ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት !!
ዛሬ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፋኖ በደቡብ (ኢትዮ ፋኖ) ተመስርቶ በይፋ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀሉ የአማራ ፋኖ በጎጃም ደስታ ይሰማዋል ። የፋኖ ትግል አማራን ህልው ከማድረግ አልፎ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዓት ወደ ፍፁም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊነት የሚቀዬር ዕውነተኛ የትግል መንገድ የሆነ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባት ሐገር እንድትሆን ያለመ፤ አሳዳጅ እና ተሳዳጅነትን፤ገዳይና ሟችነትን፤ አፈናቃይ እና ተፈናቃይነትን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር እስከወዲያኛው የሚያስወግድበት ነው። በመሆኑም የአማራ ህዝብ እያደረገው ያለውን […]