የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የወሎ ዕዝ ፋኖ ውህደት ፈፀሙ!

የምስራቅ አማራ ፋኖና የወሎ አማራ ዕዝ በመዋሃድ አንድ ወጥ የሆነ “የአማራ ፋኖ የወሎ ዕዝ” መስርተዋል። ውህደቱም ከተፈፀመ በኋላ የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ዋና አዛዡን ዋርካው ምሬ ወዳጆን፣ ምክትል አዛዡን ደግሞ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤን አድርጎ መርጧል። ውህደቱ በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈጸመ ሲሆን፤ በቀጣይ የዕዙን መዋቅራዊ አደረጃጀት በሚመለከት በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ጦሩም የደስታ ተኩስ በመተኮስ ውህደቱ ተፈጽሟል።