ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ታህሳስ 1, 2016

የአማራን ህዝብ ገድዬ፣ አፈናቅዬ፣ አስርቤ እና በድሮን ጨፍጭፌ እጨርሰዋለሁ ብሎ የተነሳው የአብይ አህመድ የኦሮሙማ
ሀይል በሁሉም መንገድ አማራን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት፣ ይህም ካልተሳካ ቁጥሩን ለመቀነስ በእጁ ያለውን መሳሪያ ሁሉ
እየተጠቀመ ነው።

ከኢትዮጵያ ህዝብ ለልማት የሚሰበሰበውን የታክስ ብር፣ በእርዳታ የሚመጣውን ዶላር፣ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጭምር ዶላር እየለመነ በሚያመጣው መሳሪያ በህዝብ ላይ እያዘነበ ነው። ይህንን መሳሪያ ተጠቅሞ በርካታ እናቶችን፣ ህጻናን፣ ቄሶችን፣ ሀጂዎችን፣ ገበሬዎችን ሳይቀሩ በገበያ፣ በመስጊድ፣ በገዳም፣ በቤተ ክርስቲያን እና በመኖሪያቸው እያሉ በድሮንስ እና በመድፍ እየጨፈጨፈ ነው።

ገበሬውን በራሱ የታክስ ወጪ የተገዛውን ማዳበሪያውን በመከልከል በረሀብ እንዲያልቅ እየሰራ ነው። በድርቅ የተጠቃው ደግሞ እንደ ቅጠል እንዲረግፍ ከወገንን ከውጪም የተገኘውን እርዳታ እንዳይደርሰው እያደረገ እየጨረሰው ነው። ገበሬው ያመረተውን ሽንኩርት ጎመንና ቲማቲም ወደ ከተማ ይዞ እንዳይሸጥ ኬላ አቁሞ ያመረተው አትክልትናንት ወተት በስብሶ እንዲጣል ፓሊሲ ቀርጾ እየሰራ ነው።

በከተማ ሰርቶ የሚበላውን ደግሞ በአማራነቱ ብቻ ከየቤቱ እያደነ ወደ ማጎርያ ጣብያ እየከተተ ነው። ይህ ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም። ጣልያንም ሰላሳ ሺ ሰው በፋስ እና በሳንጃ ጨፍጭፎ፣ የኮንሰንትሬሽን ካምፕ በሶማልያ በዲናኔ አቋቁሞ ለሀገሩ ሊቆረቆር ይችላል ያለውን ሁሉ ዲናኔ ማጎርያ ከቶ ነበር። ይሁንና ይሄንን ያየው ከተማ ተቀምጦ በጣልያን ወደ ዲናኔ አልተጫነም። የዛኑ ማታ ጠመንጃውን ወልውሎ፣ ከተማውን ለቆ በቅርብ ካሉ አርበኞቹ ጋር ነው የተቀላቀለው። የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የአብይና የሽመልስ አፈሳም ይህንን ማምጣት አለበት ይላል። ቆመህ እንደ በግ እየተጎተትክ አትታረድ ይላል።

አብይና ሽመልስ ነጋዴውና ባለሀብቱን በቀረጥና በጉቦ አራቁቶ ለማኝና ረሀብተኛ እያደረገ ነው። ሀብታሙ ግን ገና አልገባውም። አብይ እንደ ደራሽ ውሀ እያሳሳቀ ወደ ባህር ሳይጥለው ሀብቱን ለነጻነቱ ትግል ቢያውለው በሰላም የመኖር
መብቱን ያረጋግጣል።

ዛሬ ሙዝ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም ተሸክሞ እያዞረ ሸጠው የእለት እንጀራቸውን የሚያገኙ በዘር ጥላቻ በተለከፏ የነ አዳነች እቤቤና የፌዴራል ፓሊስ አዛዥ ደመላሽ ንብረቱ እየተቀማ በረሀብ እንዲሞት እየተደረገ ነው። ንብረትና ቤት ያለው ደግሞ በአዳነች አቤቤ፣ በአብይና በሽመልስ አብዲሳ ትዕዛዝ ቤቱ በዶዘር እየተናደ የዘር ማጥፋቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ሰሞኑን ጦርነት ይብቃ ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር የሄዱ የቀድሞው የኢዜማ አመራሮች፣ የእናት ፓርቲ፣ የኢህአፓ፣ የመኢአድ እና በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ ያሉዋቸውን ሁሉ በየ ቤቱና በየመስርያ ቤቱ እያደኑ እያሰሩ ይገኛሉ። ይህ ተግባር ከጣልያን ወረራ የካቲት 12 ጭፍጨፋ ጋር ይመሳስሰላል። ሰላማዊ ሆኖ ተለማምጦ መኖር እንደማይቻል የሚያሳይ የተነስ ደውል ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ደውል ተደውሏልና ተነስ። ከተማውን ለቀህ ውጣ፣ ሰልጥን ታጠቅና በወራት ውስጥ ወደ ሞቅ ቤትህ ትመለሳለህ።

የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የ50 አመቱ መጃጃል በመድገም “ይሄንን ተግባር ያወግዛል” የሚል መግለጫ አይሰጥም። ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ይህንን አረመናዊ ተግባር በማውገዝ ሳይሆን በጠመንጃው ነው የሚዋጋው። እንደ ጫጩት
እየተለቀሙ ከመወሰድ፣ በአዋሽ አርባና በኦሮምያ እስር ቤት ከመቀጥቀጥ ወደ ፋኖ ነጻ መሬቶች እየገባችሁ በህይወት የመኖር መብታችሁን አረጋግጡ ነው የሚለው።

አሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ አብይና ሽመልስ ያቀረቡለት ሁለት ምርጫ ብቻ ነው። ይሄውም እየታደኑ መጨረስ ያለበለዚያም ቆሞ ታግሎ በህይወት መኖርንና የሀገር ባለቤትነትን ማረጋገጥ ነው።

ጥሪ: ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለህበት ሁሉ

፩ኛ፣ ስርአቱን ሊጠቅም የሚችል ብላችሁ ከምታስቡት ተግባር ሁሉ ተቆጠብ። አትደግፍ፣ አታጨብጭብ፣ ለካድሬው፣ ለባለጊዜው አታሽቃብጡ፣ አይሆንም አልስማማም በሉ፣ የሱን ፕሮፓጋንዳ አታራባ፣ አዋጣ፣ ደግፍ ስትባል ይለፈኝ በሉ፣ ብሶትህን አታምቁ፣ ተናገሩ፣ ጉቦ አትስጡ፣ በራስህ ላይ ካድሬን አታደልብ። በቃ ባርያ መሆን በቅቶኛል በልና ስው ሁን። ተለማምጠህ ተልመጥምጠህ መኖርም አልተፈቀደልህም። ቁርጥህን እወቅ።

፪ኛ፣ ለስርአቱ በማገልገል ላይ ያሉ ወታደሮችን፣ ፓሊሶችን፣ አድማ በታኞችን፣ ልዩ ኃይሎች፣ አቃቤ ህጎችን፣ የእስር ቤት ዘበኞችን፣ የመንግስት ቀረጥ ሰብሳቢዎች፣ የመንግስት የፕሮፓጋንዳ ሰራተኞችን፣ የመንግስት አሽቃባጭ ነጋዴዎችን
የመጨረሻው ደውል ተደውሏልና እራሳቸውን የመጨቆኛ መሳሪያ መሆናቸውን አቁሙ ብላችሁ ምከሩ። በሚነሳው እሳት አብረው እንዳይነዱ ልጅህን፣ ወንድምህን፣ ዘመድህን፣ ጓደኛችን በቃችሁ በላቸው። እንበላለን ብላችሁ እንዳትበሉ ብለህ ምከር። የኢትዮጵያ ህዝብ በቅቶታል። ግልብጥ ብሎ የወጣ ቀን አርባ ጅራፍ ቁጭቱን አያበርድለትምንና የስርአቱ ወሬ አቀባብዬ፣ ጉቦ አቀባብዬ እበላለሁ ያለውን አሽከር በቃህ አብረህ እንዳትበላ በሉት።

፫ኛ አብይንና ሽመልስ የዘር ማጥፋት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል። ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ የሽመልስ አብዲሳ በጥላቻ ያበደ ሰራዊት አደራጅቷል፣ ሁሉንም የወታደራዊ መዋቅር የተቆጣጠሩ ጸረ እማራ የኦፒዲኦ መኮንኖች ታንኩን፣ ድሮኑን መድፏን በእጃቸው አስገብተዋል። በጫካ በጸረ አማራ ጥላቻና ያደራጁት የኦነግ ታጣቂ በየ ቁጥቋጦው ስር ሆኖ የሚል ትእዛዝ ይጠባበቃል። እነ አዳናች አቤቤ የሚያደራጁት ግማሽ ሚሊዮን አብዮት ጠባቂ ጣልያንን ለመመከት
እንዳይመስላችሁ። አንተን ለመፍጀትና ለማረድ ነው። ስለዚህ በወለጋ እንዳሉ ኢትዮጵያውያን እራስህን በየሰፈርህ አደራጅ፣ ዱላህን ዘነዘናህን ይዘህ ተሰባስበህ የራስህን፣ የሚስትህን፣ የልጅህን፣ ነፍስ ለማዳን ክጎረቤትህ፣ የሰፈርህን ሰው ተነጋገር። በሀሳብ የምትግባባ ጎረቤት ጋር በዚህ ቢመጡ በዚህ ቢያጠቁን ብለህ በየሰፈርህ ተደራጅ። የኢትዮጵያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ፓሊስ የሚባል የለም። ባምስት መቶ ካሪ ሜትር ቦታ ሀገሩንም ክብሩንም ሚስቶቻቸውን የሸጡ ጄኔራሎች ናቸው። ህሊና ቢኖራቸው ለሀገራቸው ለወገናቸው ከሆዳቸው በላይ ቢያስቡ ኖሮ ህጻናትና አሮጊቶች ሲታረዱ እኔ ቆሜ! ብለው ወለጋ ይገቡ ነበር። ስለዚህ የአዲስ አበባ ህዝብ ሲታረድ ጀነራሎቹ ዘራፍ ብለው መትረየሳቸውን በጂፕ ላይ ደግነው ወጥተው ከህዝብን ከመታረድ ያድናሉ ብለህ አታስብ ተስፋ ቁረጥ። ለዚህ ነው በሚስትህና በልጅህ ፊት እየተጠፈጠፍክ እያለቀስክ ከምትታረ ለልጅህን እናት ለሚስትህ ስትል አንድ ቀን ወንድ ለመሆን ተዘጋጅ። ይህንን የማያደርግ ልጁ እፊቱ ስትደፈር ሚስቱ ስትታረድ ያያል። ፋኖ በቅርብ አለ ይሁንና 120 ሚሊዮን ህዝብን የማዳን አቅም የለውም። ይልቁንም 120 ሚሊዮን ህዝብ ሆ ብሎ ዘነዘናውን ይዞ ከተነሳ እራሱን ያድናል፣ ሀገርንም ነጻ ያወጣል።

፬ኛ፣ በየ ከተማው ያለህ ወጣት ሙዝ ሼጬ፣ ሽንኩርት አዙሬ ያልፍልኛል ብልህ በየመንገዱ እየታፈስክ ከምትጠፈጠፍ ቆፍጠን በል። ወንድ ወንድ ሽተት። ከአዲስ አበባ 30 ኪሜትር ሳይርቅ ነጻ ምድር አለ። አትልፈስፈስ ውጣ፣ ሰልጥን፣ታጠቅ ነጻነትህንና በህይወት የመኖር መብትህን በክንድህ ብቻ ነው የምታረጋግጠው።

፭ኛ፣ ፓለቲከኛች፣ ምሁሩን፣ አስተማሪዎች፣ ጋዜጠኛች፣ ቢሮክራቶችና መሀበራዊ እንቂዎች በቃ በሉ። መለማመጥ፣ ማባበል፣ መምከር አልሰራም። በምክር፣ በጽሁፍ፣ በክርክር በሰላማዊ መንገድና አቤቱታ ለውጥ እንደማይመጣ እያየህ
ነው። ፈራ ተባ እያሉ ሰላም ይምጣ፣ ጦር ይብቃን ያሉ እስከ ቅርብ ጊዜ የስርአቱ ደጋፊ የነበሩ የኢዜማና የአብን አባሎች ሳይቀሩ እየታደኑ ወደ ዲናኔ ( አዋሽ አርባ) እየተወሰዱ ነውና ሙከራችሁ ከሽፏል። እናንተ ወደኛ ብትመጡ
ትጠቅሙናላችሁ። እንፈልጋችሀለን። ምንጃር፣ ቡልጋ፣ አረርቲ፣አሳግርት የግማሽ ቀን የእግር ጉዞ ነው። ከዛ ሆናችሁ በጽሁፋም በክርክሩም በማንቃቱም ልትሰሩ ትችላላችሁና በቃን ብላችሁ ትግሉን ተቀላቀሉ። ክርስቲያንና ከቧያለውን ያየ
የዚህን ስርአት ጭካኔና ዘር ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ለዚህ ነው ፋኖን በመቀላቀል እራሳችሁን ከባርነት ነጻ አውጡ የምንለው ። የኢትዮጵያ አርበኞች ካልዲስ ካፌ ተቀምጠው አይደለም ነጻ ሀገር ያስረከቡን። ስለዚህ ተለቅመህ፣ ተሰድበህ፣ ተዋርደህ፣ ተርበህና ተቀጥቅጠህ በአዋሽ አርባ ከምትሞት ካኪ ሱሪህንና የሚመች ጫማህን አድርገህ ና። ለሌላው አታስብ። ገበሬው ወፍራም እንጀራ በሽሮ ያበላሀል አትራብም፣ አትጠማም ወንዝ ወርደን ውሀ ቀድተን አፍልተን እናጠጣሀለን፣ በአካል ብቃት እናጎለብትሀለን። የሰውንና የነጻነትን ክብር ሊያዋርዱህና ሊሳለቁብህ የተነሱትን ታሳያቸዋለህ። ከዛ እንደ አባቶቻችን “አሉ ጎንበስ ጎንበስ አሉ በርከክ በርከክ አውሬ መስያቸው፣ ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው ትላቸዋለህ”

ውርደት በቃኝ፣ ባርነት በቃኝ በል። ተነስ ማንም ነጻ አያወጣህም። ነጻ የምታወጣው እራስህን ነውና። ለትግል የወጡ ወንድሞችህ እጃቸውን ዘርግተው ይጠብቁሀል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገሩንና በህይወት የመኖር መብቱን በክንዱ ያረጋግጣል!