Fano Unity Council

የራያ ህዝብ ሰቆቃና ስደት ይቁም!

 

ከፋኖ እንድነት ምክርቤት የተሰጠ መግለጫ

 

አብይ አህመድ ዓሊ ስልጣኔ ላይ መቆየት የምችለው “ሴማዊ” ብሎ የፈረጃቸውን የአምሓራ፣ የትግሬንና የኤርትራ ህዝብ እርስ በእርሱ ተናክሶ ተጨራርሶ ከተዳከመ ብቻ ነው ብሎ ለኦፒዲኦ  የፕሮቴስታንት ወታደራዊና ፓለቲካ መሪዎች ባደረገው ሚስጥራዊ ስብሰባ የገለጸው ቅጂ ሾልኮ ወጥቶ የፋኖም፣ አንዳንድ የህወሓትም የኤርትራ መሪዎችም አንዲያነቡት ተደርጎ ነበር።

ይህን ተንኮል የፋኖ አመራሮች ስለተረዱ የትኛውም የፋኖ አደረጃጀት አመራሮች በህወሓት ላይ ያለንን አቋም እንድንመረምርና ግጭትን የሚቀሰቅስ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወሰድ ስምምነት ላይ ስለተደረሰ በራያ ህዝብ ላይ በሚካሄደው ማፈናቀል ዘመቻ ላይ ነገሩን የሚያጋግል መግለጫ እንዳይሰጡ ተደርገዋል።

ይሁንና አሁን ህወሓትና ኦፒዲኦ ተጣምረው ነገሩን ለማጋጋል ከ50 ሺ በላይ አምሓሮች እንዲፈነናቀሉ ተደርጓል። የራያ ራዩማ መሪ የነበረው አቶ ሞላ በአብይና በነጄኔራል አበባው ትእዛዝ ቀይ ሽብር እንዲፋፋምበት ተደርጓል።

የነዚህ የቀይ ሽብር አፋፋሚዎች ከህዝብ እይታ ውጪ ስላልሆኑ ጊዜው ሲደርስ እነሱም ለፍርድ ይቀርባሉ።

ብአዴኖችም መስሏቸው እንጂ የዚህ አይነቱ ርሸና ለነእነ አረጋ ከበደም እና ጀነራል አበባውም አይቀርላቸውም።

ይህንን መግለጫ እንድንሰጥ ያስገደደን የህወሓት መሪዎች ከስህተታቸው አለመማራቸውና ከመካከላቸውም አርቆ የሚያስብ ሰው በመጥፋቱ ነው። በህዝብ ፈቃድ እንጂ በጉልበት የሚጸና ነገር እንደማይኖር የህወሓት የ27 አመት አገዛዝ ምሳሌ ነው።

ህወሓት በጠመንጃ ያቆመው ነገር ሁሉ ፈርሷል። እንኳን ስርዓቱ በመለስ ዜናዊ ስም ተሰይመው የነበሩ ትናንሽ ተቋማት ሁሉ እራሱ ጡት እያጠባ ባሳደጋቸው አብይ አህመድና ብርሀኑ ጁላ ተፍቀው አዲስ ስም ተሰጥቷቸዋል።

ስለዚህ ህወሓት የአብይ አጀንዳ ከማስፈጸም እንዲታቀብ፣ የተጀመረው ህዝብን ማፈናቀሉን እንዲያቆም፣ የተጠነሰሰውንም  የአማራንና የትግራይን ህዝብ የማጫረስ አጀንዳ አስፈጻሚ እንዳይሆን ህወሓትን ለመምከርና ወደ ራያ የላከውን ጦር በአስቸኳይ እንዲያስወጣ ለመጠየቅ ነው።

የህወሓት መሪዎች ሊረዱት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር፣ ህወሓት የአማራን ህዝብ በመጥላቱ የትግራይን ህዝብ ጎዳ እንጂ አንድም የጠቀመው ነገር የለም።  እስቲ የህወሓትን ትላልቅ ፓሊሲዎች እንይ፤

፩ኛ  የኤርትራ ህዝብና ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾች ናቸው። አዱሊስ የአክሱም ስልጣኔ ወደብ ነበረች። ዶግዓሊና ሰቲት አጼ ዮሃንስ አሉላን ልከው ደማቸውን አፍስሰው ቅኝ ገዢዎችን የመከተቡቸው ቦታዎች ናቸው።  አጼ ዮሃንስ የግብጽን ጦር የደመሰሱበት ጉንደትና ጉራ በአሁኑ ኤርትራ ውስጥ ነው ብሎ ብዙ ሰው ስለ አንድነትና እኩልነት ሲሟገት፣ መለያየትና ትናንሽ ሀገሮች መፍጠር ለትግራይም፣ ለኤርትራም፣ ለኢትዮጵያም  ህዝብ አይጠቅምም ብለው በመቶ ሺዎች ህይወታቸውን ሲሰጡ፤ የትግራይ ልጆች ደግሞ ይህ የአክሱምም የዮሃንስም ምድር አይደለም፣ “ኢትዮጵያዊ በቅኝ የያዘችው” ሀገር ነው ብለው 20ሺህ የትግራይ ልጆች ወደ ኤርትራ ልከው በናቅፋ ደማቸውን አፍሰው ኤርትራን አስገነጠሉ። እንዲያም ሆኖ የኤርትራ እና የአማራ ህዝብ ግን ዝምድናውን አልበጠሰም።

ይሁንና አማራን እጎዳለሁ ብሎ ህወሓት የወሰደው እርምጃ ማንን ጎዳ?  ትግራይን ወይስ አማራን? አማራን ነጥዬ አስጠቃዋለሁ ብሎ ያሰበው ህወሓት በአማራና በኤርትራ መሀከል የጠነከረ ወንድማማችነት እንዲፈጠር በር ከፈተ። በተቃራኒው አስመራ፣ ምጽዋ፣ አሰብ ሰርቶ ከብሮ ኢኮኖሚውን ሲቆጣጠር የነበረው የትግራይ ተወላጅ ጥርግ ተደርጎ ከኤርትራ ተባሮ አዲስ አበባ ጃንሜዳ በላስቲክ ድንኳን ኑሮውን እንዲገፋ ተደርጎ፣ መጨረሻ ላይ ያ ሁሉ ባለጸጋ መዘጋጃ ቤት ነው የቀበራቸው።
ጊዝያዊ ማጭበርበር ውሸትና ተንኮል ዘላቂ ወዳጅ እንደማይፈጥር ህወሓት ምሳሌ ነው።  እውነታው የአማራ ሀብታም ቀርቶ ሱቅ በደረቴ የነበረው በኤርትራ አልነበረም። ይልቁንም እውነቱ ሲወጣ በኤርትራና በአማራው በኩል የማይሰበር መተማመንና ወንድማማችነት ተፈጠረ።

፪ኛ፣ እምዬ ምኒሊክ ምንም አድርጎው ሀገሩን ይፍጠሩት፣ ሰፊ ሀገር በመፈጠሩ የትግራይ ህዝብ በመላው ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሶ፣ ነግዶ፣ አርሶ፣ ጋራዥ ከፍቶ፣ አስተማሪ፣ ወታደር፣ ዳኛ፣ ሀገረ ገዢ ሆኖ፣ ባህሉ፣ ልብሱ፣ፊደሉ በመላው ኢትዮጵያ ተቀባይ እንዲሆን እነ ዳግማዊ ምኒልክና እነ አጼ ኃይለስላሴ በማድረጋቸው የትግራይ ህዝብ ምን ተጎዳ?

መለስ እንዳለው “ምኒሊክ በጠመንጃ የሰበሰባት ሀገር ብትበታተን” ግድ የለንም ብለው ሃገሪቷን ሸንሽነው ለብሄር ባላባቶች በማከፈላቸው የትግራይ ህዝብ ምን ተጠቀመ? እራሱ ባደራጀውና ባሰለጠነው የኦፒዲኦ ካድሬ፣ ማርኮ ጄኔራል ባደረጋቸው ወታደሮች የትግራይ ስም ያለው ሁሉ እየተለቀመ ወደ እስር ተጣለ። ንብረቱ ተዘረፈ፣ ባከነ፣ አንዳንዱ ያለ ፍርድ ተረሸነ። ታድያ ህወሓት የዘራውን መርዝ ማን አጨደው?  የትግራይ ህዝብ።

፫ኛ፣ አሁን ደግሞ ያውም ኦፒዲኦ የራሱን ካድሬዎችን ሰግስጎ ቤተክርስትያንን ለመቆጣጠር ቀን ከለሊት በሚሰራበት ወቅት፣ የትግራይ ኃይማኖት ለምን ከአክሱም ተነስቶ የኦሮሞው፣ የጋሞው፣ የወላይታው፣ የጉራጌው እና የከተመኛው ሆነ? ለምን የትግራይ ቄስ ቀዳሽ፣ ነፍስ አባት ሆኖ በመላው ኢትዮጵያ መጠቀሙን እንደ ጉዳት ቆጥሮ ‘መንበረ ሰላማ” የሚባል የማፍያ መነኩሴዎች ፈጥሮ ወደፊት የትግራይ ቄስና መነኩሴ ከመላው ኢትዮጵያ ተጠራርጎ ወደ ትግራይ የሚመለሱበትን ጥርጊያ መንገድ ደልድሏል።

ታድያ ከነዚህ ሁሉ የህወሓት ፓሊሲዎች የትግራይ ህዝብ ምን አተረፈ? ከአማራውና ከትግራይ ህዝብ ማንስ ነው በብዛት የተጎዳው?

ህወሓት ለሻዕቢያ ቢሞትለትም ሻቢያ ህወሓትን አላከበረውም።  እንደውም ናቀው ቀጠቀጠው። ህወሓት ማርኮ አደራጅቶ ጄኔራል አድርጎ የሾማቸውን እነ ብርሀኑ ጁላ እንዲሁም አብይ ትግርኛ በመናገሩ ብቻ  ከተራ ወታደርነት አንስቶ ኮለኔል፣ ዶ/ር እና የሃገሪቷ  የስለላ ተቋም ሀላፊ በማድረግ  አከበራቸው። በአማራ ጥላቻ ላይ የተመሰረተው የህወሓት ርዕዮት የትግራይን ህዝብ መከራ ውስጥ ነው የጨመረው። አብይ የህወሓትን ዘረኝነት ከልጅነቱ ስለተረዳ በትግርኛ እያሳሳቀ ወስዶ ወደማይወጣው ገደል ገፈተረው።  ስልጣን ቀምቶ አንድ ሚሊዮን የትግሬ ህዝብ ቅነሳ ተገበረ።

ይሁንና አሁን የአዲስ አበባን ቤተ ክርስቲያናትንና መብራት ያጨናነቀው ከትግራይ ተጎሳቁሎ ተርቦ የተሰደዱ እናቶችና ልጆች ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሓትና በትግራይ ህዝብ መሀከል ያለውን ልዩነት ይረዳል።

አሁን እያንዳንዱ የትግራይ ልጅ ረጋ ብሎ ለመሆኑ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ያመጣለት አንድ ጥቅም ካለ እስቲ ይጻፈው።
በህወሓት ፓሊሲ አማራ ተጎድቶ የትግራይ ህዝብ የተጠቀመ ቢሆን እንኳን አንድ ነገር ነው። ይሁንና የህወሓት ፓሊሲ በይበልጥ እየጎዳ ያለው ያንኑ የፈረደበትን የትግራይ ህዝብ ነው። እንደ ትግራይ ህዝብ በልጆቹ እንዲቀጣ የተፈረደበት ብሄር የለም።

አሁን አምሓራው ወጣት አይኑ ተከፍቷል። ትንሽ ካንቀላፋ እንደሚታረድ ያውቀዋል፣ ማንም እንደማይጮህለትም ያውቃል። ስለዚህ እራሱን ሊከላከልለት የሚያስችለውን ኃይል ቀን በቀን እየገነባ ነው።  በአንድ አመት ውስጥ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ ኃይል ገንብቷል።  በቅርብ ቀን መላው ኢትዮጵያ አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ ሆኖ ለመጨረሻ ግዜ ተቧድኖ የሚረግጠውን የአብይን ስርዓት እንደሚያስወግድ ጥርጥር የለውም።

አንድ ህወሓቶች ያልተረዱት ነገር የኦፒዲኦ የስልጣን ዘመን ማብቃቱን ነው። ኦፒዲኦ የሚሰጠውም የሚነፍገውም ምንም ነገር የለም።

ስለዚህ ህወሓት የአብይ አጀንዳ አስፈጻሚ ሆኖ በአምሓራ ህዝብ ላይ ሰቆቃ በመፈጸም ከጉዳት በስተቀር የሚያተርፈው ነገር የለም።

ስለዚህ የህወሓት መሪዎች የትግራይን ዘላቂ ጥቅም የሚከበርበት የወንድማማችነት ትብብር ላይ እንዲያተኩሩ እንጠይቃቸዋለን። የአብይ ተራ መጠቀሚያ ከመሆን እራሳቸውን አድነው፣ ከመላ ራያ በአስቸኳይ ታጣቂዎቻቸውን እንዲያስወጡ እንጠይቃለን።