሚመራን የተማረ ሰው ብናገኝ ውጤት እናመጣ ነበር አሉ።

ታድያ አንደኛው የፋኖ መሪ ለምን አለ? የወለጋው አርበኛ፣ የተማረ ይሻላል፣ እኛማ አልተማርን ምን እናውቃለን አሉ። ከዛ አንኛው የፋኖ መሪ እስከ ስንተኛ ተምራችሀል ብሎ ይጠይቃቸዋል። አንዱ በእድሜው ወጣት የሆነና በጥይት ተመቶ ለህክምና የመጣው እስከ 7ኛ ክፍል አለ፣ አዛውንቶቹ ደግሞ እስከ 5ኛ አሉ።

ከዛ የፋኖ መሪው ለመሆኑ “አፄ ሚኒሊክ ስንተኛ ክፍል ይመስሏችሀል?” ብሎ ጠየቀ። አይ በዛን ግዜማ የፈረንጅ ትምህርት የት አለ ብለው መለሱ። የአርበኞች ቁንጮ የሚባሉትስ ራስ አበበ አረጋይስ ይላቸዋል? “አይ እሳቸውስ ቢሆኑ ዳዊት ደግመው እንደሆን እንጂ አሳኳላ ወየት ይገባሉ’ አሉ። ፋኖው በመቀጠልም ‘በላይ ዘለቀስ፣ ሀይላማርያም ማሞስ እያለ የአርበኞችን ስም ይዘረዝርላቸው ገባ።

የወለጋዎቹ ፋኖዎች ነገሩ ወዴት እንደሚሄድ ስለገባቸው ፈገግ ብለው ‘መቼ በነሱ ዘመን የፈረንጅ አስኳላ አልነበር’ አሉ።

በመደምደሚያው ‘አያችሁ ታላቅ መሪ እንደ ሚኒሊክ፤ እንደ አበበ አረጋይ፣ እንደ በላይ ዘለቀ ለመሆን የፈረንጅ ትምህርት ቅድመ ሁኔታ አይደለም። ጀግናም መሪም በትምህርት ቤት አይፈጠርም፣ በመከራና በትግል ውስጥ እንጂ” አላቸው።

አጼ ሚኒሊክን ታላቅ የጥቁር መሪ ያስባላቸው ጣልያን ነው። ደፍሮ መጥቶ አድዋ ላይ ባይገጥማቸው ኖሮ አያሸንፉትም ነበር። ጣልያን ሀገር አቋርጦ ባህር ሰንጥቆ መጥቶ ሚኒሊክን እንደ ዝንጀሮ በፍግርግር ብረት አስሬ አሳያችሀለሁ ብሎ ታብዮ ባይመጣ ኖሮ የምኒሊክ ማንነት ነጥሮ አለም አያየውም ነበር።

“እነ ራስ አበበ አረጋይ፣ እነ በላይ ዘለቀ፣ እነ ጃገማ ኬሎ እነ አብዲሳ አጋ እነ ዘርአይ ድረስ በፈተና ውስጥ ነው የተፈጠሩት”። አሁን እናንተን ለመምራት ወለጋ የሚመጣ ፕሮፌሰርም ዶክተርም የለም። ታሪክ እናንተ ላይ እድል ጥሏል። እናንተም ሞላ፤ አበበ፤ ሰይድም (ስማቸው ተቀይራል) ተብላችሁ ወደ ወለጋ ተመልሳችሁ አበበ አረጋይ፤ በላይ ዘለቀ፤ ጃገማ ኬሎ፣ መስፍን ስለሺ ሆናችሁ መውጣት ትችላላችሁ አላቸው።

አሁን እነዚህ የአምስተኛ ክፍል ገበሬዎች ቅጠላቸውን እየበሉ ጫካ እያደሩ ህዝባቸውን ከእልቂት እያዳኑ ነው። ዛሬ ተናንቀው ይሞታሉ እንጂ በዶዘር አይቀበሩም።

ይህንን ያመጣነው የፋኖ ጥንካሬ መሪና ማኒፌስቶ በማሳተሙ ሳይሆን ችግሩን የሚፈቱ መሪዎች ከታች መፍጠር መቻሉ ነው። ከከፋው፣ ከተጠቃው፣ ከመረረው ውስጥ ጀግና በመፍጠር እንጂ ዲግሪውን እያሳየ ነጻ አወጣሀለሁ በማለት አይደለም። እነ ጋሽ ሞላ ነገ እነ ራስ አበበ አረጋይን እነ ዳግማዊ ሚኒሊክን የማይሆኑበት ምንም ምክንያት የለም።

የፈረንጅ አፍ ለመሪነት ‘አልፋና ኦሜጋ ነው” የሚለውን የኤቢሲዲ ምርቆች ትርክት ፋኖ አይቀበለም። ይሄንን ስንል ፋኖ ያልተማረ ሰው ስብስብ ነው ለማለት አይደለም። ፋኖ የሚቃወመው ሰፊ ሕዝብ በማለት ሕዝብ እንደ እንስሳ ለራሱ የማያወቅ አርጎ የሚያየውን ፍልስፍናና እና ኤቢሲዲ የቆጠረው ደግሞ ነጻ አውጪ፣ ሁሉን አዋቂ እና መሪ (Vanguard: vanguard is typically seen as a small, elite group that is able to lead
the masses) አድርጎ የሚመድበውን ፍልስፍና ነው።

ድልን የመቀራመት ጥድፊያ፣ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተገንጥሎ “ህዝባዊ ግንባር” የመፍጠር ሙከራ አደጋው ለዚህ ነው። እድሜ ልካቸውን ውጤት ሳያመጡ ውርደት ቀለባቸው የሆኑ ተመልሰው ነጻ እናወጣሀለን ብለው እንዲያታልሉት አይፈቅድም።

ሻለቃ ዳዊት ፋኖ የስድስቱን ቀን የማጥቃት ዘመቻው ሊጀመር ሶስት ወር ሲቀረው ነው ላግዝ ብለው ግንኙነት የፈጠሩት። ማንም የፋኖን ዓላማ እና የፋኖን አንድነት ምክር ቤት መደገፍ እፈልጋለሁ ሲል በሩ ክፍት ነው። በዚህ አጋጣሚ የሳተላይት ስልክ እገዛላችሀለሁ በማለት የፋኖ መሪዎችን ስልክ መሰብሰብ ጀመሩ። ይህንንም በቅንነት የፋኖ መሪዎች አልተቃወሙም። ከዛ እስክንድርን በማግባባትና በማስፈራራት በውጪ ወኪላችን ሻለቃ ዳዊት ነው
በል ብለው ሲወተውቱ ከረሙ።

እውነት ለመናገር እስክንድር በመጀመሪያ መሪም እኔ ነኝ፣ ሻለቃንም ዳዊትም ወኪሌ ነው የሚለውን ሀሳብ አልተቀበለም ነበር። ከበርካታ ጭቅጨቃና ማስፈራራት በኋላ ወባ ታሞ በተኛበት ሰአት ያቺን ሻለቃ ዳዊት ወኪላችን ነው የምትለውን ቃል ፈልቅቀው አውጡ። ያችን ይዘው ሚሊዮን ዶላር ሰበሰቡ። እሱን ይዘው ፋኖን ለመሸመት ተመልሰው መጡ።

የሻለቃን አዝማሚያ የተረዳው የፋኖ አንድነት ምክር ቤት አባሎች ሻለቃን እንዲያርፉ በጽሁፍ ሳይቀር መከሩ። የተጻፈላቸው ደብዳቤ ጊዜው ሲደርስ በአደባባይ ይታተማል። እሳቸው ግን ቀድመው ባዘጋጁት የኢትዮ360 የፕሮፓጋንዳ ሞገድ ‘ፋኖ መሪ የለውም፤ የሚናበብ ኃይል አይደለም፤ ዓላማም ግቡንም በደንብ አያውቅም’ እያሉ መሬቱን አለስልሰው ስለነበር ለማሳመን ጊዜ አልወሰደባቸውም። ህዝቡም ይሄንን ፕሮፓጋንዳ ገዝቶ፤ አንድ ፋኖ
ሳያሰለጥኑ፣ አንድ ጥይት ሳይገዙ፣ አንድ ብርጌድ ሳያቋቁሙ የፋኖ መሪ ናቸው ብሎ ተቀበለ። አሁን እንደ ኮለኔል መንግስቱ ግዜ ታላቁ መሪ ሆነው ብቅ አሉ።

ብዙም ሰው ስላልገባው ብሩን ሰጠ። ሻለቃም ብሩን ይዘው የፋኖ ብርጌድ መሪዎችን ብር እንድሰጣችሁ ታላቁ እስክንድር መሪያችን ነው በሉ ማለት ጀመሩ። ይሄንንም ለማስፈጸም ኢትዮ360 ያለውን ተደማጭነት ተጠቅሞ ሌላ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን ለመፍጠርና ኢንጂነር ሀይሉ ሻውልን “ሀየሎም ሻውል” እያለ ባጥላሉበት ታክቲክ ዛሬም ሻለቃን የፋኖ ግንባር ታላቁ መሪ ለማድረግ እየተጋጋጠ ነው። ለምሳሌ እንዲሆን በኢንጂኔር ሀይሉ ላይ የተደረገውን ተመሳሳይ ዘለፋ ይመልከቱ

(https://youtu.be/B7th1WypBcQ?si=10nu8_AMq9ah_dqG)

ሻለቃ ዳዊት ወኪል ናቸው እስክንድር መሪ ነው የሚለው ተረት ተረት ነው። ሻለቃ ዳዊት የአስክንድር መሪ እንጂ ተከታይ አይደሉም። እስክንድር የሻለቃ ጓንት ነው። ከቦቀሱበት ቦሀላ አውልቀው ይጥሉታል። ለሱም እየሰራ ያለውን ስህተትና የወደፊት የሚጠብቀውን እንዲረዳ በደብዳቤም በቃልም ተመክሯል።  ሻለቃው ተጠቅመውበት በኋላ ያጠፉታል።

ልክ እነ መለስ ዜናዊ እነታምራት ላይኔን እንደ ኮንደም እንደተጠቀሙባቸው፤ ብርሀኑ ነጋም ቅንጅትን ለመቆጣጠርና የመላው አማራን ድርጅት ለማፍረስ የብርቱካን ሚደቅሳን ተወዳጅነት እንደተጠቀመው ዛሬም የእስክንድር ነጋን ተቀባይነት እንደ ጓንት ተጠቅሞ መጀመሪያ የፋኖን ትርከ መቆጣጠር፣ ከዛም የፋኖን ብርና ድጋፍ መጥለፍ፣ ከዛ የፋኖን ተዋጊ ኃይል በገንዘብና በኢትዮ360 ማስፈራርያ መቆጣጠር ነው።

እስክንድር ነጋ ወንድማችን ነው ለዓላማውም የከፈለውን መስዋዕትነት እናከብራልን። እሱ ሻለቃን ለማንገስ በለቀቀው ድምጽ ምክያት መንግስት ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ እስክንድርን ለመግደል ሲዘምት በመቶ የሚቆጠሩ የፋኖዎች ህይወት ገብረው እስክንድርን ማዳን የተቻለው። የአብይ ጦር በየ ገዳሙ እየገባ የጨፈጨፈው የቆሎ ተማሪና መነኩሴ ከሶስት መቶ ይበልጣል።

እስክንድር ፋኖን በማደራጀት ላይ ምንም አስተዋጻኦ አልነበረውም። ያደራጀውም 100 ተዋጊ የለውም። የፋኖ አንድነት ምክር ቤትን የተቀላቀለው ብአዴን አስሮ ለፌዴራል ሊሰጠው ሲል በፋኖ መዋቅር የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ኃይል “ምን አድርጉ ነው የምትሉት እንደዜጋ ጎጃም መኖር ወንጀል ነው ወይ” ብሎ መንገድ ዘግቶ እስርቤት ከቦ ካስፈታው በኋላ ነው።

እስክንድርን ወደ ጎንደር በማምጣት የፋኖ አንድነት ምክር ቤት መሪዎች በሚኖሩበት መደበቂያ ቤት አንድ ላይ እንዲኖርና የወረቀት ስራ እንዲያግዝ የተደረገው። ከዛ ውጪ ፋኖዎችም እስክንድር የት እንዳለ እንኳን የሚያውቁበት እድል አልነበረም። መታስሩ ለበጎ ሆኖ ከትልቁ ከፋኖ አንድነት ምክርቤት ጋር ለመስራት እድል ከፈተ።

እስክንድር ስሙ ነው እንጂ ሻለቃ ዳዊት ባቋቋሙት ህዝባዊ ግንባርም ሆነ አሁን ኢትዮ360 ሊያደራጀው በሚሞክረው ህዝባዊ ኃይል ስብስብ ውስጥ መሪም አይደለም ተደማጭነት የለውም።

እስክንድር ሻለቃ ዳዊትን የሚያዝበት ምንም ስልጣን የለውም። ሻለቃ ዳዊትም እስክንድርን መሪዬ ነው ብሎ የሚቀበሉበት ባህሪ የላቸውም። ፈረንጆቹ ጭራው ውሻውን ይወዘውዛል እንደሚሉት ነው። የሻለቃ ዳዊት ተመክረው አደብ እንዲይዙ ካልተደረጉ ልክ እነ ጀነራል ፋንታ በላይን እና እነ ጀነራል ደምሴ ቡልቶን በተሳሳተ ስትራቴጂና ሚስጥር ለሻቢያና ለወያኔ ናቅፋ ድረስ ሄደው አካፍለው ጄኔራሎቹን እንዳስጨሷቸው ፋኖንም ያስመቱታል።

እስክንድር ይሄንን ያህል ዘመን የደከመለትን ትግልና ስም ታምራት ላይኔን በሚያወርድ አጉል ሽንገላ ከተደራጀው የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተገንጥሎ አዲስ ያደራጃል ብሎ ያሰበ ሰው አልነበረም። ይህ ስህተት ነው። ያለውን አጠናክሮ መምራት ይችል ነበር።

ይህ ሻለቃ ዳዊት በፈጠሩት ቀዳዳ በርካታ እኛም እኛም የሚሉ ተሻሚዎች ማኒፌስቶ እየጻፉ የራሳቸውን ፓርቲ ለመፍጠር ተፍ ተፍ እያሉ ነው። ምክንያታቸም እነ ሻለቃ መጥተው ሊቆጣጠሩን ነው የሚል ፍርሀት ለሌሎች ብልታ ብልጦች በር እየከፈተ ነው።

ሁለት ስህተቶች ሲደመሩ ትክክል አይሆንምና ሁሉንም እረፉ እንላለን። እየመሩ ያሉት ቀንም ማታም ተኩስ ላይ ናቸው። የማይታኮሱት ደግሞ ኢንተርኔት ላይ ተጥደው ስለ ማኒፌስቶ ሲያወሩ ይውላሉ።

አሁንም ሁሉም በአንድነት ምክር ቤት ውስጥ ያላችሁን ወንበር እየያዛችሁ የውሳኔው ተሳታፊ ሁኑ የሚል ነው። 80% የሚሆነው የፋኖ ብርጌድ ትቶ የየ አጥቢያው ማኒፌስቶ መፍጠር አስፈላጊ አይደለም። የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ለሁሉም ክፍት ነው። መሪ መሆን የሚፈልግም በተግባሩ በሀሳብ ጥራቱ፣
አስቀድሞ በማሰቡ ችሎታው ያለው እጅ አውጡልኝ ሳይል መሪ የሚሆንበት ስርአት ፋኖ ገንብቶልና።

ክፍል ስድስት

አሁን ያለንበት፣ የሚቀድመው የስነልቦና ስብርትን ማቃናት ነው

ፋኖ የአማራ ሕዝብ ለሀምሳ አመት እንዲሰፍርበት የተደረገውን የራስ መጥላትና አቅመ ቢስ ነኝ ብሎ የማሰብ አዚም ከላዮ ላይ እንዲያነሳና እኔ ታላቅ ሕዝብ ነኝ። እኔ አም’ሐራ ነኝ፤ እኔ ነጻ ህዝብ ነኝ፣ ችግሬንም የምፈታው እኔው ራሴ አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ ሆኜ ነው ብሎ እንዲያስብና የአባቶቹን በራስ መተማመን እንዲገነባ በማድረግ ነው። አማራ ነጻ የወጣው ዳግምም ወደ ባርነት የማይመለሰው የፋኖ ወጣቶች ይሄንን በተቀበሉ ቀን ነው።

ዶ/ር መራራ ጉዲና “ትልቁ ድላችን የኦሮሞን ስብዕና እየገነባን የአማራ ልጆች ደግሞ እራሳቸውን እንዲጠሉ፤ ንጉሳቸን እዲገድሉ፣ ሀይማኖታቸውንና ማንነታቸውን እንዲጠየፋ በማድረጋችንና እራሳቸውን ጠልተው አባቶቻቸውን እንዲረሽኑና እንዲንቁ በማድረጋችን ነው” ያሉትን እሳቤ ማፍረስ ነው።

የአማራው ጠላቶች የሌሎች ብሄር ፖለቲከኞች ብቻ አይደሉም። ኤቢሲዲ እንዲቆጥሩ ለፈረንጅ ለማደጎ የተሰጡ የአማራ ልጆች ይብሳሉ። የአማራ ሕዝብ የተዋረደውና የተጨረሰው በነ ታምራት ላይኔ፣ በነ አገኘሁ ተሻገር፣ በነደመቀ መኮንን፣ በነ ብናልፍ አንዷለም በነ ጄኔራል አበባው ብቻ ሳይሆን እነ በዋለልኝ መኮንን፤ እነ ነገደ ጎበዜ፣ በነ፣ ሽመልስ ማዘንጊያ፤ በነ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርግስ ጭምር ነው። ንጉሱን ገለው ጳጳሱን አንቀው እነ አክሊሉ
ሁብተወልድን ረሽነው፤ አማራውን ትጥቁን አስፈትተው፣ ርስቱን ቀምተው፣ አደህይተው የደሀውን ልጅ ማግደው ያለ ሰው አስቀርተው ነው አማራውን ለህወሀትና ኦነግ መጫወቻ ያደረጉት።

ባለፉት ሀምሳ አመት በተሰራው ፕሮፓጋንዳ የአማራ ስብዕና ወርዶ የትልቁ የአማራ ማኅበረሰብእ መሪ ነን የሚሉ እንደ ብአዴን ያሉ ሰዎች በትናንሾቹ ብሄረሰብ መሪ ነን በሚሉ በነ ሬድዋን ሁሴን በጥፊ የሚወለወሉ ስብዕና ያላቸው አማሮች ተፈጠሩ።

አማሮች ተገደልን ሲሉ እንዴት ከማለት ይልቅ እንደ አገኘሁ ተሻገር ያሉ “ማን አዛ ሂዱ አላችሁ’ የሚሉ የአማራ ነፍስን ከተሰጣቸው V8 መኪና በታች አሳንሰው የሚያዮ አካለ ስንኩሎች ተፈጠሩ።

የፋኖ አንድነት ምክር ቤት አሁን ደግሞ “አንተ አማራ ዋጋ የለህም” እኔ ነጻ አወጣሀለሁ ማለት አይፈልግም። ይህ ነው ፈረንጆቹ ስውር መልዕክት (A subliminal message is a message or signal that is designed to pass below the normal limits of perception) የሚሉት።

ከታች ወደላይ እየተገነባ ያለውን የፋኖ መሪዎችና ምክር ቤት ከላይ ጉብ እንበልበት ማለት ውጤትም አያመጣም ከውርደት በቀር። የፋኖ ትምህርት አትፍራ ትምክህተኛ ቢሉህም አትሸማቀቅ። አርበኛ ነፍጠኛ ሆነህ ሀገር በመመስረትህ፣ ሀገር በመገንባትህ፣ ቅኝ ገዢዎችን በማሳፈርህ አትፈር፣ አትሸማቀቅ፣ ኩራ። እኔም ያባቴ ልጀ ነኝ በል የሚል አስተምህሮ ነው።

የአባቶችህን አራሽነት ተኳሽነት እና ቀዳሽነት ታሪክ አቧራውን አራግፈህ ልበሰው። የአባቶችህን ገድል አንብበህ በሁለት እግርህ ቁም። ማንም ነጻ አያወጣህም፣ አባቶችህ ነበሩ የአለምን ጥቁር ህዝ ነጻ ያወጡት ። አሁንም የኢትዮጵያንም ህዝ  ነጻ የምታወጣ፣ ለጥቁር ሕዝብም መመኪያ የምትሆን እንጂ አንተ ደካማ ስለሆንክ ነጻ ላወጣህ ነው የሚልህን አትስማ የሚል ነው።

ማን ሆነን ነው ይሄንን ታላቅ ሕዝብ ነጻ እናወጣሀለን የምንለው። ኤቢሲዲ ስለቆጠርን እኛ ከእናንተ እንሻላለን ማለት “ለእናቷ ምጥ አስተማረች እንደሚሉት ነው’

ይልቁንም እኔም ሰው ነኝ፣ እኔም በአባቶቼ ሀገር ላይ ድምጽ አለኝ፣ እኔም በሀገሬ ላይ ሀብት ማፍራት የመኖር፣የመንቀሳቀስ መብት አለኝ ብሎ የራስን መብት ለማስከበር የተነሳ ኃይልን መደገፍ እንጂ የከሰረን የማኦን አደረጃጀት ለመጫን አንሞክር።

አልገደልም ማለት ትምክህት አይደለም፣ ጽንፈኝነት አይደለም። በአባቴ ገድል እመካለሁ እኮራለሁ የሚል ሕዝብ መፍጠርና የተጫነበትን የስነልቦና ቀውስ ማከም ነው።

ፋኖ ከዚህ አልፎ ተርፎ ላጥቃህ ያለውን ምላሹን ለመስጠት ነው የተነሳው። አሁን ትግሉ ሁሉም በአማራ ክልል እንደታየው ለራሱ እንዲተማመን ማድረግ ነው።

አንተ መጥፎ ነህ፣ አንተ ትምክተኛ ነው፣ አንተ ቅኝ ገዢ ነሕ፣ አንተ መጥፎ መጥፎ መጥፎ ነህ፣ ዝም በል ብለው መሳሪያውን አስፈትተው ስነልቦናውን ገፈው ለህወሀትና ለኦነግ አስረከቡት ቦሀላ ማኒፊስቶ ጽፈው ነጻ እናወጣሀለን የአማራ ሕዝብ በራሱ ተማምኖ ጠመንጃውን የወለወለ ቀን ነው ነጻ የወጣው።

የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ነጻነት

የአማራ ህዝን ነጻነቱን አውጇል፣ የአዲስ አበባ፣ የጋሞ፣ የአፋር፣ የጉራጌ፣ የቱለማ ሰው አንደ አማራው እኔም ነጻ አውጪ ጠባቂ አይደለሁም ያለ ቀን ነጻ ይወጣል። ፋኖ የዛሬ አንድ አመት ተኩል ይህንን እምነት ለማስተዋወቅ የሚረዳ “የጉንዳን ትግል” የሚል አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ አደራጅቶ ለውይይት በትኖ ነበር። የዚህ ጽሁፍ ጭብጥ እያንዳንዱ እራሱን ነው ነጻ የሚያወጣው ብሎ አውጇል። ችግሩ ሁሉም ነጻ አውጪ ጠባቂ መሆኑ ነው የሚል ነበር።
ዝርዝር የጥናት ጽሁፉ ያለንበትን አገናዝቦ በድጋሜ ይለቀዋል።

ጭብጡ ግን አንባገነንነት ስርአት የሚቆመው በሁለት ኃይል ነው። ይሄኛውም አንደኛው በጥቅም በሚሰባሰቡ አንድ ፐርሰንት በማይሞሉ የስርአቱ ደጋፊዎች ሲሆን 99% ደግሞ አቅም የለንም ብሎ እንዲያስብ በተደረጉ ዜጎች ሸክም ነው።

እነዚህ 99 በመቶ የሚሆኑት ስርአት በነሱ ድጋፍ እንደቆመ አያውቁም። ማርክሲስቶቹ የተሳሳተ ስነ ልቦና ይሉታል (False consciousness refers to a concept in social theory that suggests individuals hold beliefs or ideas that are contrary to their own best interests)

እንድ ስርአት የሚቆመው ባልገባቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሆነ ሲገባቸው በቀናት ውስጥ ነጻ ይወጣሉ።

ስርአትን ለማፍረስ ጠመንጃ ማንሳትም ላያስፈልግ ይችላል። መንግስትን አለመደገፍ ብቻ በቂ ነው። ምክያቱም ስርአቱ የሚያስፈራራበት ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ፣ መርማሪ፣ የእስር ቤት ጠባቂ፣ ሰላይ፣ አሳባቂ የሚሆነው ከመሀበረሰቡ ውስጥ የወጣና ነው። ይህ ሁሉ አባት እናት ወንድም እህት አለው። በቅርብ ያለ ሰራዊቱ የጭቆና መሳሪያ መሆኑን እንዲረዳ ማድረግ በቂ ነው።

ለዚህ ነው እራሳቸውን ነጻ አውጪ፣ ፕሬዚዳንት የፖሊት ቢሮ አባል አድርገው ለመሾም የሚሹ ለአማራ ሕዝብና ለመላው ኢትጵያ ሕዝብ ምን ይበጀዋል? እኛስ ምን ይመቸናል ብለው ቢጠይቁ ተሽቀዳድመው ጥቡቆ ልስፋልህ አይሉም ነበር።

የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ማኒፌስቶ በተግባር “ሰው ሰው፣ ፍትህ ፍትህ፣ ሰላም ሰላም፣ እኩልነት እኩልነት” የሚሸት ተቋም ነው። ያለማቀፋዊ ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ተቀብሎ ፈርሞ ዘቅዝቀው የሚገድሉ ስርአት እንዳለ እያየን ነው። ስለዚህ ፋኖ ተጣድፎ ጥቡቆ መስፋቱን ስላልፈለገ ነው። ግን ሕዝብን እያዳመጠ፣ እየተወያየበት እየተከራከረበት እያጠራው የሚመጣ ፍትሀነገስት ይኖራል።

ፋኖ የት ነው?

ፋኖ ሀሳብ ነው፣ በራስ ሀሳብ በራስ ጉልበት በራስ ንብረት እራስን ነጻ የማውጣት ፍልስፍና ነው። ፋኖ አራሽ እንጂ በምጽዋትና በሌሎች ድጋፍ መቆም አይደለም።

ፋኖነት ነጻ አውጪ መጠበቅ ሳይሆን በራስ ህይወት በራስ ጠመንጃ በራስ ትግል እራስን ነጻ የማድረግ ፍልስፍና እንጂ ሕዝብን ነጻ አውጥቶ በሰፉት ጠባብ ጥብቆ ለማስገባት መከርከም አይደለም።

ከሁሎም በላይ ደግሞ ፋኖነት ቀዳሽነት ነው። ይህ ማለት ሀይማኖታዊ ስግደትና ቅዳሴ ለማለት ሳይሆን በራስ ሀሳብ እራስን ነጻ ማውጣት ነው።

በማርክስ በስታሊን በማኦ በአብረሀም ሊንከን ጥብቆ ውስጥ ሕዝብን ለማስገባት መከርከም አይደለም። በምንጃር፣ በራያ፤ በአርባምንጭ፣ በወልቂጤ እና በአዲስ አበባ ሕዝብ ፍላጎትና ጥቅም ልክ ጥብቆ መስፋት ይቀላል ነው። ለዚህ ነው ፋኖ ኃይል ብቻ ሳይሆን ጽንሰ ሀሳብም ነው የምንለው።

ለዚህም ነው ጉራ ሳይሆን ፋኖ ኢትዮጵያውያን ለአደጋ በተጋለጡበት ክፍለሀገራት ሁሉ አለ። በመንግስት ተቋማት፣ በጸጥታ ሀይሎች፣ በፓለቲካ ድርጅቶች፣ በመሀበራዊና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ፋኖ ይተነፍሳል። አሁን እንዳየነው ብዙው ጠመንጃውን እየጣለ፣ ስልጣኑን፣ ጥቅሙን፣ መአረጉንና ደሞዙን እያሽቀነጠረ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። በየቀኑ ወደ ፋኖ በሚቀላቀለው ወታደር፣ ሚሊሽያ፣ ምሁር፣ ቢሮክራሲ፣ ጋዜጠኛ ነጋዴ በርካታ ነው።

የፋኖ ያልዘረፈ፤ ያልደፈረ፤ ያላሰቃየና “ሰው ሰው” ስለሚሸተው ሁሉም ተስፋ አድርጎ ሲያየው አብይ አህመድ ደግሞ እየተናደ ያለውን ምናባዊ ቤተ መንግስቱን ለማቆም ማታ ይገሉኝ ይሆን ብሎ የሚፈራውን የራሱን ባለ ቀይ ባርኔጣ የክብር ዘበኛ እራት እየጋበዘ በየመሀከላቸው እየዞረ ሲያቅፍ ሲተሻሽ ይታያል። ጥዋት ደግሞ ጅማ ሄዶ የሚሸሽበትን ቦታና ሕዝብ ሲሸነግል ቦታ ሲመርጥ ይውላል፤ ካዛ ተመልሶ ደግሞ በጌምድርንና ራያን ውሰዱ እያለ ህወሀትን ይማጸናል። ከአማራ ሀይል ለመክፈል ጦርነት ክፈቱልኝና በአማራ ሕዝብ ከፋፍሉልኝ እርዱኝ ይላል። ይሄንን ሳይጨርስ ደግሞ የህወሀትን ሰራዊት፣ የአማራውን ማኅበረሰብ እና፣ ብሔረ ኢትዮጵያዊውን ያማልልኛል ያለውን የቀይ ባህር አጀንዳ ይለቃል። ወደ ቀይ ባህር ሊተም ነው ስንል ደግሞ ጃን ማሮን በሂሊኮብተር አፈላልጎ ጭኖ እባክህ አዲስ አበባ ዙርያ ምሽግ ቆፍርና ከኢትዮጵያ ሕዝብ አድነኝ ብሎ ይማጸናል።

በተቃራኒው ደግሞ በጥንካሬውና በጨዋነቱ በተግባር እያስመሰከረ ስርአቱን እየናደ ያለው የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ነው። በጎሳ ትስስር ለአብይ ይሞታሉ ተብለው የሚጠበቁት ሳይቀሩ ለፋኖ ክብር ሲሰጡ እያየን ነው።

ክፍል ሰባት

የስድስቱ ቀን ማጥቃት

ልክ ፋኖ በስድስት ቀን የአማራን ክልል እንደተቆጣጠረው በቅርብ ቀንም መላው ኢትዮጵያ ውስጥ ይከሰታል። በዚሁ መንገድ ስርቶ ሲያሳይ ሁሉም “የፋኖ አንድነት ምክር ቤት” ተዋጊዎች ጥበብ ይረዳል።

ይህንን ጽሁፍ ለምን አስፈለገ?

ይህ ጽሁፍ ፋኖ አንድ አይደለም፣ እንድ እዝ የለውም፣ ስለዚህ እኛ አደራጅተን እንመራዋለን የሚሉ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ስለበዙ እባካችሁ ታገሱን አደብ ግዙ ለማለት ነው።

አሁን የተጀመረው ጥድፊያ የዛሬ 14 አመት እነ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ቅንጅትን ለመቆጣጠር የኢንጂነር ሀይሉን ስልጣን ለመቀማትና የተጠቀሙበትን ስትራቴጂ ነው። (ቅንጅት መሪን ኢንጂነር ሀይሉን “ሀየሎም ሻውል” እያሉ ሲያብጠለጥሉ እንደነበረ ለማስታወስ ይሄንን ቪዲዮ ማየት ይበቃል።

(https://youtu.be/B7th1WypBcQ?si=10nu8_AMq9ah_dqG)

የዚህ ዘመቻ መከፋፈልና መጥፋት ነው ያመጣው።
ፋኖ ለገበያ የቀረበና የሚሸጥ የአማራ ስነ ልቦና የለውም። ለረጅም ግዜ የአማራ ፋኖ ትግል ሲረዱ የቆዩትን እነ AAA (Amhara Association of America) እና iAM (International Amhara Movement) በነሱ ስር ያሉ ስብስቦችንና ግለሰቦችን በማጥቃትና በመከፋፈል እየተደረገ ያለው ሙከራ ትግሉን ይጎዳል።

ይሄንንም ብዥታ ለማጽዳት ስላስፈለገና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ “ነገርን አዳምጦ እህልን አላምጦ” እንደሚባለው እውነታውን እንዲረዳ ነው።

ይህ ለምን ሆነ?

ፋኖ ከፈረንጅ ተውሶ ያልተላመጠ ፍልስፍና ነጻነትም እኩልነትም እንደማይመጣ የኢትዮጵያ የ50 አመት ትግል ውጤቱ ይታወቃል።

ይልቁንም በአለም ላይ ብቸኛዋን ነጻ ሀገር ፈጥረው ለሶስት ሺ ዘመን ያቆሙትን የአባቶቻችን አስተምህሮና ጥበብ መልሶ በማጥናት ነው። ስለዚህ አባቶቻችን ቢሆኑ ይህንን ችግር እንዴት ይፈቱታል በማለትና በመፈተሽ ነው።

አንደኛውና ዋነኛው ፋኖ የሚቃወመው፣ ”የነጻ አውጪና ነጻ ወጪ” የሚለውን የማርክሲስቶቹ ትርክት ነው። በሌላ ፍልስፍና ነጻ አውጪ (vanguard) በሌላ ወገን ደግሞ ማሰብ የማይችል መብቱን የማያውቅ ሰፊው ሕዝብ (the mass) ወዘተ ብሎ የአማራን አርሶ አደር እንደ ዲዳ መናገር የማይችል እና የሚነገረውን ማድመጥ ብቻ ያለበት ነው ብሎ በመመደብ አይደለም። ብዙ ነጻ አውጪ መጥቶ ሄድወል ጭቆናና አፈና ግን አልቀረም።

ስለዚህ ፋኖ እራሳቸውን ነጻ ያወጡ ነጻ ዜጎች ብቻ ናቸው ነጻ ሀገር መፍጠር የሚችልሉት ብሎ የሚያምነው። ስለዚህ አባቶች እንዳስተማሩት ምሉዕ ዜጋ ለመፍጠር እያንዳንዱ ዜጋ “አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ” ማድረግ ነው ።

“አራሽነት” እራስን መቻል ነው። በራስ ሀብት፣ በራሱ ንብረትና በራሱ ላብ ላይ መቆም ነጻ መሆን እንጂ በመጽዋት፣ በድጋፍ፣ በልመና ነጻ ሀገርም ነጻ ዜጋም አይፈጠረም ብሎ ያስተምራል።

ሁለተኛው ነጻነት ያለ “ተኳሽነት” እራስን የመከላከል አቅም አይመጣም። ኢትዮጵያ በታሪኳ የወረችው ሀገር የለም። ይሁና አቅም አልነበራትን ማለት አይደለም። ከነ አሌክሳንደር ዘግሬት፣ የሮማን ኢምፓየር፣ የኦቶማን አንፓየር፣ የማምሉክስ ኃይል፣ ግብጽ፣ ከፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና ጣልያን አካባቢዋን ሁሉ እየወረሩ ሲገዙ ኢትዮጵያን ግን አልቻሉም። ይህም በዘመናዊ ጦርና ታንክ ሳይሆን ሁሉንም ተኳሽ የሚያደርግ ስራአትና ባህል ስለነበራት ነው። የአማራ ወጣት አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ መሆንን በዘመናዊ ትምህርት አራክሰው እንዲጥል ካደረጉት ቦሁላ እንደ እርድ ከብት እያሰለፉ ያርዱት ገቡ። አሁንም ወደፊትም ልጆቹ ተኳሽ ሳያደርግ ያሳደገ አባት ልጁን ለተገዢነትና ታራዥነት እያዘጋጀ ነው ብሎ ፋኖ ያምናል።

መተኮስና ማረስ ብቻ ነጻነት አያጎናጽፍም። ማሰብ ግድ ነው። ይህም “ቀዳሽ” በሚለው ጽንሰ ሀሳብ ነው። ፈርኦኖች ስክራይብ (scribes)፤ ኢሮፕያውያኑ ደግሞ ስኮላርስ (scholars) የሀሳብ ሰዎች (men of worlds) አሁን ደግሞ ልሂቃን (intellectuals) ብለው ይጠራቸዋል። በራሱ ማሰብ የማይችል ግለሰብም ሆነ ማኅበረሰብእ ኤቢሲዲ (ABCD) በቆጠረ እመራለሁ ሲል የሚሆነውን ለ50 አመታት አይተናል።

ካፒታል፣ ፋብሪካ፣ ሀብት ባልተፈጠረበት ሀገር የመደብ ልዮነት አለ ብለው እንደነ ጸሀፊ ትዕዛዝ አክሊሉ፤ እንደነ አበበ አረጋይ፤ እንደነ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ያሉትን ሀገርን በደማቸው ያቆሞትን፣ በጻም በጸሎት ሀይማኖት ያስተማሩት ጳጵሳትና መነኩሴዎች አንቆ የሚገል አባቱን የሚንቅ የሚያዋርድ ትውልድ ይፈጠራል።

ለዚህ ነው ፋኖ ትልቅና ትንሽ፣ መሪና ተመሪ፣ ነጻ አውጪና ነጻ ወጪየሚለውን ትርክት ለማጥፋት የሚሰራው። ይህ ያልገባቸው የማርክሲስቱ አስተምህሮ ልክፍት ያልተላቀቃቸው አሁንም ታላቁ ታናሹ፣ የምልህን ካልሰማህ አዋርድሀለሁ የሚሉትን እባካችሁ አደብ ግዙ የምንለው።

ከአንድ ክምንጃር፤ ከአርማጭሆ፤ ወይም ከሰቆጣ ካለ ገበሬኤቢሲዲ የቆጠረው ስለገበሬው ችግር ከገበሬው በላይ አውቃለሁ የሚለውን የ50 መታታት መታበይ የማስቆም ነው። ለፋኖ “በአራያ ስላሴ የተፈጠረ ሰው ሁሉ እኩል ነው”። በትምህርቱ፤ በእምነቱ በብሄሩ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋው አያበላልጥም አያገልም አያጠቃም።

አባቶቻችን ይህቺን ሀገር ለስድስት ሺ ዘመን ያቆያት አካለ ስንኩል ቢሆን፣ ቢቆመጥ፣ ከሰውነት ወርዶ የተሳቆለና ቢሆን፣ የሚበላው የሌለው የነጣ የገረጣ ቢሆን “በአእያ ስላሴ” የተፈጠረ ሰው ነው ብለው፣ አክብረው፣ አብልተው። አጠጥተው ቢሞት እንኳን ገንዘው ፍትሀት ፈትተው፣ ሰልስቱን፤ አርባውን አስበው ነው የሚሸኙት እንጂ ደሀነው ብለው አይጥሉትም። ይህ በክርስቲያኑም በእስልምና ተከታዮም ያለና የቆየ እሴት ነው። ዛሬ ግን ህጻናትን የሚያርድ፤ የእርጉዝ ሆድን የሚቀድ፤ እናት አባትን አርዶ ልጆችን “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” የሚያስብል አረመኔ ስርአት መጥቷል ፋኖ ይህንን “ወላሂ እኔ ሁለተኛ አማራ አልሆንም የሚያስብል ስርአት ለመደምሰስ ነው የሚታገለው። ለዚህም ነው ፋኖ በመላው ኢትዮጵያ ተስፋ የጫረው።

ፋኖ ወንድማማችናት እንጂ “መሪ ተመሪ፡ ታላቁ ታናሹ፡ አንቂ ነቂ፡ ነጻ አውጪ ነጻ ወጪ” የሚል የማርክሲስት አስተምህሮ እርግፍ አድርጎ ስለጣለ ነው ኃይል የሆነው። ፋኖ እንደ ብርሀኑ ጁላ እና እነ ጀነራል አበበ ወረደ እንደሚመሩት ግባ በተባለው አይኑን ጨፍኖ የሚገባና የሚማገድ አይደለም። ከሃላው ሆኖ “ለትግራይ አልሞትም ካለ ረሽነው” የሚል አመራይ ይዞ አይደለም የሚዋጋው። ፋኖ ቁጥር ሳይሆን በአርአያ ስላሴ አምሳል የተፈጠረ ክቡር ሰው መሆኑን ያምናል። የፋኖ ወጣቶች የሚሰውት ለራሳቸው ለቤተሰቦቻቸው ለሀገራቸው ክብርና ነጻነት መሆኑን ስላመኑ ነው። በራሳቸው ህይወት ላይ በሚወስን አጀንዳ ላይ ሙሉ ተሳታፊና መካሪ እንዲሆኑ ስርአት ስለተዘጋ ነው ታንክና ድሮንስ ያለውን ስርአት እየደመሰሰ ያለው።

የፋኖ ዝግጅት

አባቶቻችን ሁለቱን ወገን ሳያዳምጡ አያስታርቁም ወይንም አይፈርዱም ነበር። ፋኖ ቀዳሽ ማለትም አሳቢ ባይሆን ኖሮ ህወሓት ተሸነፈ ብሎ ጉሮ ወሸባዬ እያለ ወደ ቤቱ፣ ዩኒቨርስቲው፣ እርሻውና ንግዱ ይመለስ ነበር።

አብይ ራያ ላይ ቁሙ ብሎ ክፊት ቀድሞ የሄደውን ፋኖ ሀይል በምድፍ ሲደበድብ የበሻሻው አራድነት ግልጽ ሆነ። ይህ ከታየ ቦሀላ በመንግስ የሚከፈትብንን ጦርነት ለመመከት የፋኖ ስልጠና በአስቸኳይ እንዲቀጥል፣ ጉሮ ወሸባዬ እንዳይዘፈን፣ የመከላከያ ወረዳዎችና መልከዐ ምድሮች በአስቸኳይ እንዲመረጡ፣ ስንቅና ትጥቅ እንዲከማች፣ ጥቃት ሊፈጽምባቸው የሚችልባቸው ኦሮምያን የሚያዋስኑ ወረዳዎች በአስቸኳይ ህዝቡ እንዲሰለጥንና እንዲታጠቁና እራሳቸውን ከመጥፋት እንዲላድኑ የሚል ነበር።

ይህንን አጥር ለመገንባት ሙሉ ግዜያቸውን ሰጥተው በእያንዳንዷ አዋሳኝ ወረዳ ሰዉ እንዲደራጅና እራሱን እንዲያሰለጥን እንዲታጠቅ ኃይል ተሰማራ። ይሄንን በፍጥነት ያስተማሩና ያደራጁ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከዲያስፖራም የመጡ ወጣቶች ነበሩ። እንደተባለውም በአጭር ግዜ ተአምር ሰሩ። የሰው አጥር ተገነባ። ይህ እንግዴህ የሁለተኛው ምዕራፍ ጦርነት ማለትም ህወሓት ሽንፈቱን ተቀብሎ ፊርማውን ከማስቀመጡ አንድ አመት በፊት ነው።

የፋኖ ጥንካሬው ጥይት መተኮሱ እና ጀግንነቱ ሳይሆን አስቀድሞ ጥያቄ ጠይቆ ማሰብና መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉንም ማሳተፏ ነው።

አብይ አማራውን እንደሚወጋ መተማመን የተደረሰው በራያ ጉዳይ እንጂ የብርሀኑ ጁላ ጦር ጎጃምን ሲወር አይደልም።

 ህወሓት ሳያውቅ ያከሸፈው የኩሽ እቅድ

የህወሃት መሪዎች መተኮስ ቢችሉም አርቆ የሚያስብ ሰው ግን የላቸውም። ማሰብ ያስፈራቸዋል። ምክንያቱም ማሰብ የራስን ሀሳብና እይታ ይፈጥራል። የራስ ሀሳብ ካለ ደግሞ የሁለት ሰዎች ሀሳብ አንድ አይሆንም፣ አንድ ካልሆነ ደግሞ አንድነት አይኖርም ብለው እንዲያስቡ ስለተደረጉ በራስ ማሰብ የተወገዘ ሀጥያት ነው።

የአብይ አህመድ ጦር ደግሞ ከመጀመሪያውም ማሰብ አይፈቀድለትም። ይህ ስትራቴጂ አያዋጣም ያለ ብሄሩ ተጠይቆ በጠላት ይመደባል። ከታች ወደላይ በብሄራቸው የተትትኮሱት ደግሞ የተማረኩና ወታደራዊ እውቀት የሌላቸው ናቸው። ስለዚህ እውር እውርን እንዲመራው ነው የተደረገው። ለዚህም ነው የሚያስበውን አንድ ተራ የፋኖ ታጋይ የአብይ ያማያስብ ጄኔራል መመከት ያልቻለው።

ለዚህም ነው ፋኖ ድል አድራጊዋን የኢትዮጵያ ባንዲራ በድጋሜ አራት ኪሎ ላይ የሚያውለበልበው።

 

Related: