Ethiopia Fano

የህዝባዊ አመጽ ጥሪ

የአምሓራ ህዝብ ያለው ምርጫ ሁለት ብቻ ነው። እንደኛው ተባብሮና ተያይዞ በህይወት የመኖር መብቱን ማረጋገጥ ነው ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ በወለጋ፣ በአርሲና በሌሎች ቦታዎች እንደተገበረው ቤት ለቤቱ በሚመጡ ባለ ገጀራና ባለ ጥቁር ክላሽ ታጣቂዎች መታረድ፣ መጨፍጨፍ ነው።

ስለዚህ የአምሓራ ህልውና ለፋኖና ለጥቂት ተሟጋቾችና ቀስቃሾች የሚተው አይደለም ። ሁሉም ሰው ራሱን ለማዳን መነሳት አለበት።

የፋኖ እንድነት ምክር ቤት የዛሬ እንድ አመት ተኩል ላይ ትግሉ እንዴት መካሄድ እንዳለበት የሚያመላክት “የጉንዳን ትግል” የሚል የጥናት ጽሁፍ ለመወያያ አቅርቦ ነበር። https://fanolisan.org/100/
አሁንም ይህንን የትግል ስትራቴጂ መተግበር ግድ ይላል።

አሁን አብይ አህመድ የመጨረሻውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማካሄድ በርካታ ሰራዊት ወደ ክልሉ በማስገባት ላይ ነው። ስለዚህ ይሄን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማክሽፍ  ትግላችንን እሱ  በመረጠውና በፈቀደው ቦታና ግዜ ሳይሆን እኛ በምንፈልገው መንገድ ማስኬድ ግድ ነው።

በዚህ መሰረት፤
፩ኛ፣ ሁሉም ፋኖ በያለበት የመረጃ ማሰባሰቡንና ማጋራቱን በአስቸኳይ እንዲጀምር። ህዝቡም የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ባየበት ቦታ ሁሉ እንዲጠቁም።

፪ኛ፣ አብይ በህዝብ ላይ ያወጀውን ዘመቻ መቀልበስ የሚቻለው በመረጃ ላይ ተመስርቶ ኃይልን ለጥቃት በማያጋልጥ መንገድ የደፈጣ ጥቃት በማድረግ ሰራዊቱን ግራ በማጋባትና ሰራዊቱ ከትርጉም አልባ ሞት እርሱን ለማዳን ከነ ትጥቁ ከፋኖ ጋር እንዲቀላቀል አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ነው።

፫ኛ፣ ፋኖ ህዝብን በማስተባበር መንገድ መዝጋት፣ የአቅርቦት መንገዱን ማስተጓገል፣ ሰራዊቱ በእያንዳንዷ እርምጃ ላይ ስጋት ውስጥ እንዲገባ ማድረግ።

፬ኛ፣ ፋኖም ሆነም አልሆነ አምሓራ እስከሆነ ድረስ ስርአቱ ወጣቱን ከመግደል አይመለስም። ስለዚህ ወጣቶች ከተሞችን በአስቸኳይ ለቀው ወደ ነጻ መሬት በመግባት እራሳቸውን ከሞት፣ ከእስራትና ከድብደባ እንዲያድኑ።

፭ኛ፣ ይህንን ትግል መላው ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ ስርአቱን ለማዳከም የራሱን አጀንዳ እየቀየሰ ሰርአቱን ወጥሮ መያዝ አለበት። ትልቁ ስህተት በኔ አይደርስም ብሎ መዘናጋት ነው። እነ ሽመልስ አብዲሳ የአዲስ አበባን ዙሪያ አፍርሰው ህጋዊ ደሀ አደረግናቸው ሲሉ የአዲስ አበባ ሀብታም የሱ ቤትና ፎቅ የማይፈርስ መስሎት ተዘናግቶ ነበር። አሁን ሁሉም የስርአቱ እቅድ ግልጽ ሆኖለታል። የኦፒዲኦ ስርአት ግቡ ዘር ማጥፋት ነውና አምሓራውን አጥፍቶ የሚተወው ነጻ ብሄረሰብና ማህበረሰብ አይኖርም። ስለዚህ ሁላችንም በያለንበት እንደ ጉንዳን በትንሹም ቢሆን መቆንጠጥ አለብን።

፮ኛ፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት ሆይ ለ30 ዶላር ደሞዝ ብለህ ለኦፒዲኦ ጌቶችህ አትሙት። ልጅህን የሚያሳድግልህ ወይንም እናትህን የሚጦርልህ የለም። ለኦፒዲኦ ባለስልጣናት ምቾትና ዘረፋ ጭዳ አትሁን። ከቻልክ 10 ሚልዮን ብርና አዲስ አበባ ውስጥ መሬት ተሰጥቷቸው በቅጥረኝነት የሚማግዱህን ጀነራሎች እያስወገድክ የጓጉለትን ህዝብን በማጥፋት ለመንቀባረር ያሰቡትን በአጭሩ አስቀር። ይህንን ማድረግ ካልቻልክ ደግሞ ትጥቅህን ይዘህ ስርአቱን የማስወገዱን ትግል ተቀላቀል።

ስለዚህ ተነስ ታገልና መብትህን አስከብር። ይህ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው።