የአምባገነን ስርአት ማስወገጃ ስልት

የለውጥ መንገድ፡ ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት የተሰጠ የመወያያ ነጥቦች

ትልቅ ግንድን ምስጥ የሚበላው በትንሹ/ በማይክሮ ግራም/ የሚገመት ነው። መፍለጫ መጋዝ ይምጣልኝ አይልም። የኢትዮጵያም ነጻነት የሚመጣው ሁሉም በጥቃቅኑ ሲሳተፍ ነው።

የጽሁፉ ጥቅል ጭብጥ

አሁን ሰላማዊ አመጹ በአማራ ክልል ተጀምሯ ሌሎች ይህ ሀይል ነጻ ያወጠናል ብለው ከጠበቁ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት
ይሰራሉ። ግዙፍ የመንግስት ስርአት የሚቀየረው በግዙፍ የህዝብ ሀይል ነው።

1ኛ አምባገነንነት ያለ ህዝብ ድጋፍ ለአንድ ቀን አንኳን አይቆምም። አንባገነን ጥቂቶች አውቀው በመደገፍ ብዙዋች
ደግሞ ባለማወቅ አንባገነንነትን በራሳቸው ላይ ሰለሚያነግሱት ይላሉ ጠበብቶቹ። እርስዋ ዛሬ ምን አደረጉ?

አንደኞው ደጋፊ በጥቅም ወይንም በእምነት የስርአቱን ካድሬ ሆኖ የሚቆም ሲሆን ይህ ሁሌም በጣም
ጥቂት የህብረተሰብ አካል ነው።
ሁለተኛዎቹ ደግሞ በየዋህነት መንግስት “ህጋዊ ነው” ብለው የሚታዘዙ፣የተባሉትን ሁሉ የሚፈጽሙና
የሚገረፉበትን አለንጋ ቆርጠው የሚያቀብሉ ዜጎች ናቸው። ይህንን ውነታ ‘manufacture of consent’
ይሉታልi (Edward S. Herman and Noam Chomsky, Antonio Gramsciii) ። ይህ ቡድን በመቶ
ሚሊዮን የሚቆጠር ሲሆን አይኑ የተከፈተለት ቀን ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ስራት የመፍጠር አቅም
አለው። ይህንን አንዳያይ በፕሮፖጋንዳ እንዲታወርና እንዲፈራ በመደረጉ ማርክሲቶች የሀሰተኛ ህሊና
እስረኛ ነው/ false consciousness/ የሚሉት ነው። ይህን በምሳሌ ለማሳየት ለምሳሌ ብአዴን ከኦፒዲኦ
ሲወዳደር የገዘፈ ሀይል ቢኖረውም የብአዴን መሪዎችን ኦፒዲኦን አግዝፎ እንዲያደርጉ ስለተደረጉ
መታዘዝ፡ ሲገደሉ በል ዋጥ አርጋት ሲባሉ ዋጥ የሚያደርጉ ሆንዋል። ለነ ደመቀ መኮንን ለነ አበባው አቅም
ማጣት ሳይሆን የበታችነቱ ጭንቅላት ውስጥ የተቀበረ ነው። ከዚህም አልፎ መንግስት የሚባለው ሀይል
ከህዝብ ሀይል ጋር ሲታይ ኢምንት መሆኑን ነው። ይሁንና አዲስ አበባ፤ ደቡብ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሱማሌ
እንዲሁ በ false consciousness ታስሮ ደንዝዞ ይጠብቃል።

2ኛ ሌላው መንግስት አቅም አለው ብሎ የሚፈጠረው የስነ ልቦና መሰለብ ነው። ማንም የህዝብን አቅምና የመንግስን
አቅም ለመመዘን ሳይሞክር፤ ልዮነቱን ለመረዳት ሳይሞክር መንግስት አይነኬ ነው ብሎ እንዲያስብ በመደረጎ ነው።

ለምሳሌ 1፣ ብልጽና ፈተና ቢገጥመው አብሮት ለመሞት የተዘጋጀ አንድ ሺ ሰው አይኖርም። ለፓርቲዮ ለአብይ አህመድ ግንባሬን እሰጣለሁ የሚለው አስር ሰው ከተገኘ በጣም ብዙ ነው። ከኦፒዲኦ ጋር አብሮ ለመብላት ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ካድሬዋች አሉ። ይሁንና አብሮ ለመሞት የሚቆም ግን የለም። እስቲ አይናችሁን ጨፍኑና ከአብይ ጋር አብረው ይሞታሉ፤ ለአብይ ብለው ግንባራቸውን ለጥይት ደረታቸውን ለጦር ይሰጣሉ የምትሉት ካለ ጻፉ። እስቲ አስቡት አገኘሁ ጥሩነህ ነው፣ ሬድዋን ሁሴን ነው፣ ተሾመ ቶጋ ነው፣ ፤ ጀ/ል አነባው ነው፤ ሽመልስ አብዲሳ ነው ዳናኤል ክብረት ነውና ብለን ስዩም ናት፣ ሳህልወርቅ ናት፣ በለጠ ሞላ ነውና ስዩም ብናልፍ ነው ወይስ ብርሁኑ ጁላ? አንዳቸውም ተታከው መክበር እንጂ የሚሞትለት አይኖርም። እንደውም ጊዜ ዘንበል ሲል እነሱ ልክ ህወሀትን እንዳደረጉት ራሳቸው ሳንጃቸውን ይመዙበታል። እነ ሬድዋን ሁሴን ሲለፈልፉ ከህወሀት በፊት ግንባግን የሚሰጡ ይመስለን አልነበረምን?

ለምሳሌ 2፣ የብአዴን ካድሬ፣ የኦፒዲኦ ካድሬ፣ የደቡብ ካድሬ፣ የስልጤ ካድሬ፣ የሲዳማ ካድሬ፣ የሀረሪ ካድሬ እና ሌሎችም ህወሀት ደብረብርሀን በደረሰ ግዜ ብልጽናን ሊያፈርሱብን ነው፣ መሪዮን ሊጥሉ ነው፣ ይሄንን ከማይ እኔ ልሰዋ ብሎ የዘመተ አንድ ካድሬ ነበር? ካለ ሜዳልያ ይገባዋል። ይልቁንም በካዝና ያለ ብር ተካፍለው ለመሸሽ ነው የወሰኑት። የሞተው ከላይ ያየነው “የዋሁ ደሀ ህዝብ” ነው ምክንያቱም አንቶኒዮ ግራምቺ እንዳለው እነዚህ ደሆች የ ‘manufactured consent’ ወይንም “አዚም” ሰለባዎች ናቸው።

ስለዚህ እነ ግራምቺ አንባገነኖችን ማስወገጃ በጣም ቀላል ነው ይላሉ። ነጻነቶን ከናፈቁ በትዕስት ይንብቡና ራስዎን ነጻ ያውጡ። የአለም አቀፍ ተሞክሮን ለኛ እውነታ እንደሚስማማ አድርገን በዚህ ጽሁፍ አቅርበነዋል።

በአጭሩ ነጻነት የሚመጣው “የዋሁ ህዝብ” ለመንግስት ያበደራቸውን ነገሮች መልሶ መውሰድ ሲጀምር ነው።

ለምሳሌ የአማራ ህዝብ የብአዴን ካድሬዎች ህዝብን እንዲያስፈራሩበት፣ አጃቢ ሆኖ እንደ አንበሳ የሚንጎማለሉበት፤ ኬላ አቁመው ህዝብን የሚያጉላሉበት የአማራ ልዩ ሀይል ነበር። ይህ ህዝብ ለብአዴን ያዋሰው ሀይል ነበር። አሁን ይህንን ሀይል መልስልኝ ሲል ሀይሉ ከህዝብ ጋር ሲቆም የብአዴን መሪዎች ሮጠው አዲስ አበባ ገቡ።

ለዚህ ነው የዋሁ ህዝብ ለመንግስት ያዋሳቸው የመጨቆኛ መሳሪያዎችን የሚከተሉት ናቸው። እስቲ መልሰን
እንበለው። ስለዚህ መንግስትን ዛሬውኑ መልስልኝ በማለት ብቻ የሚፈልገውን አስተዳደው መፍጠር ይችላል።

1ኛ፣ መንግስት ህጋዊ ብሎ ህዝብ ሲቀበክ የኢፍትሀዊ ተግባር ተሳታፊ ይሆናል፣ ለመንግስት መታዘዝ የሞራል ግዴታ ነው ብሎ ያስባል (false consciousness) ። አሁን አማራ ክልል እንደታየው ለመንገስት መታዘዝና መደገፍ ግዴታ አይደለም። እልሰለፍም አልደግፍም ልጄን አሳልፌ አልሰጥም በማለቱ ብቻ መንግስት ታንክና ወታደር ለመላክና ለማስፈራራት እየሞከረ ነው። በፊት ማስፈራሪያው ከህዝብ የተሰጠው ልዩ ሀይል ነበር። ግን ይህ ሀይል እንቢ ሲል ስራአቱ ተርበተበተ። በቅርብ ግዜ ደግሞ ህዝቡ ወታደር ልጆቹን መልስልኝ ካለ ልጆቼ ህዝብ መጠበቂያ እንጂ ህዝብ መግደያ አይሆኑም።

2ኛ፣. የህዝብ የመንግስት ማስፈራሪያ የሆነውን የሰው ሀይል አበዳሪ ነው። ህዝብ ነው ለመንግስት ልጆቹን ወታደር፣ የፖሊስ፣ ሚሊሽያ፣ ካድሬ፣ አቃቤ ህግ፣ ዳኛ፣ ገራፊ፣ ህግ አስከባሪ፣ ቢሮክራሲ፣ ጋዜጠኛ እንዲሆኑ የሚያውሰው። ይህ ግዴታው ሳይሆን መንግስት ያለ ተጨቋኙ ድጋፍ መቆም ይችላል የሚል አዚም ውስጥ ስለሚገባ ነው። ህዝቡ ላይ የሰፈረው አዚም ብደግፍ ባልደግፍ፣ ብታዘዝ ባልታዘዝ ምን ለውጥ አመጣለሁ ብሎ እራሱን እንዲያይ ስለተደረገ ነው።

ህዝብ ልጆቼን መልስልኝ የሚልበት አካሉን ጉትተህ ስጠኝ ማለት አይደለም። አቃቤ ህግ ሆኖ የተቀጠው ልጁ የውሸት ክስ አልመሰርትም በል ነው። ታዝዤ ነው ብሎ የሀሰት የፈጠራ ወንጀል መፈብረክ ግዴታ አይደለም በምድርም በሰማይም ያስጠይቃልና ይህንን የወንጀል ጥዋ አትጠጣ ማለት ነው። ፓሊስ ልጁን በህዝብ ላይ አልተኩስም ይላል በግፍ ባጠፋሀው ህይወት በምድርም በሰማይም ትጠየቃለህ ማለት ነው። የሰራዊቱ አባሎች ደግሞ እኔ ዳር ድንበር ማስከበር እንጂ በህዝቤ ላይ አልተኩስም ማለት ነው። የህዝቤ ጠባቂ አንጂ የአንባገነን ዘበኛ አይደለሁም ማለት ነው። ጋዜጠኛ ደግሞ ለ3 ዶላር በቀን ድሞዝ ብዬ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ አይሰራም ማለት ነው። በድህነት ወለል ላይ ያለ ቢሮክራሲና ጋዜጠኛ በእርግጥ ለዚህ
ኑሮ ያጓጓል።

እነዚህን የአንባገነኖች መመኪያ እና እንደ ተናካሽ ውሻ ማስፈራሪያ የሆኑ ሰዎች ወንድም፣ እህት፣ ሚስት፣ አባት፣ እናት፣ ጓደኛ እና መሀበረሰብ አላቸው። የነቃ እና እራሱን ባርያ አላደርግም ያለ ህዝብ ምንም ባያደርግ እንኳን ልጄ፣ ባሌ፣ ወንድሜ በወንጀል ተሳታፊ አትሁን ብሎ ማለት ለትግሉ ትልቅ እስተዋጽኦ አለው። አሁን የብአዴን አድማ በታ ኝ ነን ያሉና ወንድማቸውን በመግደል ብር እናገኛለን ብለው የሚጓጉትን ይህ ቀን ያልፋል የአብይና የኦሮሞ የበላይነትም መወገድ የማይቀር ነውና ያኔ ለራስህስ ለልጆችህስ ለምን በቀል ትዘራለህ ብሎ መምከር ከባድ ነውን? ይህ ነው የጉንዳን ትግል የምንለው። የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የሚለው። እንቢ ያለውን ደግሞ በመሀበራዊ ተጽዕኖ ይቀጣል። ህዝብ ይህንን ሲረዳ
ለመንግስት የሚመካበት ነገር ሁሉ ህዝብ ለመንግስት ያዋሰውን ልጅ እንጂ መንግስት ያስፈለፈለው ወይንም ከቻይና በኮንቴነር ያስገባው ሰራዊት አይደለምና።

3ኛ ህዝብ የመንግስት የፋይናንስ፣ የጊዜ፣ የጉልበት ምንጭ ነው። የባርያ ስርአት ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ባሮችን በጥቂት ሰዎች ነበር የሚነዱት። ምክንያቱም ባሮች የባሪያ አሳዳሪው የሀብትና የጉልበት ምንጭ መሆናቸውን ባለመረዳታቸው ነው። አንባገነን ስርአትም እንደ ባርያ አሳዳሪ ስርአት ነው።. በህዝብ አይን እንደ ሰጪ ለጋሽ ደጋፊ ሆኖ ይቅረብ እንጂ የመንግስትን ራሱ የህዝብ ተደጋፊ ነው። ይሄንን መገንዘብ ብቻ በቂ ነው። 120 ሚሊዮን ህዝብ የሰበሰበውን ሀብት ወስዶ አብይ አህመድ በዙንቢል ለድሆች ጎመንና ድንች አያደለ እንደኛ የሰጠ የለም ይላሉ? ህዝብ አብይ ከየት ያመጣው ብር ነው። የህዝብን ብር ወስዶ መልሶ ልጋሽ መምሰል ከዛ መመረቅ የሀሰት ስነልቦና የሚባለው ነው። ከህዝቡ የሰበሰበችውን ቀረጥ ወስዳ ልክ ክራስዋ እንደወጣ በትምህርት ቤት ምግብ እየሰጠን ነው ትላለች አዳነች አቤቤ። ይልቁንም ህዝብ ለአዳነች አቤቤ ካልሰጠ መንግስትና ካድሬው ይበተናል። ስለዚህ ለመንግስት አትስጥ። በተቻለህ መጠን ሁሉ እወደዳለሁ ብለህ ብርሃን አትስጥ፣በየ ስጋ ቤቱ ካልከፈልኩ ውስኪ ካላወረድኩ አትበል። አንተም በባርነት እየኖርክ በባንኮኒ ላይ ውስኪ መጠጣት ምን አይነት ግብዝነት ነው። መጀመሪያ ባርያ ሳልሆን ሰው ነኝ በል።

4 ህዝብ የሞራል ምንጭ ነው። በየተጠራበት አዳራሽ ሄዶ ማጨብጨብ ግዴታው አይደለም። አለማጨብጨብ፣ አለማዳነቅም፣ አለ መሰለፍ፤ አለመጋበዝ የህዝብ መብት ነው። በየ ሶሻል ሚዲያው ማጋራቱ፣ ማሽቃበጡ የህዝብ ግዴታ አይደለም። የመንግስትን ፕሮፓጋንዳና ማስፈራሪያ በራስ ቴሌቭዥን አለማድመጥ የህዝብ ግዴታ አይደለም። አንድ ካድሬ በሶስት ስብሰባ ላይ ባይጨበጨብለት ካድሬው መስመሩን ይቀይራል ወይንም ሁለተኛ ህዝብ ፊት መቅረብ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ሲረዳ ይቀየራል። ሳሎንህ ግ ገብቶ በግድ ቴሌቭዥኔን እይ አላለህ በቃ በቴሌቭዥንህ ላይ እንኳን ሰው ሁን። ፕሮፓጋንዳ አትመገብ። ፕሮፓጋንዳው አንተን አቅመቢስ እንደሆንክ በማሳመን ባርያ እንድትሆን ነው። የሳሎንህ
እንኳን ጌታ ሁን። አንተ የራስህ ሰው እንድትሆን ነጻ አውጪና ፈቃጅ አትጠብቅ።

ስለዚህ የአዲስ አበባ፤ የሸዋ፣ የጉራጌ፣ የደቡብ፣ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የሱማሌ፣ የኦሮሚያ ህዝብ ለመንግስት ያዋሳቸውን ነገሮች መልስልኝ ማለት አለባቸው። አማራ ልዮ ሀይሉንና ሚሊሻውን አስመልሷል ለመከላከያ የሰጠውን ልጆች ማስመልስ ጀምራል። በህዝባችን ላይ አንተኩስም አያሉ ነው። የቀሩትም ከባርነት አዚም ሲነቁ ወደ እሳት ሊማግዳቸው ያሴሩትን መሪዎች እያሰሩ ለፍርድ ያቀርባሉ።

ክፍል ሁለት

የኢትዮጵያ ህዝን ነጻነት፣ ዲሞክራሲን፤ ሰላምን፤ እኩልነትን፤ፍትህን፤ አንድነትና በነጻነት ሀሳብ መስጠትን ለማግኘት ቢመኝም ይህ ምኞት ላለፉት ሀምሳ አመታት እውን አልሆነም። ሁሌም ብልጣብልጦች በሰዉ ልብ ውስጥ ያለውን ምኞት እያጠኑ እኔ ስልጣን ስይዝ አሳካልሀለሁ፣ “ከዘሬ ወዲህ ሳናጣራ አናስርህም፣ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ ትሆናለህ፣ ትበለጽጋለህ እንጂ ያለችህን ቤት አናፈርስም” ብለው ህዝቡን ያስፈነድቁትና ከህዝብ በተሰበሰበ ብር ሰራዊት ካደራጁ ቦሀላ መግረፍ፣ መርገጥ፣ መግደል፣ ማሰር፣ መሳደብ ዋነኛ ተግባራቸው ይሆናል። ብትታሰር አትሟሟ። ሁሉም ለመታሰር ከተዘጋጀ ታሳሪው ከአሳሪው ይበዛልና በፍርሀት ቆፈን ባርያ አትሁን።

የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ለወራት በርካታ ምሁራንን እየጠራ ሀሳብ አሰባስቧል። ባደረኛቸው ውይይቶች ላይ ለምን የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስት ጊዜ ታለለ የሚለው ጥያቄ ለረጅም ግዜ ያከራከረንና በርዕሱም ላይ ንባብ እንድናደርግ ያስገደደን ጥያቄ ሆነ። በመጨረሻ የደረስንበት ድምዳሜ ብልጣብልጥ አንባገነኞች ብቻ ሳይሆኑ እኛ የኢትዮጵያዊያን (ህዝብ ባጠቃላይ) ለመከራችን ተጠያቂዎች ነን የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስን።

ይህ አባባል “ህዝብ አይወቀስም” የሚልውን የማርክሲስቶች ማታለያ አንቀበልም። ቤቱ ቁጭ ብሎ አንድ ብር ሳያዋጣ ሌላው ዱር አድሮ ከዛ መጥቶ መብት እንዲሰጠው ሀሳቡን እንዲያደምጠው የሚፈልግ ማህበረሰብ በሀሰት ተስፋ ይታለላል። ህዝብ ይታለላል፣ ህዝብ ይሳሳታል ምክያቱም ህዝብ በራሱ የሚኖር ሳይሆን የግለሰቦች ድምር ነው። ግለሰቦች የስህተት ድምር ውጤቱ የህዝብ ስህተት ይሆናል። በአጭሩ ግን ግለሰቦች እራሳቸውን ታግለው ነጻ ማውጣት ሲጠበቅባቸው ነጻ አውጪ ጠባቂ ሲሆኑ ዋጋ ይከፍሉ።

የመጣውን ለውጥ ሁሉ ለመቀበልና ለማጨብጨብ ይገደዳሉ። ስለዚህ የበግ ለምድ የለበሰ ነጻ ላወጣህ ነው ያለውን ሁሉ አጨብጭቦ ይቀበላልና ከጭቆና ወደ ጭቆና ይሸጋገራል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ስንወያይ ስለ አንባገነንነት ባህሪዎች የተጻፉ የምርምር ህትመቶችን መርምረናል። ለምሳሌ አንቶኒዮ ግራምቺ የሚባለው የጣልያን ማርክሲስት ፈላስፋ ‘ hegemony’ and the ‘manufacture of consent’ 1 ብሎ የሚያነሳቸውን ነጥቦች በደንብ ተመርምረዋል። በተጨማሪም በቅርብ ግዜ የታተመው ከዲክታተርሺፕ ወደ ዲሞክራሲ የሚለው በጄን ሻርፕ አይተናልiii

የመጨቆኛችን ዱላ አቀባይ እኛው ነን

120 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ሁሌም 119 ሚሊዮኑ ና ለሀገርህ ሙት ሲባል ይሰለፋል፣ ልጅ ይሰጣል፣ ስንቅ ያዘጋጃል፣ ኢትዮጵያ ያለውን ሁሉ ሙሴ ይላል። ይሁንና ለራሱ መብት ሲሰለፍ፣ ሲታገል፣ እልታዘዝም ሲል ወይንም የጉንዳን ያህል እንካን ሲቆነጥጥ አይታይም። ምክያቱም ነጻነት የሚገኘው 119 ሚሊዮን ህዝብ በትናንሹ እንደ ምስጥ ሲቆነጥር ለገዢዎች አይመችም። አንድ ጉንዳን ስትቆነጥጥ ከመቀመጫ ታስፈነጥራለች። ስለዚህ ህዝብ የማይመች እሾክና ጉንዳን ከሆነ ነው እላይ ላይ የሚቀመጡበት። ህዝብ ሌላ ነጻ አውጪ ሙሴ ከጠበቀ ከባርነት አይላቀቅም። የአማራ ገበሬ ገብቶታል የአማራ ባለሀብት ግን በውስጡ ያለው ባርነት ብሩ አላላቀቀውም። ለትንሽ ወንድሙ ቀለብና እራሱን መከላከያ ዱላ እንኳን አይገዛለትም። ባርያ አድርገው ለሚገዚት ደግሞ ሲያሸረግድ ይታያል። ነጻ አውጪ ጠባቂ መቼም ነጻ አይወጣም።

ምሳሌ ወደ ስድሳ ሚሊዮን የሚገመተው የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ አለ። ዛሬ አንድ የስልጤን ወይንም የአደሬ ሰው በጥፊ ቢመታ እሳት ይነሳል። ይሁንና 60 ሚሊዮን ህዝብ ተከታይ ያላት ቤተ ክርስቲያን በእሳት ስትለኮስ መእመናን በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ 60 ሚሊዮን ሰዎች ሻማ አብርተው በፌስ ቡክ ይለጥፋሉ። ከቤታቸው በር ላይ ቆመው ብረድስትና ቢደበድቡ እንኳን አንባገነኖች ሀገር ጥለው እንዲሸሹ የሚያስችል አቅም እንዳላቸው አያውቁም። ይሁንና false consciousness አዚም አቅም የለንም ብለው እንዲያስቡ ሆነዋል።

ሰሞኑን እንደታየው ዱላና አርጩሜ ህዝብ ይዞ ሲወጣ እበላ ባይ ካድሬ አገር ጥሎ ይሸሻል። አንቶኒዮ ግራምቺ አንባገነኖች መጀመሪያ false consciousness ይፈጥራሉ ከዛም manufacture of consent’ ያገኛሉ የሚለው። ለዚህ ነው እዚህ ሀገር ትላልቆቹ ብሄረሰቦች እንደ ጥንቸል ትናንሾቹ ደግሞ እንደ ዝሆን ገዝፈው የሚታዮት።

ሌላው በብሄር የሚሳደደውና የሚገለው ትንሹ የአደሬ ብሄር ሳይሆን ምናልባትም በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የአማራ ብሄር ነው። በመጨረሻም የመንግስቱ ግዜ ህዝብ ቆጠራ አማራው 29% ሲሆን የኦሮሞ ብሄር ደግሞ 32% ነበር። ህወሀት ከመጣ ቦሀላ ደግሞ የብሄር ፓለቲከኞች ቋንቋቸውን ያልተናገረውን አይቀበሉም። አግላዮች ብቻ ሳይሆን አሳዳጅም ስለሆኑ ከየ ብሄሩ በቋንቋው የተባረረው ሁሉ ዛሬ አማራ ሆንዋል። ይሄም ይቅርና ሁለተኛ ነው ብለን እንውሰድ። ሁለተኛ ማለት ከአማራ ያነሱ 84 ብሄረሰቦች አሉ ማለት ነው። እነዚህ 84 ብሄሮች እንደ አማራው አልታረዱም አልተቀጠቀጡም። ታድያ በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጤ፣ ወራቤ ወይንም ሌሎች ከመቶ ሺ ህዝብ በታች ያላቸው ብሄሮች ሳይደፈሩ ለምን ትልቁ ብሄር ለጥቃት ተጋለጠ ካልን፣ ይህም ከላይ ያልነው የስነልቦና ሰለባ ነው። ይህ ማለት ህዝቡ አቅሙን ባለማውቅቁ ለራሱ መብተ ነጻ አውጪ ጠባቂ በመሆኑ ነው።

ሌላው የአዲስ አበባ ህዝብ ነው። እስከ 7 ሚሊዮን ይደርሳል ይባላል። እንደው አሳንሰን 5 ሚሊዮን ህዝብ አለ ብንል እንዴት ከገጠር የመጡ ሰዎች ጢቢ ጢቤ ይጫወቱበታል። የቀበሌህ ሊቀመንበር ነኝ፣ ቤትህ መፍረስ አለበት፣ ግብር መክፈል ያለብህ ይህ ነው፣ ለልማት ትነሳለህ፣ በእርግጥ ለኮንዴሚኒዬም ከፍለሀል ግን ያንተ ቤት ለሌላ ተሰጥቷል፣ ዕህል አይገባም፣ ዳቦ 10 ብር ትገዛለህ ሲሉት ዝም ይላል። ምን ስለሆንክ ነው መሀል አራት ኪሎ እንደ ወጥ በሰባት ሚሊዮን ህዝብ መሀል ተቀምጠህ ከብቤሀለሁ የሚለው። ማነው ከባቢው ማንስ ነው ተከባቢው? የአዲስ አበባ ህዝብ ነው ካላረፍክ እኔው ከብቤ አንጠልጥዮ አወጣሀለሁ ማለት ያለበት። ይሁንና መሀል እንደ ወጥ የተቀመጠው በተፈጠረው false consciousness ከዛም manufacture of consent’ ሰለባ ነው። እያንዳንዱ ባለ ስልጣን በህዝብ መሀል በሶስት ታጣቂ በሚጠበቅ ቤት ነው የሚኖረው። በመሀላችን በመኖራቸው መፍራስ ሲገባቸው እነሱ በመቶ ሺህ የሚቆጠረውን ሰፈርተኛ በሶስት ጠባቂ ያስፈራሩታል። ይህ ነው የህሊና ሰለባ።

ሌላው ሀገር የዳቦ ዋጋ በ10 ሳንቲም ጨመረ የተባለ ቀን መንገድ ወጥቶ መንግስት ያባርራል። ለምን የአዲስ አበባ ህዝብ ጥቂት የገጠር ልጆች መቀለጃ ሆንን ካልን የአዲስ አበባ ነዋሪ ለሌሎች እንጂ ለራሱ መብት መታገል የሱ ተግባር አይመስለውም። ነጻ አውጪ ጠባቂ እንዲሆን ተደርጎ ተሰልባል።

ጭራሽ 7 ሚሊዮንን ህዝብ በ2 ሺ ሰው በማይሞላ ካድሬ ተኝቶ ሲያድር ሰባት ሚልዮን ደግሞ በፍርሀት ሲገላበጥ ያድራል። ሽመልስ የሸገር ከተማ ፈጥሬ አንቅሀለሁ ይላሉ። የጀርመን ሁለት ሚሊዮን ጦር ሌኒን ግራድን ከቦ አላንበረከከውም። ከና ቤት ተገንብቶንስፕው መጥቶ ሸገር ከባቢን ይሆናል ብለው የሚያስቡ ባላገሮችና መሀይማን ናቸው። የአዲስ አበባ ህዝብ 7 ሚሊዮን መሆንህ ሲገባህ ደሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ድርቀት በገደለው ነበር ትላልህ። አንድ ነገር ኮሽ ቢል ግር ብዬ መጥቼ እንደ ዶሮ ነው የምገነጣጥልህ በል። 7 ሚሊዮን ህዝብ ከአዚሙ ሲነቃ ማን ከባቢ ማን ተከባቢ እንደሚሆን ይታያል። ስለዚህ ጫካ ግባ ተኩስ ክፍት አይደለም የምን ይህ በቤትህ በቀዮህ በሰፈርህ ወንድ ሁን ነው። እስቲ ከነገ ጀምረህ እኔ ጨቋኜኝ በምን እያገዝኩህ ነው ብለህ ጠይቅና መገረፊያህን ልምድ አታቀብል። ሞት አይቀር ምንድነው እንዲህ መፍራት።

ስለዚህ የህዝብ ትግል የሚከተሉትን ሲረዳ ነጻ ይወጣል።

1 ነጻ አውጪ መጠበቅ አቁም፣ እራስህን ነጻ አውጣ።

ህዝቡ አቅሙ ከራሱ አልፎ ለሌላ የሚተርፍ ሆኖ ሳለ “hነጻ አውጪና ነጻ ወጪ” የሚል ትርክት እንዲቀበል በመደረጉ ምክንያት ህዝቡ የራሱን ችግር ፈቺ ሳይሆን ከሌላ መፍትሄ ጠባቂ እንዲሆን ተገደደ። ለሀምሳ አመታት ይሄው የኢዲዩ፣ የኢህአፓ፣ የከፋኝ፣ የጎሹ ወልዴ፣ የመድህን ጦር፣ የአርበኞች ግንባር፣ ግንቦት 7 ወዘተ ነጻ ያወጣናል ብሎ እጁን አጣጥፎ እንዲጠብቅና አንባገነኖች መጫወቻ እንዲሆን ተደረገ።

አንድ መቶ ሀያ ወታደሮች ሰላሳና አርባ ሚሊዮን እጁን አጣጥፎ የቆመውን ህዝብ ጋለቡት። 65 ሚሊዮን ህዝብ ሆኖ ሳለ አይሮፕላን ተሳፍረው፣ ፎቅ አይተው፣ በቅጡ ጫማ እንኳን ተጫምተው የማያውቁ ገበሬዋች መጥተው ሲጋልቡት ገለል በሉ ከማለት ይልቅ ኮ/ል ጎሹ፤ ከዛም ግንቦት ሰባት ነጻ ያወጣኛል ብሎ ህዝቡ በእጁና ጭንቅላቱ ላይ ቁጭ ብሎ ጠባቂ ሆነ። በመጨረሻ ያ ይፈራ የነበረው ስርአት ልጆች ድንጋይ ኮልኩለው ታንኩን፣ባንኩን፣ ደህንነቱን ጥሎ ወደ መቀሌ እንዲሸሽ አደረጉት። ለዚህ ነው ሰው በአንባገነን የሚገዛው ሲፈቅድ ብቻ ነው የምንለው። ሰው በቃኝ ሲል አምባገነን እንዴ ጤዛ በራሱ ይጠፋል።

ይህ ደግሞ እየተደገመ ነው። ወለጋ የሚኖሩ አማሮች ሰፈራቸው እየተከበበ ተሰልፈው አንገታቸው ይቆረጥ ነበር። ዘመዶቻቸው በዶዘር እየቀበሩ እባክህ አብይ አህመድ አድነን ብለው ለምነው ነበር። በመጨረሻው ነጻ የሚያወጣቸው እንደማይኖር ሲያውቁ ዱላቸውን መጥረቢያቸው እና አሮጌ ጠመንጃቸውን ይዘው ኦነግ ሸኔንና ልዩ ሀይሉን መግጠም ሲገቡ እርዱ ቆመ።የሰው ልጅ ቁርጡን ሲያውቅ በመጥረቢያው እየጨረገድ ራሱን አስከበረ። ዛሬ ይዞ ይሞታል እንጂ እየተማጸነ አይታረድም። በአርሲም በባሌም በሀረርም በሻሸመኔም በአርባ ጉጉም ይሄንን ውነታ ሲረዳ እራሱን ያድናል ይከበራል። አንዱን ይዞ ለመሞት የተዘጋጀን ፈሪ አይደፍረውም። ስለዚህ ደላህን መጥረቢያህን ጠመንጃህን ይዘህ እንደ እሸቴ ይታገሱ ወንድ ሁን። አንተ ታረድክ ብሎ የሚደርስልህ የልም። ተነስ ፈርተህ አትሙት። መንግስት የለም ፓሊስ የለም ፍትህ የለም ለኔ መኖር እኔ ብቻ ነኝ ብለህ አስብ ተዘጋጅ።

በወለጋ አላማ የሌለው መንጋ የሰው ሰንጋ አርጄ እበላለሁ ብሎ ሲመጣ የጥይት ሀሩር በጆሮው ሲጮህ ድርሽ ማለት አቆመ። የአዳነች አቤቤ ወደድክም ጠላህም የኦሮሚያን ባንዲራ ትዘምራለህ ባንዲራ ትሰቅላለህ ብላ መጣች። እናቶችና ተማሪዎች በአምስት ትምህርት ቤት ግልብጥ ብሎ ሲወጡ መዘዙ ትልቅ እንደሆነ ስለገባት ወደ ምሽጓ ተመለሰች። አብይ አህመድም ወደድክም ጠላህም “ሸሌ አለ ውስኪ አለ ጫት አለ የሚል የኦሮሞ ሲኖድ ያሳልምሀል” ብሎ ደነፋ። ሳምንት ሳይሞላው የጭንቅ ቀን ሲመጣ ይቀርታ ጠይቆ ወደ ምሽጉ አሸገሸገ። የአጣዮና በአውራጎዳና ህዝብ ብዙ ግዜ ተዘርፋል፣ ተቃጥሏል በመጨረሻ ግን አበዛችሁት ብሎ በኦነግ ሸኔና በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጆሮ ላይ ጥይት ሲያጮህበት ደብዛው ጠፋ። አሁንም አማራ ወደድክም ጠላህም ትጥቅህን ፈትተር ተሰልፈህ ትታረዳለህ ሲል ናና ሞክረኝ ሲል በቀን ሁለት ግዜ መግለጫ መለማመጫ ማታለያ ይለፈልፋል። ነገ ደግሞ ሰራዊቱን አፍርሼ ኦሮምያን እመሰርታለሁ ሲል የኢትዮጵያ ጦር ያለ ኢትዮጵያ ጦሩ አንደማይኖር ሲረዳ ጠመንጃውን አዙሮ እስቲ ሞክረው ይለዋል።

ይህ ነው ነጻነት ማለት የመጀመሪያው ነጻነት ከውስጥ ነው የሚወጣው። ስለዚህ የኔ ነጻ አውጪ እራሲ ነኝ ብለን የራሳችንን ነጻነት ስናውጅ ነው ነጻ መንግስት የሚኖረን።

ይህ ነጻውጪን መጠበው ስናቆም ከራሳችን ተርፈን ሌሎችን ነጻ እናወጣለን።

ያለኛ ድጋፍና ፈቃድ በራሱ የሚቆም አንባገነን የለም። እኛኑ ወታደር፣ ፌዴራል፣ ልዮ ሀይል፣ ሚሊሽያ፣ የእስር ቤት ዘበኛ፣ አቃቤ ህግ፣ ዳኛ፣ ጋዜጠና ሰላይ አድርጎ የሚረግጠን። ስለዚህ እራሱን ነጻ ያወጣ ሰው ለማንም የጭቆና መሳሪያ አይሆንም፣ የሀገሩን ዜጋ የሀይላንድ ኮዳ እያንጠለጠለ አይገርፍም፣ አይገልም።

2 አቅምን ያለማወቅ የስነልቦና ቀውስ

ሁለተኛው ችግር የኢትዮጵያ ህዝብ አቅሙን ያለማወቅ የስነልቦና ቀውስ ነው። ለምሳሌ ዛሬ የኢትዮጵያን 120 ሚሊዮን ነው። ዛሬ ህዝብን በወለጋ የሚደረገውን ግድያ ትደግፈለህ ወይ ብለን ብንጠይቅ እርግጠኛ ነኝ ከ 120 ሚሊዮን ውስጥ 119 ሚሊዮኑ አልደግፍም፣ ትክክል አይደለም የሚል ነው። ይሁንና ጥቂት የታጠቁ ሀይሎች ሲያርዱ 119 ሚሊዮኑ ምን አቅም አለኝ በሚል የስነልቦና ቀውስ ተሰልፎ ይታረዳል። ስለዚህ ነጻ መውጣት ያለብን ከተጫነብን የስነልቦና አዚም እንጂ ከመንግስት አይደለም። ነጻ አይምሮ ባርነትን አይሸከምምና።

ነጻነት የሚጀምረው ለኔ፣ ለልጄ፣ ለሰፈሬ፣ ለከተማዮ፣ ለሀገሬ ከኔ የተሻለ ምንም ሀይል አይመጣም ስለዚህ የሚስማማኝም ስደግፋለሁ፣ በማልስማማበት ሀሳብ ደግሞ አላጨበጭብም ብሎ ሲወስን ነው። ይህንን የሚል ግለሰብ ትላንት ህወሀት ከእረኝነት ሰብስቦ አሰልጥኖ ሱፍ አልብሶ የለቀቃቸው የብዴንና የኦፒዲኦ ካድሬዋች እየገረፈ ማሰልጠን ይችላል። የኢትዮጵያ ህዝብ ከነዚህ መሀይሞች በምንም አያንስም ነበር።

የነሱ ጥንካሪው የኛ የስነልቦና መዛባት ነው። ስለዚህ ለካድሬ፣ ለብልጽና እበላ ነኝ ባይ ፊት መንሳት ስንጀምር አብሬ እባላለሁ ብሎ የተሰባሰበው ጥሎ መውጣትና ከህዝብ ጋር ማበር ይጀምራል።

አማራ ክልል አዚሙ ተነስቶለታል። ገበሬው ታጥቆ መንደሩን ይጠብቃል፣ ጉራጌውን፣ ጋሞውም፣ ሀድያውም፣ ኦርቶዶክሱም፣ በየከተማው የተበተነውም አዲስ አበቤውም ተደራጅቶ እንደ ፋኖው በመንደሬ መጥተህ አትገለኝም ቤቴን አታፈርስም ሲል አንባገነን ድራሹ ይጠፋል። ያሁኑ ትግል የጉንዳን የምስጥ ነው የተባለው ለዚህ ነው። ሁሉም የአቅሙን መቆንጠር አለበት።

3 እውቅና በመስጠት

መንግስት የሚቆመው ህዝብ መንግስት ነው ብሎ እውቅና እስከሰጠው ድረስ ብቻ ነው። ህዝብ እውቅና መስጠት ባቆመበት ማግስት አንባገነን መንግስት ይፈርሳል። ታድያ ለምን የአለም ህዝብ ሁሉ በጭቆና ውስጥ ይማቅቃል ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። መልሱ ህዝብ ስላማያስብና ነጻ አውጪ ጠባቁ ስለሚደረግ ነው። እስቲ በዝርዝር እንየው።

ብዙ ሰው ባለማወቅ መንግስት ህጋዊ ነው፣ መንግስት ባይኖር ምን እሆናለሁ ብሎ ለመንግስት እውቅና በመስጠትና ይታዘዛል።
በእንግሊዘና legitimacy መስጠት ይሉታል። ህዝብ የማያውቀውና እንዲገነዘበው የማይፈለገው ነገር መንግስት ህዝብ እውቅና የነፈገው ቀን ይወድቃል። ይህንን ግን ማንም ህዝብ እንዲረዳ አይፈለግም። አንድ የቻይና ተረት አለ። አንድ የቻይና ሽማግሌ ዝንጀሮዋችን እየያዘ ክልጅነታቸው ጀምሮ በፍግርግር ብረት ውስጥ ያኖራቸውና ጥዋት ጥዋት ወደ ጫካ ይለቃቸዋል። ዝንጀሮዎቹ አባቶቻቸው በጫካ ውስጥ በነጻነት ከዛፍ እዛፍ ይዘሉ ይኖሩ እንደነበር ረስተዋል።

የዝንጀሮዎቹ ተግባ የሚበሉ ፍራፍሬዋች ክየዛፍ ላይ ለቅመው ከጌታቸው ማምጣት ነው። ለራሱ ከፍሬው ላይ የቀመሰ ወይንም በደንብ ያልለቀመውን ዝንጀሮ ገበሬው ይገርፈዋል። ስለዚህ ከዚህ ለማምለጥ ሁሉም ዝንጀሮዎች ጠንክረው ያለ እረፍት ወደ አፋቸው አንድ ነገር ሳያስገቡ ለቅመው ይመጣሉ። ከዛ ከራሱ የተረፈውን አካፍላቸውና ወደ መኝታቸው ይከታቸዋል።

እነሱ ይራቡ እንጂ እሱ ሳይጠግብ አይተኛም። አንድ ቀን አንድ ወጣት ዝንጀሮ አይምሮውን ማሰራት ይጀምራል። ጉዳይ እየከነከነው አንድ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህንን ጫካ የተከለው የኛ ጌታ ነው ወይ ብሎ ይጠይቃል? ከዛ አንዱ ሽማግሌ ጫካውማ በተፈጥሮ የበቀለ ነው ይሉታል። ከዛ ትንሽ ይቆይና ታድያ ከዚህ ጫካ ውስጥ ፍራፍሬ ለመልቀም ከሱ ፈቃድ ያስፈልጋል ወይ ብሎ ደግሞ ይጠይቃል? የዛን ሰአት አይናቸው ይከፈታል። የተጫነው አዚም false consciousness ይገደፋል። ሁሉም ዝንጀሮ የለቀሙትን እየበሉ ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ በነጻነት ኖሩ። ስራ የማይወደውም ብልጥ ሰውዮ የሚበላው አጥቶ ሞተ ይላሉ የቻይናዎች።

የአንባገነኖች፣ የሁራ ታሪክ አንዲሁ ነው። እንደ ዝንጀሮዋቹ አንባገነኖች በህዝብ የሚገርፉት እራስህ ቆርጠህ አምጣ በሚሉት አርጩሜ ነው። አርጩሜውም እራሱ መርቆ በሚሰጠው ልጁ ነው። ልጁን ወታደር ባለ ቀይ ኮፍያ የክብር ዘበኛ አድርጎ በመስጠት፣ ፌዴራል ፓሊስ፣ ሚሊሽያ፣ ዳኛ፣ አቃቤ ህዝብ አድርጎ በማቅረብ ነው። ይህ ባለ ቀይ ኮፍያ ወለጋ ጎጃም ወሎ አዲስ አበባ ያለችውን እናቱን ይገርማል እህቱን አብይን ለማስደሰት ይደፍራል። እሱ የሀይል ምንጭ መሆኑን ስለማያውቅ ባርነት ያስደስተዋል። በአሜሪካ የባሪያ አሳዳሪ ስርአት እንድ ነጭ ሺ ባርያ ይነዳል። የሚለግም ባርያ ሲያይ አንዱን ወጠምሻ ባርያ ይልክና አንቆ አምጥቶንእሱ ፊት እንዲገርፈው ያደርጋል። የነ ጀኔራል አበባው የነ ዳንኤል ክብረት ደስታ ይህ ነው። እናታቸውን ደፍረው ይምፕጡና ከአብይ መሬት ይለምናሉ። መሬቱም ሀገሩም የነሱን መሆኑን አይረዱም። ህዝብ መንግስት ህጋዊ ነው legitimate ነው በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ይሄንን ያመጣል።

ለፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር

ማታገልና መምራት ማለት ይህንን ለህዝብ አቅሙን ማሳየትና ተሳፋሪ ማድረግ ነው። መምራት ማለት እራስህ የምትገረፍበትን አርጪሜ አታቀብል፣ አንተ ላይ የሚተኩስ ልጅህን ምከር፣ አቃቤ ህግ ሆኖ የተሾመው ልጅህ በሀሰት እንሳይከስ፣ ዳኛው ልጅህ በሀሰት እንዳይፈርድ የመጨቆኛ መሳሪያ እንዳይሆን መምከር በቂ ነው።

አሁን በአማራ ክልል ብፕአብዛኛው ይሄንን እያደረገ ነው። ሌሎች ክልሎች ይሄንን ያደረጉ ቀን አንባገነንነት ነገ ጥዋት ይበናል።
ወደፊትም አንባገነን ለመሆን የሚመኝ በዚህ ምድር አይበቅልም። ህዝብ ሀይል እንዳለው ይረዳል።

መደምደሚያ

የኢትዮጵያ ህዝን በነጻነትና በፍትሀዊ እና በዲሞክራሲያዊ ስራት መኖር ከፈለገ እንደ ጉንዳንና እንደ ምስጥ ሁሉም የአቅሙን መቆንጠት አለበት። አምስት ትልቅ ግንድን በልቶ ይጨርሳል። ትልቅ መጋዝ መክተፊያ መፍጫ ይምጣልኝ አይልም። ሁሉም ባለችው የአፍ ይቆነጥራል። የብዙ ቁጫጭ ድምር ውጤት ዝሆኑን አጥንቱ እስኪቀር ቅርጥም አድርገው ይበሉታል። ትልቅ ግንድ ወድቆ ያገኙ ምስጦች የእንጨት መሰንጠቂያ፣ መጋዝ፣ መጥረቢያ ይቅረብልን፣ ዶዘር መጥቶ ያንከባልል አይሉም። ሁሉም የሚችለውን ታክል ግንዱን ይቆረጥማል። የዚህ ድምር ውጤት ግንዱ በአጭር ግዜ ውስጥ አፈርነት ይሆናል።

የህብረተሰብም እርምጃ በማመረርና በማለቃቀስ ሳይሆን ሁሉም የሚችለውን ያህል በመቆንጠጥ ነው። አላጨበጨብክም ብሎ የተከሰሰ ዜጋ እስካሁን አላየንም። አልደገፍከኝም ብሎ የታሰረ ሰው የለም። ሁሉም ወደ ባለስልጣን ተጠግቶ ህዝብን ከመግረፍ፣ አገልግሎት መከልከል፣ ማመናጨቅ፣ መዝረፍን ቢተው መንግስት የሚባለው ነገር ከዚህ ውጪ የለም።ዛሬ ይጀምራል አበባው ውስኪ ካልከፈልኩ የሚለው የአማራ ባለሀብት ጀነራሉንም ከስህተት ያድነዋል የሰበሰበውንም መሬት ሳይሸጥና ሳይበላ አይሜትን። ስለዚህ አቁሙ። ማፈርያ አትሁኑ። መንግስት ምናባዊ ነው። ገራፊው ገዳዮ ከኛው በውሰት የተሰጠ ነው። አለመገረፍ ከፈለግን ያዋስነውን ገራፊ መልሰን መቀበል ነው። ስለዚህ አባቶች ያዋሳችሁትን ገራፊ ልጆች ተረከቡ፣ ጎረቤት እየ ገረፈ እበላለሁ የሚለውን አግለው። ልጁን የምታስተምር የምታርም የምታንጽ አንተ ነሕ። ተወው እርሳው። ራሱን ይቻል። የሚገሉ የሚያስሩትን በእድር በቤተሰብ አስመክር።

የሰላማዊ ትግል መሳሪያዎች

1ኛ፣ መንግስት ህጋዊ አይደለም ማለት መብት ነው፣  ለመንግስት መታዘዝ የሞራል ግዴታ ነው የሚለውን እርግፍ አድርጎ መተው።

አንባገነን ስርአት የሚቆመው በዚህ የተሳሳተ የሞራል ግዴታ ላይ ነው። ለመንግስት እውቅና አለመስጠት ስርአትን ያከስማል።
አይወክለኝም አይቆምልኝም የኔን ጥቅም አያስከብርም ያልከውን ስርአት እውቅና አትስጠው (legitimacy ንሳው)

2 የህዝብ ሀይል አቅርቦት የመንግስት የጭቆና ግብአት ነው ጨቋኝ ስርአት የሰው ግብአት ይፈልጋል። ወታደር፣ ፖሊስ፣ ሚሊሽያ፣ ካድሬ፣ አቃቤ ህግ፣ ዳኛ፣ ገራፊ፣ ህግ አስከባሪ፣ ቢሮክራሲ፣ ጋዜጠኛ ቀረጥ ስብሳቢ፣ ጉቦ አቀባባይ፣ ወሬ እቅራቢ፣ አሽቃባጭ እጅ እስታጣቢ ወዘተ። እነዙህን ሁሉ አገልጋዮች ከቻይና አይደለም መንግስት በኮንቴነር የሚያስመጣቸው። ከህዝብ ነው። ስለዚህ ወንድምህን ገና ለገና ካድሬ መሬት ይሰጠኛል ብሎ ለሀጩን ሲያዝረከርክ እጅ ካላሳጠብኩ ሲል ገስጸው።

3 ጨቋኝ ስርአት የህዝብን እውቀት የፈልጋል። አትስጠው። አትስጥ አትምከር አንቀጽ ጠቅሰህ እትክሰስ በሀሰት አትፍረድ። በቃ ባይበላስ ቢቀር።

4 መንግስት ህዝብ ያለ ሀብት አይቆምም። ሀብትህን አትስጠው። አቆይ አዘግይ።

5 መቃወም፣ ስራ ማቆም መሰለፍ፣ አለመተባበር። እነዚህ የሰላማዊ ትግል መሳሪያዎች ናቸው። አማራ ክልል ተቀጣጥላል። አንተ አትጠብቅ። ነገ ጀምር።

6 ህዝብ ውሀ ቀጠነ ብሎ ለተቃውሞ መውጣት መብት ይሆናል። ስለዚህ ህዝብ እንደ ጉንዳን ዛሬ ማድረግ ያለበትን ነገር ዛሬ ማድረግ
ከጀመረ 20 ሺ የማይሞሉ የገዢ መደብ አባሎች 120 ሚሊዮን ህዝብን ማስገበር አይችሉም።

 


1 Gramsci, Antonio (1971) Selections from the Prison Notebooks of Antonio Gramsci, New York, International
Publishers.

i Edward S. Herman and Noam Chomsky in their book “Manufacturing Consent” The Political Economy of the Mass
Media” (1988).

ii Antonio Gramsci concept of cultural hegemony is related to his book “Prison Notebooks”. January 1, 1947
iii Gene Sharp, 2012, From Dictatorship to Democracy: A Guide to Nonviolent Resistance,