ጎጃም ዕዝ

የጎጃም ዕዝ ፋኖ አሁን ያለበት ቁመና እና ያጋጠማቸዉ እንቅፋቶችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፤

ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም!

የጎጃም ዕዝ ለበርካቶች የትግሉ ደጋፊዎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ኩራት የሚሆን ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። በተለያዩ አካባቢዎች የሰራናቸዉ ኦፕሬሽኖች እና ዘመቻዎች ሕዝብንና ሀገርን የሚያኮሩ፤ በታሪክ ማህደር ለቀጣይ ትዉልድ በደማቁ የሚፃፉ ድሎችን አስመዝግበናል። ከእነዚህ ጠንካራ እንቅስቃሴዎች በተቃራኒው የቆሙ አካላት የትግሉን መልካም ጅማሮ ለማበላሸት ወደፊትም የተሻለ ሥራ እንዳይሰራ ከጠላቶቻችን ባልተናነሰ መልኩ የእዙን ፈጣን ጉዞ ለማደናቀፍ የሚታትሩና ከመንገዳችን ላይ እንቅፋት እና መሰናክል በመጣል እንደቆመ ጋሬጣ እንጨት በፊት ለፊት እየቆሙ የሚያስቸግሩንም አልጠፉም።

የሕዝባችንን የሕልዉና ትግል ከዳር ለማድረስ ከጠላት ፊትለፊት በመሰለፍ በጥይት እርሳስ በየጢሻዉ፣ በየምሽጉ የተዋደቁትን እና የተሰዉትን ብርቅየ ታጋዮቻችንን በመዘንጋት ደማቸዉ ሳይደርቅ ስጋቸዉ ሳይሟሽሽ ዓይናቸዉ ሳይፈርጥ የሞቱለት ዓላማ እና የቆሰሉለትን፣ አካላቸዉን ያጎደሉለትን ትግል የካደ የባንዳነት ሥራዎችን በአንፃሩ እያየን ቢሆንም አሁን ካለንበት አቋማችንና ዓላማችን ሊያነቃንቀን የሚችል የዉስጥ ባንዳ እንደማይሳካለት አስረግጠን እንናገራለን።

የትግሉን መነሻና መዳረሻ በውል ያልተረዱ የትግሉ ማዕበል ያጠራቀማቸዉ ግብስባሶች ግራ በመጋባት አውቀውም ይሁን ሳያውቁ አራት ኪሎ የሚደርሰዉን ትግላችንን በ4ሜትር ለማስቀረት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከክህደት የበለጠ ትርጉም እንደማንሰጠው ሊገነዘቡ ይገባል።

እነዚህን ሁሉ የትግሉን መሰናክሎች እና ፈተናዎች ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት የትግሉ ደጋፊዎችም ከጠላት ጋር የምትጋፈጡ ጀግኖቻችንም እስካሁን ከመጣንባቸዉ ቆራጥነትና ጀግንነት በላይ ያለንን አቅም በሙሉ በመጠቀም ለማይቀረው ነፃነት ትግላችንን ወደፊት አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል።
እያደረግነዉ ባለነዉ የሕልውና ትግል ዉስጥ ምንም አይነት መስዋትነት ያልከፈሉና ትግሉን ከርቀት ሆነው ሲመለከቱ የነበሩ አንዳንድ አካላት የከፈልነዉን መስዋትነት የምንጓዝበትን የትግል ተራራ ሳያዩ ከዚህ በፊት በፖለቲካ ትግላቸዉ ደጋግመዉ የከሰሩና ያከሰሩን አሁን ደግሞ ተቀባይነት ያጡ ፖለቲከኞች በሕልዉና ትግሉ ዉስጥ ጣልቃ ለመግባት እና የትግሉ ፊትአዉራሪ ለመምሰል መሰሪ በሆነ የትግል ጠለፋ ሴራ ተጠምደዉ ሲያሴሩ ውለው እያደሩ ነው።

ሀቁንና እዉነታዉን ሕዝባችን የሚያዉቀዉ ቢሆንም አሳማኝ ያልሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር የማስመሰል ትግል በማካሄድ በበርካቶች ሕይወት የሚቀልድ የፓለቲካ መስመርን መርጠዉ በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመዉጣት አቀበትና ቁልቁለት የበዛበትን የትግላችንን ጉዞ ሳይደፍሩ ቅርብ ላይ ቁመዉ ወንበር የናፈቁ ድንኳን ሰባሪ ፖለቲከኞች ቀጣፊ ምላሳቸውን ታቅፈው ከመቅረት ዉጭ ሌላ ትርፍ እንደማያገኙ አስረግጠን መናገር እንፈልጋለን።

የጎጃም ዕዝ የተመሰረተበትን መሰረቱ በጠንካራ አለት ላይ የተገነባ በብዙዎች ፍላጎትና ምርጫ በእዉነተኛና ቆራጥ ታጋዮች ምሰሶ ያቋቋምነው የጋራ አሻራችን እንጅ የፖለቲካ ቁማርተኞች የሚቆምሩበት የጥቂቶች ቁማር ቤት እንዳልሆነ መሰመር አለበት። ጥቅማቸዉ የከሰረባቸው ዉሸታምና አስመሳይ ግለሰቦች በድርጅት ስም የግል ጥቅማቸዉን ሲያሳድዱና እራሳቸዉን ሲጠቅሙ የነበሩ ዛሬ ላይ በተፈጠረዉ የእዝ አደረጃጀት ከመደሰት ይልቅ የተከፉ፣ ከመኩራት ፋንታ የህፍረት ማቅ የለበሱ: በስንት መስዋትነት እና ድካም ያቋቋምነዉን የእዝ መሰረት ለማናጋትና አቅሙንና ተቀባይነቱን ለማሳጣት በደካማ የፓለቲካ ገመድ አንቀዉ ይዘዉ የገቢ ምንጭና የዶላር መሰብሰቢያ ከፍ ሲል ደግሞ የስልጣን መደራደሪያ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቀሴ በእጅጉ እንቃወማለን።

ይህን ስንናገር ሁሉም የፖለቲካ አደረጃጀቶችና ግለሰቦች እንዳልሆነ ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ፖለቲካ ከሌሎች ቀድሞ መረዳትና የሕዝብና የሀገርን መጭ ዘመን አስቦ ለእድገትና ለስልጣኔ ከሌሎች የተሻለ ሀሳብ ማፍለቅና ማመንጨት መሆኑን ብንረዳም፤ የእኛ ፖለቲከኞች ግለሰባዊ ፍላጎትን መሰረት አድርገዉ በመነሳት ለለዉጥና ለነፃነት የተነሳሳዉን ወጣት ከፊት ለፊት አድርገዉ በልፍስፍስ የትግል አቋማቸዉ ምክንያት የሰዉን ኃይልና የሕዝቡን ኢኮኖሚ ለግል ፍላጎታቸዉ ተጠቅመዉበት ያልፋሉ።

ከሕዝባቸዉ ጥቅም ይልቅ የእራሳቸዉን የግል ጥቅም ያስቀደመ የጥሎ ማለፍ ግብግብ መሆኑ በትግል መንገዳችን ዉስጥ ብዙ ትምህርት ወስደናል።

የአማራ ፋኖ ትግል የሕልዉና የነፃነት ትግል እንደሆነ ከተረዳን ነፍስ ያለዉ ሁሉም አማራ ለእራሱ ነፃነት የሚችለዉን አቅሙ የፈቀደዉን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል።
በአንፃራዊነት ካየነዉ ደግሞ የጎጃም እዝ በሚንቀሳቀስባቸዉ አካባቢዎች ተነግሮ እና ተዘርዝሮ የማያልቁ ለነገ ትዉልድ በታሪክ የሚፃፉ በርካታ ገድሎች እንደሕዝብ በጋራ ፈፅመናል።

አገዛዙን ከልብ የማይጠሉ መላሾ የለመዱ ታጋዮች ብቅ እልም እያሉ ቢያስቸግሩንም ወደኋላ ቢጎትቱንም ሞትን፣ መከራ፣ ስቃይና ፈተናችንን እየገፋ በመሄዱ በቁጣ እንደቀፎ ንብ ገንፍሎ የወጣዉን የሕዝባችንን ማእበል ፊትለፊት ሆነን መርተን አስክሬን ተራምደን፤ ደም ረግጠን፣ ቁስል አስረን፣ ቆስለን ሞተን ማሸነፍን ስናሳያቸዉ የተደበቁት ሁሉ ከተደበቁበት መዉጣት ችለዋል። ይኼን ተጋድሎ እንደጥሩ አጋጣሚነት መጠቀም ሲኖርባቸዉ ጎን ለጎን በመሄድ ቆራጡ ፋኖ አንድነት እንዳይኖረዉ በሴራ ትብታብ ሊጠልፉ ሲዳዱ ስናይ ግን አዝነናል።

በብልፅግና የፋሽስት አገዛዝ ማዕቀፍ የተሰበሰበዉ ዘራፊና ጨፍጫፊ ቡድን ከነበረበት የወረዳና የዞን መዋቅር እየሸሸ በአንድ ጉድጓድ ተከማችተዉ የቀራቸዉን የሕይወት ዘመን በጣር እና በጭንቀት ዉስጥ እያሳለፉ ይገኛሉ።

በጀግኖች የፋኖ ታጋዮቻችን የጥይት ባሩድ እየነደዱ የሚገኙ የአገዛዙ ካድሬዎች እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል እልህ የሕዝብን ሀብት በመዝረፍና ሥራ ላይ ተሰማርተዋል።

በተለይም በትልልቅ ከተሞች ላይ ያሉ ቦታዎችን በሊዝ እየቸረቸሩ ቤተሰቦቻቸዉን በቅንጦት የሚያኖር ገንዘብ እያከማቹ ይገኛሉ። በ2000 እና በ3000 ብር ደሞዝ የሚላላከዉ ተከታዩ ካድሬ ስሙን እየቀየረ በየዘመድ ቤቱ እራሱን ደብቋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነን የሚሉ የዐብይ ስልጣን ጠባቂ የራሱን እናትና አባት እህትና ወንድም እየገደለ የተሰጠዉን ጀነራል፣ ኮሎኔል፣ ሻለቃ፣ ማእረግ ደርድሮ በየከተማዉ ሴቶችን ሲደፍር ሕጻናትና ደካሞችን በከባድ መሣሪያ ሲጨፈጭፍ ቤተ-እምነቶችን ሲያወድም እና ሲያረክስ ይዉላል።

የአብይን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ግን ከፋኖ ድል ማግስት በለበሰዉ መለዮ ወደልመና መዉረዱ የማይቀር ሀቅ ነዉ። ይሄን በመረዳት በስደት ሀገር ሆናችሁ ከምታገኙት የእለት ጉርሳችሁ ቀንሳችሁ የናፈቃችሁን ነፃነት ለማየት ትግሉን የምትደግፉና የሕዝባችሁ ጉዳይ የሚያንገበግባችሁ ደጋፊዎቻችን ከዚህ በፊት ላደረጋችሁልን ድጋፍ ከልብ እያመሰገን ትግሉ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ያበረከታችሁት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን።

ሀገራችሁንና ሕዝባችሁን በልባችሁ ማኅተም አትማችሁ ዉቅያኖስና ባሕር አቋርጣችሁ የምትኖሩ በሙሉ የእኛ የአካል ክፋዮቻችን መሆናችሁን በምታደርጉት የማያቋርጥ ድጋፍ አረጋግጠናል።
ፋኖ በራሱ ትጥቅና ስንቅ የሚዋጋ የነፃነት ታጋይ መሆኑን ስለምትረዱ የሎጄስቲክና የፋይናንስ ምንጫችን የሚሸፈነዉ ከእናንተ እገዛ መሆኑን ለአፍታም እንዳትዘነጉ።
አሁን ካለንበት የትግል ጉዞ ወደቀጣይ መዳረሻና የመጨረሻዉ ግባችን ለምናደርገዉ ዘመቻ በሁሉም አቅማችሁ ከጎናችን በመሆን እንድትደግፉን በጥብቅ እንጠይቃለን ።

እኛ የእናንተ ልጆችና ወንድሞች በጀግኖች የአባቶቻችን በእነአፄ ቴዎድሮስ፣በእነአፄ ምንይልክ፣ በንጉስ ሚካኤል፣በንጉስ ተክለሃይማኖት ፣በአባኮስትር በላይዘለቀ እና በአሳምነዉ ፅጌ ምለን ህይወታችንን ለትግሉ አሳልፈን ሰጠናል።

እናንተን የሚያኮራና የአባቶቻችንን ታሪክ በእኛ ትዉልድ በደማችን ደግመን ለመጻፍ እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት ቆርጠን ተነስተናል። በጎራ ፓለቲካና በአካባቢ ስብስብ ዉስጥ ያለን ታጋዮች በነብዩ አሳምነዉ ፅጌ ቃል አንድ ሆነን የያዝነዉን ትግል ዳር ማድረስ እና አማራን ከአንገቱ ቀና እንዲል ማድረግ የሁላችንም ግዴታ ነው።

ትግሉ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚፈልግ መሆኑን በመረዳት ሁሉም ሕዝቡንና ሀገሩን የሚወድ አማራ ብሎም ኢትዮጵያዊ ከጎናችን ይቆም ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን።

የተከበራችሁ የአማራ ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች :-እንደሚታወቀዉ የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ላይ ያወጀዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል በእናንተ ሚና እየተፈፀመ መሆኑን በተግባር አይተናል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያላችሁን ሳትሰስቱ የሚገድለን አገዛዝ ስልጣን ለማትረፍ ያላደረጋችሁት አስተዋፅኦ የሌለ ቢሆንም በጦርነቱ ማግስት ግን በአማራነታችሁ ብቻ ተለይታችሁ በሀብትና ንብረታችሁ እንዳትጠቀሙና ሀገር እንዳታለሙ ሆን ተብሎ በእናንተ ላይ የተቀነባበረ ሴራ በማሴር ሀብት ንብረታችሁ እንዲወድምና ድርጅታችሁ እንዲከስር በመደረጉ በእጅጉ አሳዝኖናል።

በአማራ ባለሀብቶች ላይ ያነጣጠረዉ ማሳደድና ማዋከብ በሚደግፉት ድጋፍ ሳይሆን አማራ በመሆናቸዉ ብቻ እንደሆነ የገሀድ አለም ሚስጥር ሆኗል። አካዉንታችሁ የታገደዉ፤ ድርጅታችሁ የተዘጋዉ ፋኖን ስለደገፋችሁ ሳይሆን አማራ በመሆናችሁ እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀዉ ያገጠጠ እዉነታ ነዉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ከላይ የፋኖን ልብስ የለበሱ ዉስጣቸዉ ግን ብልፅግና የሆኑ ዘራፊ ቡድኖች ባለሀብቶች ላይ ያነጣጠረ እገታ እየፈፀመ መሆኑን የጎጃም እዝ ባገኘው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል።

ትግሉን ባለማገዛችሁ ህሊናችሁና ነገ ታሪክ የሚወቅሳችሁ ቢሆንም በፋኖ ስም እንድትዘረፉ እንድትታገቱ ግን ፈፅመን አንፈቅድም ።
ፋኖና ህዝብ አንድ መሆኑ እየታወቀ ፋኖን እና ህዝብን ለመነጣጠል የታቀደ ሴራ መሆኑን ህዝባችን እንዲያዉቀዉ እያሳሰብን የጎጃም ዕዝ በሚንቀሳቀስባቸዉ ቦታዎች በባህርዳር ዙሪያና በደብረ-ማርቆስ አካባቢ በዕገታ ስራ ላይ መንግስት ያሰማራቸዉ ግለሰቦችን በጎጃም ዕዝ ክትትል ካደረግን በኋላ እርምጃ የወሰድን እና በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉ ሲሆን የምርመራ ሂደቱ ሲያልቅ ዝርዝር መረጃ የምንሰጥበት ይሆናል።

ረዥም ኔትወርክ ዘርግተዉ በዕዙ ስም ብር ያስላኩ ማንነታቸዉን ስናጣራ ‘ህዝባዊ ሀይል’ ጋር እንሰራለን ብለዉ የሚናገሩ የግለሰቦች እጅም እንዳለበት የስልክና የድምፅ ሪከርድ አረጋግጠናል ።

የግለሰቦች ማንነት ዝርዝር መረጃ እስክናወጣ ድረስ ማንኛዉም ነጋዴና ባለሀብት ከእነዚህ ግለሰቦች እንዲጠነቀቅና ችግር ካጋጠመዉ ለዕዙ እንዲያሳዉቅ በጥብቅ እናሳስባለን ።

ሰሞኑን በጎጃም ዕዝ ስም የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማዋቀራችንን እየገለፅን በጋዜጠኛ ተስፋየ ወልደስላሴ የሚመራ የጋራ ግብረ ሀይል የጎጃም ዕዝ እዉቅና እየሰጠ ለሚያደርጉት የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ ሁሉም አቅሙ የፈደቀዉን እንዲያግዛቸዉ በምሽግ በሚዋደቁት ታጋዮች ስም እንጠይቃለን።

በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ ስያሜ የምትንቀሳቀሱ የአማራ ማህበራት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዉ በጊዜያዊነት ለአንድ ጊዜ ወይም ለኢመርጀንሲ ፈንድ ብቻ የተቋቋመ መሆኑን እንድትረዱና ድጋፍ እንድታደርጉላቸዉ እናሳዉቃለን።

ድጋፍ የሚደረግባቸዉ ዋና ምክንያት አማራ እንደህዝብ ከመጥፋት አደጋ እራሱንና ትዉልዱን ለማዉጣት ከጨፍጫፊዉ የፋሽስት መንግስት ጋር እያደረገዉ ባለዉ የህልዉና ጦርነት ምክንያት ለወደሙ ት/ቤትና የጤና ተቋማት ግንባታ እንዲሁም በመድሀኒት እጦት ለሚሰቃዩ ወላድ እናቶችና አቅመ ደካሞች ባሸባሪ መንግስት የድሮን የሞርታር የ BM ጥቃቶች ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናትና ሀብት ንብረታቸዉ ለወደመባቸዉ አዛዉንቶች ፣ሰብላቸዉ ለተቃጠለባቸዉ አርሶ አደሮች የሚዉል ድጋፍ መሆኑን አስረግጠን እንገልፃለን።
የአማራ ሕዝብ አሁን ላለበት የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሰብአዊ ምስቅልቅል ኃላፊነቱን የሚወስደዉ እራሱን እንደመንግስት የሚጠራዉ አሸባሪዉ ፋሽስታዊ አገዛዝ ቢሆንም፤ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ጉዳዩን በትኩረት አይተዉ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያቀርቡ የጎጃም እዝ ጥሪ ያቀርባል።

በሀገር ውስጥም ከሀገር ዉጭም የምትኖሩ የትግሉ ደጋፊዎች የጎጃም እዝ አሁን ስላለበት ቁመና ምን እንዲሚመስል ማወቅ የምትፈልጉ በሙሉ የጎጃም እዝ በጎጃም ምድር ሁሉንም የጦር መሣሪያ አንግቦ ጫካ የገባዉን እና በሀሳብም፣ በማቴሪያልም፣ በፋይናንስም ከትግሉ ጋር የተሰለፈዉን የነፃነት ታጋይ አጠቃሎ በመያዝ እየታገለ ሥራዎች በተግባር እየተገለጡ መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።
የፓለቲካ አደረጃጀትን በተመለከተ እንደ አማራ በሚፈጠር አማራዊ አደረጃጀት የሚካተት ሲሆን፤ አሁን ላይ እንወክለዋለን የሚሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች የዉሸት ፓለቲካ አራማጅ ስለሆኑ በእነሱ ለመመራት ፍቃደኛ እንደማይሆን አስረግጠን እንናገራለን። በፎቶ ሾፕ ፓለቲካ ትግሉን ለመደለል የሚደረጉ ጥረቶች ፀረ-ሕዝብ መሆናቸዉን እንድትረዱ እንፈልጋለን “ቢተባበሱ እንደቅቤ ቅል መተኮስና መግደል ለየቅል” እንዳለዉ ፎካሪዉ ዉጊያና ፎቶ ልዩነት እንዳለዉ የሚጠፋዉ ሕዝብ የለም እዙ የት እንዳለ የጠፋችሁ ትግሉን የምትደግፉ በሙሉ በጎጃም ተራራዎችና ምሽጎች ብቅ በሉ።

በላብ ወዝቶ ፀጉሩ ጎፍሮ፣ አካሉ ደርቶ ከአስፈሪ የፊት ገፅታና ከታጠቃቸዉ የጦር መሳሪያዎች ከማረካቸዉ ሞርተር ዙ 23 ዲሽቃ ብሬን ስናይፐር ክላሽንኮቭ ሽጉጥ ጋር ታገኙታላችሁ። በተለያየ አለም ሁናችሁ በቲክቶክ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ወ.ዘ.ተ የጎጃም እዝ በመደገፍ ላይ ላላችሁ የቴክኖሎጅዉ አለም ፋኖዎቻችን ከልብ እያመሰገን እስከነፃነት ድረስ እንድትበረቱ እንጠይቃለን።

በሌላ መረጃ የጎጃም ዕዝ ፋኖን ማግኘት ከፈለጋችሁ ብርሀኑ ጁላን እና የላካቸዉን ተላላኪዎቹን ደዉላችሁ ብጠይቋቸው የት እንዳለን በደንብ ይነግሯችኋል። ከዓባይ በርሃ እስከ ባሕርዳር ከመተከል እስከ ቡሬ ወለጋ ያሉት እነማን ናቸዉ? ብላችሁ ብትጠይቁ እንደ ሲጃራ የባሩድን ጭስ እየሳብን የመሣሪያችንን አፈሙዝ በጠላት ደም እየቀባን ሲርበን ለምነን እየበላን ሲጠማን ላባችንን እየጠጣን የብልፅግናን የፋሽስት አገዛዙን ሰራዊት እየገረፍነዉ እንገኛለን።

ፎቶ ከፈለጋችሁ ለፎቶ የሚሆን መልክ ስናገኝ እንልካለን ። በየአዉደ ዉጊያዉ የተሰዉቱን ጓዶቻችንን አደራ ተሸክመን የአባቶቻችንን ወኔ ሰንቀን፣ የሕዝባችንን መከራና አገዛዙ የፈጸመብንን ግፍ አስበን ነገ ላይ በምናገኘዉ ነፃነት ያለምንም ጥቅማ ጥቅም ዛፉን ቤታችን፣ ወንዙን ካፌያችን፣ አፈሩን ምግባችን፣ ድንጋዩን ትራሳችን እና ትጥቃችንን ሱፋችን በማድረግ በአኩሪ ተጋድሎ ላይ መሆናችንን ስንገልጽ በልበ-ሙሉነት ና ኩራት ነው።

ጨፍጫፊዉ እና ተስፋፊው የኦሮሙማ አገዛዝ መሬት ላይ ባሉ ሀቀኛ ታጋዮች ይወድቃል!!

እዉነት የያዘ እና የተገፋ ህዝብ ያሸንፋል!!

ድል ለአማራ ህዝብ!
ፋኖ ያሸንፋል!
ጎጃም እዝ ፋኖ!

 

ምንጭ፣ ሙሉጌታ አንበርብር