Jan 21, 2025
የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ውህደት ፈጠሩ
የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ኅዳር 29/2017 ዓ.ም በሁለቱ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም በበላይ ጠባቂ አባቶች አማካይነት በይፋ አንድ ለመሆን ከስምምነት ላይ መድረስ መቻላቸውን ከገለጡ በኋላ በርካታ ሥራዎች ተከናውነው እነሆ ዛሬ መዋቅራዊ ውሕደትና አንድነት ተፈጥሮ ለሕዝባችን፣ ለሠራዊታችን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ይህ ተቋማዊ አንድነት የአማራ ፋኖ በጎንደርም ሆነ የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ከዚህ በፊት የሚጠሩበትን ስም አክስመው ከዛሬ ጀምሮ “የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር” በሚል የተቋም ስም የሚጠራ ይሆናል። የተቋሙን ሎጎ በተመለከተ በቀጣይ ይፋ እናደርጋለን።
በዚህ መሠረት የተቋሙን አወቃቀርና አመራሮች እንደሚከተለው ሰይመናል።
አርበኛ ሐብቴ ወልዴ | ሰብሳቢ |
አርበኛ ባዬ ቀናው | ም/ሰብሳቢ |
አርበኛ ሳሙኤል ባለእድል | ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ |
አርበኛ ሸጋ ጌታቸው | ም/ወታደራዊ አዛዥ |
አርበኛ ማንደፍሮ ተሠማ | የጽ/ቤት ኃላፊ |
አርበኛ ማሩ ጥሩነህ | ም/ጽ/ቤት ኃላፊ |
አርበኛ ያለው አዱኛ | የዘመቻ መምሪያ አዛዥ |
አርበኛ ዮናስ አያልቅበት | ም/ዘመቻ መምሪያ አዛዥ |
አርበኛ ግዛቸው አሌ | የልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ አዛዥ |
አርበኛ ሻምበል መሳፍንት | ም/የልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ አዛዥ |
ብ/ጄኔራል ተዘራ ንጉሤ | የወታደራዊ እቅድና እስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ጌጡ ድረስ | ም/ወታደራዊ እቅድና እስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ አስቻለው በለጠ | ም/ ሰብሳቢና የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ አራጋው እንዳለ | ም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ |
ሻምበል አምሳሉ ማዘንጊያ | የሎጀስቲክስ አቅርቦትና ሥርጭት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ስጦታው መልኬ.. | ም/የሎጀስቲክስ አቅርቦትና ስርጭት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ደምሰው አባተ | የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ አንድነት አማረ | ም/የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ አበበ ብርሐኑ | የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ሸርብ አሸነፍ . | የሕዝብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ታደሠ ወርቁ | ም/የሕዝብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ጸዳሉ ሙላት | የማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ዓለሙ መለሰ | ም/የማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ቢኒያም አለምነው | ም/የገንዘብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ በዬነ አለማው | የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ አያናው አዱኛ | ም/የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ሲሳይ አሸብር | የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ተመስገን ውባንተ | ም/የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ዮሐንስ ንጉሡ | የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ድረስ ሞላ | ም/የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ባሻ ስጦታው | የሰው ሀብት አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ማንዴላ እያዩ | ም/የሰው ሀብት አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ዶ/ር አታለለ ሰጠኝ | የጤና መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ እያቸው ብርሐኑ | ም/የጤና መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ በላይ ዘለቀ | ሕግና ሥነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ ማሩ ቢተው | ም/የሕግና ሥነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ... | የመረጃና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ |
አርበኛ... | ም/የመረጃና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ |
መሆናቸውን ለሠራዊታችን እንዲሁም የኅልውና ትግላችንን በስስት ለሚመለከተው በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም ለሚኖረው ሕዝባችን መግለጽ እንወዳለን። ከዚህ በተጨማሪም የበላይ ጠባቂ አርበኞች ምክር ቤት አባላትንም እንደሚከተለው ሰይመናል።
አርበኛ መሣፍንት ተስፉ | ሰብሳቢ |
አርበኛ አረጋ አለባቸው | ም/ሰብሳቢ |
አርበኛ ሻምበል መሠረት ዓለሙ | ፀሐፊ |
አርበኛ ሠፈር መለሰ | አባል |
አርበኛ ሻምበል ገብሩ ልይህ | አባል |
አርበኛ ደስታው ደመላሽ . | አባል |
አርበኛ እሸቴ ባዬ | አባል ሆነው ተሰይመዋል |
– Mulugeta Anberber