ከአራቱ የአማራ ጠቅላይ ግዛት ፋኖዎች የተሠጠ መግለጫ
የአማራ ሕዝብ እያካሄደ የሚገኘው የህልውና ትግል በዓይነትም፣ በትግልም፣ በስልትም ተለዋዋጭና የሥርዓቱን ፖለቲካዊ ሻጥር በሚያፈራርስ ተክለ ቁመና ላይ ይገኛል።
ትግሉ የሕዝባችንን ህልውና ማረጋገጥ በሚቻልበት ሃዲድ እየተጓዘ መሆኑን በርካታ አመላካች ጉዳዮች ቢኖሩም በአራቱም ጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ጋርዮሻዊ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ግዳጆችን ከመፈጸም ጀምሮ እንደ አንድ ተቋም ለመታገል የሚያበቁ ተግባራትንና ዘላቂ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ፋኖ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና የደህንነት አዛዦች በተደረገ ቅንጅታዊና የታቀደ ኦፕሬሽን በዛሬው እለት ማለትም በ04/08/2016 ዓ.ም የአሸባሪው ሥርዓት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ከወሎ ሠፈር እስከ ቦሌ ፍሬንድሽፕ ባለው አካባቢ የሥርዓቱ ወንበር ጠባቂ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ላይ አስደናቂ ኦፕሬሽን ሠርቷል።
ከረፋዱ 5:00 እስከ 7:00 የቆየው ይህ ልዩ ኦፕሬሽን የአማራ ፋኖ በጎንደር ቀጠናዊ ዘመቻ አስተባባሪ፣ የአጼዎቹ ክ/ጦር ዘመቻ መምሪያ አዛዥና በጃንተከል ብርጌድ ዋና አዛዥ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ የተመራ ሲሆን ከ30 በላይ የሥርዓቱ አገልጋዮች በፋኖ አርበኞች እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል።
በዚህ የታቀደ ወታደራዊ ኦፕሬሽን የተሳተፉ የአማራ ፋኖ አርበኞች ተልእኳቸውን በተሳካ ሁኔታ መፈጸማቸው የህልውና ትግላችንን ከክልላችን በፍጥነት አውጥተን ወደ 4 ኪሎ ለምናደርገው ግስጋሴ እንደ መቅድም የተጠቀምንበት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
በመሆኑም በዚህ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ውስጥ የኦፕሬሽኑ አርበኞች መሪ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ የተሰጠውን ግዳጅ አከናውኖ አርበኛ ጓዶቹን ሽፋን እየሰጠ ካስወጣ በኋላ በጠላት ጦር ከበባ ተደርጎበት እጁን ለጠላት ላለመስጠት እንደ አጼ ቴዎድሮስ የያዘውን ሽጉጥ ጨልጦ በጀግንነት ተሰውቷል።
የአጼ ቴዎድሮስ የግብር ልጅ የሆነው አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ ከ2008 ዓም ጀምሮ መሪር ትግል ሲያደርግ የነበረ፣ ዛሬ በጀግንነት እስከተሰዋበት እለት ድረስም በአማራ ፋኖ በጎንደር አጼዎቹ ክ/ጦር እንዲሁም ጃንተከል ብርጌድ ውስጥ ሲታገልና ሲያታግል የቆየ የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን በአርበኝነት ያስመሰከረ ጀግና ተዋጊ ነው። በአርበኛችን መሰዋት የገጠመን ሃዘን መሪር ቢሆንም ፋኖነት በነጻ ፈቃድ ለፍትህ፣ ለሐቅና ለሕዝብ ህልውና ዘብ በመቆም የሚከፈል መስዋዕትነት መሆኑን ለሰከንድም ሳንዘነጋ መሪሩን ሃዘናችንን ወደ መራር ትግል መቀየር የትናንት፣ የዛሬና የነገም የትግል መርሐችን መሆኑን እንገነዘባለን።
ስለሆነም፦
1ኛ፥ በአራቱም የአማራ ጠቅላይ ግዛቶች ለምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች 1ኛ. ከነገ 05/08/2016 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ዘመቻ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ በማካሄድ የአሸባሪው ሥርዓት ዙፋን ጠባቂ ጦር ላይ የማያዳግም እርምጃ እንድንወስድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
2ኛ. በጀግንነት የተሰጠውን ግዳጅ ፈጽሞ የተሰዋውን የአጼ ቴዎድሮስ የግብር ልጅ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌን አስከሬን በክብር እንዳያርፍ ጸያፍ የሽብር ተግባሩን በመፈጸም፣ ከ2 ቀናት በፊት በመቂ በኦነግ ኦፊሰር በአቶ በቴ ዑርጌሳ ላይ እና በመንግሥታዊ ነውር ላይ በማይሳተፉ በስማቸው በሚነግድባቸው የኦሮሞ ልጆች ላይ ስንኳን ሳይቀር፣ የሚከውነው መንግሥታዊው የሽብር ቡድን በእያንዳንዷ ተግባሩ ልክ አጸፋውን የሚቀበልበትን ቀጠናዊ፣ የተናበበና የታቀደ ሁሉን
አቀፍ ደመላሻዊ የአርበኝነት ተግባር እንድንፈጽም ጓዳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
3ኛ. የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የዲፕሎማቲክ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ቀጣይነት ያለውና ደረጃውም ከፍ ያለ ኦፕሬሽን በተከታታይ የምናከናውን መሆኑን እየገለጽን የተለያዩ አገሮች ቆንስላ ጽ/ቤት ሠራተኞች ይህንን ተረድተው የራሳቸውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጀምሮ የሥርዓቱን መፈራረስና መውደቅ በሐቅ እንዲገልጹ እንጠይቃለን።
4ኛ. በመላው ዓለም የምትገኙ የአማራ ተወላጆችና የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግልን በሐሳብም በግብርም የምትደገፉ ኢትዮጵያውያን የአማራ ፋኖ ትግል አድማሱን እያሰፋ ሥርዓቱን መቅበር ወደሚችልበት ምዕራፍ መሸጋገሩን ተገንዝባችሁ ጠንካራና የታቀደ የዲፕሎማሲ ሥራ በመሥራትና ከተበጣጠሰ የማይናበብ አካሄድ በመውጣት ትግላችንን ከፍ እንድታደርጉት ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
5ኛ. በተለይ ዒላማ ለተደረገው የአማራ ሕዝብ እንዲሁም የአፓርታይድ ሥርዓቱ በቋንቋና በሌሎች ማንነታችሁ ሚዛን ለአካላዊ፣ ስነ ልቡናዊና ኢኮኖሚያዊ ሰለባ እየዳረጋችሁ የምትገኙ በመላው ኢትዮጵያ በተለይ በአዲስአበባ ከተማና ዙሪያዋ የምትገኙ፤ እንዲሁም መኖሪያ ቤትህ ሳይቀር በላይህ ላይ እየፈረሰ ለስደት፣ ለረሃብና ለማኅበራዊ ቀውስ የተዳረግኸው የአዲስ አበባ ሕዝብ፣ ቁጭ ብሎ ነጻ አውጭ ከመጠበቅ ደካማ እሳቤ ወጥተህ በመዲናችን አዲስ አበባ በጀግንነት
ደሙ የፈሰሰውን አርበኛ ወንድምህ የተሰዋለትን የትግል ዓላማ በግብር በመደገፍ መንግሥታዊውን ሽብርተኛ ሥርዓት በተለያዩ መንገዶች እንድትታገለው አርበኛ ወንድሞችህ ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን።
6ኛ. በአጠቃላይ በመላው ዓለም የምትገኙ የሚዲያ አካላት ከነገ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በመላው አማራ የሚካሄደውን ዘመቻ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌን በልዩ ሁኔታ እየተከታተላችሁ ለሕዝብ እንድታደርሱና የሥርዓቱን ሠራዊት መፈራረስም ለዓለም ሕዝብ እንድታጋልጡ እንጠይቃለን።
ፈጣሪ የአርበኛችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያሳርፍ!
“ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!”
የአማራ ፋኖ በጎንደር
የአማራ ፋኖ በጎጃም
የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ
የምሥራቅ አማራ ፋኖ
አማራ፣ ኢትዮጵያ!!!