የፋኖ አንድነት ምክር ቤት መግለጫ ክፍል ፫ እና ፬

ክፍል ሶስት
የፋኖ አንድነት ምክርቤት ከዜሮ እስከ ዛሬ

የፋኖ ትግል ውጤት እያመጣ መሆኑን ለመረዳት የአብይን እንቅስቃሴ መመልከት በቂ ነው። ፋኖ እንዳቀደው የአማራ ሕዝብ በህይወት የሚያድነው ነጻ አውጪ መጠበቅን አቁሞ የራሱን ነጻነት ሲያውጅ ነው። ይህ ደግሞ ሁላችንም በአይናችን እያየነው ነው። ወጣት አዛውንት፣ ተማሪ ምሁር፣ ገበሬ ነጋዴ ሁሉም ለመብቱ ቆሞ መታገል ጀምራል። በመቶ ሺ የሚቆጠር ሰው ወደትግሉ ገብቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። የሚችለው ጠመንጃውን ተነስቷል፣ ገበሬው የሚችለውን እያካፈለ እየቀለበ ነው፣ ወጣቱ በመረጃ በፕሮፓጋንዳ እየሰራ ነው፣ በውጪ ያለውም የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው። ይህ ጅምር ነው ገና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንዝዘው ቁጭ ያሉ ከእንቅልፋቸው እየነቁ እራሳቸውን ለማዳን ወደ ትግሉ ይቀላቀላሉ ያለበለዚያም በምርጫቸው የሽመልስ አብዲሳ ሚሊሽያ ያርዳቸዋል።

ይሁንና አሁን በትንሹ ጠመንጃ ይዞ የተነሳው የፋኖ አብይን ሲያሯሩጠው ማየት በቂ ነው። በመጀመርሪያው የማጥቃት ዘመቻ ያቀደው መሳሪያ መማረክና እራስን ማስታጠቅና የብአዴንን መዋቀር ማፍረስ ነበር። ይህ ተሳክቷል።

አምሐራ መሆኑን እረስቶ ባርነትን የመረጠው ብአዴን ለህወሀትና ለሽመልስ አብዲሳ ማደር አትራፊ እንዳልሆነ እየተረዳ ነው። አሁን እበላ ብሎ አብይን የከበበው ጥሎት መሸሹን እያየ ነው። ህሊና ያላቸው ወደ ትግሉም ተቀላቅለዋል። ሌሎቹም በዘረፋ ባህር ውስጥ እነደ ኖህ ግዜ የዘረፉት አንገታቸው ድረስ ደርሶ አልበቃ ብሏቸው አማራን እየሰደብን እየገደልን ተጨማሪ ጥቅም እናገኛለን ብለው እነሱም ልጆቻቸው የማይበሉትን ሀብት እያጋበሱ ነው።

ለሰላሳ ሁለት አመታት አማራን መስደብ፣ መግደል፣ መግረፍ፣ ማፈናቀል በህወሀት እና በብልጽና የሚያሾም ነበር። አማራን የሰደበ፣ የደበደበና የገደለ በፈጣን የስልጣን እርከኑን እየዘለሉ መሾም የተለመደ ነበር። አማራን መስደብና መግደል እንደ ታማኝ አገልጋይ በመለስ ዜናዊም ሆነ በነሽመልስ አብዲሳም የሚይሳሳይ ዋነኛ መመዘኛ ነው።

ከጅምሩ እነ ታምራት ላይኔ “ጊዜው አሁን ነው አማራን በሉት’ በማለትና ኤርትራ ድረስ ሄደው በአማራ ስም ይቅርታ
በመጠየቅ” እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ደርሰው ነበር። “አማራ ልጋጋም ያለ፣ አማራው ዛፍ ስለቆረጠ አባረርኩ ያለ

እንደ ሽፈራው ሽጉጤ ያለ፣ አማራን ለመግደል የአብይ አሽከር እያለ የሚፎክረው እነ ጄኔራል አበባውና አገኘሁ ተሻገር በመሬትና በሀብት ሊሰምጡ ነው። በገደሉና በተሳደቡ ቁጥር በስልጣን ላይ ስልጣን በመሬት ላይ መሬት ይጨመርላቸዋል። ለአማራ የተቆረቆረ ደግሞ፣ በለሆሳ ቢሆን የአማራ ግድያ ይቁም ያለ አዋሽ አርባ ተወስዶ ይሰቃያል።

የብአዴን ባለስልጣናት ከአማራ መሀበረሰብ ውስጥ የወጡ ቢሆኑም የእድገታቸው መሰላል በአማራ ላይ ባላቸው ጥላቻና ጭካኔ ብቻ ነበር። አሁን ግን ይህቺ ጥጋብና ጥላቻ የምታስሾም ሳትሆን ጥይትን ያለ ውሀ የምታስውጥ ሆናለች። ወደ ፌዴራል ተሾሜ እሄዳለውሁ፣ ቪላ ቤት ይሰጠኛል፣ አጃቢና V8 ይኖረኛል፣ ቅቅቴን አራግፌ በቦስተን ስፓ ወገቤን እየታሸሁ፣ ሼራተን እየዋኘሁ እኖራለሁ የምትለው የደሀ የህልም እንጀራ አማራን በመግደል እንደማትገኝ ግልጽ ሆንዋል። ዛሬ ሁለት ሚሊዮን የሚገመት አማራ ታጥቋል። ልጁን የገደለበትን ወይንም ያስገደለበትን እስከ ዘር ማንዘሩ ለፍርድ ያቀርባል። እነዚህ በልተው የማይጠቅቡ ህወሀት ከእረኝነት ሰብስቦ ያመጣቸው ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለልጆቻቸው ፍዳ አውርሰው ነው የሚሄዱት። የደርና የህወሀት ጥጋብተኞች ዛሬ የት ነው ያሉት። ሀገርም ውሽት ይሁኑ በስደት የአማራ ህዝብ እያደነ ለሚያፈሱት የህጻናትና የአዛውንት ደም ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።

እሁን ትንፋሽ ያገኙ ቢመስላቸውም ካሁን ወዲያ የሞት እንጂ የጥጋብ ዘመን እንዳልሆነ ተረድተዋል። ለዚህ ነው አብይ አህመድ ለብቻው ሲክለፈለፍ የሚታየው።

ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም አነሰም በዛም በኮሚኒስት እዕዮት ያበዱ ህይወታቸውን ሊሰጡት የተዝውጋጁ ካድሬዎች ነበሩት። ለገሰ ዜናዊም ካሰለፋቸው 60 ሺ ታጣቂዎች ውስጥ ህይወታቸውን ሊሰጡት የሚችሉ በሺዎች ነበሩ። ፋኖ አንደነት ኮሚቴ ለአብይ አህመድ ሊሞትለት የሚችለው ሰው ማን ነው ብሎ ውይይት አድርጎ ነበር። ስም እየጠራም አቋማቸውን የስነ ልቦና ጥንካሬያቸውን መዝኗል።

ለአብይ አህመድ ብርሀኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰ፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ደመቀ መኮንን፣ሽመልስ አብዲሳ፣ ብርሀኑ ነጋ፣ ሬዲዋን ሁሴን፣ ብለነ ስዮም፣ ታደሰ ጫፎ፣ ብናልፍድ አንዱአለም፣ ተስፋዬ ቤልጂጌ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አብረሀም በላይ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ በለጠ ሞላ ወዘተ ይሞቱለት ይሆን ብሎ ተወያይቷል። እነዚህ ሁሉ ቶሎ ቶሎ ብለው የሀብት ዘርፈው አሜሪካ፣ ዱባይና ካናዳ ቤት ገዝተው ለመሸሽ የተዘጋጁ
ረሀብተኞች እንጂ ለአብይ አህመድ ጋር ሊሞቱ የተዘጋጁ ወንድሞቹ እንዳልሆኑ የፋኖ ግምገማ አሳይቶ ነበር።

እንደተተነበየውም ይሄው አሁን አብይ ብቻውን ነው የሚያነበንበው፣ በየቦታው እንዳበደ ውሻ ሲከንፍ የሚታየው።

አብይ ሁሉም እየክዳውና ስለሄደ ልቡ ሲሸበር ባለ ቀይ ኮፍያ ወታደሮቹን እራት እየጋበዘ በመሀላቸው እየዞረ ሲያቅፍ ሲደባብስ ላየ “እናንተ ብቻ ናችሁ የቀራችሁኝና አደራ እናንተም እንዳትጥሉኝ” የሚል ይመስላል።

በጥዋት ተነስቶ ሄሊኮፕተር አስነስቶ ጅማ ይገባና መደበቂያውን ሲቃኝ ሲያስገነባ ይውላል፤ ከዛ ተመልሶ ህወሀትን በሬዲዋን ሁሴን በኩል ለምን በጌምድርንና ራያን ወራችሁ አትወስዱም ይላል። ከዛ አልፎ የህወሀትም 20ሺ የሳምሪ ጦር በሱዳን ጦርነት ምክያት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ቀለብ በማቆሙ ሊበተን ሲል እንዳይበተኑ እኔ ቀለባቸውን ብሎ የሳምሪን ኮማንዶ በዶላር እየቀለበ ነው። ይህንን እነ ተመስገን ጥሩነህ፣ እነ ደመቀ መኮንን ያውቃሉ። የአማራ የደህንነት ካድሬና እበላ ባይም ያውቃሉ። ይሁንና አማራን ዘር ሊያጠፋ የተነሳውን ሀይል እነሱ እኮ አማራ ቢሆኑም ብአዴን ናቸው ብሎ ይተዋቸው ይመስል አሁንም በራሳቸው ላይ ሀይል ከሚያደራጅ ሀይል ጋር ይሰራሉ።

ይህ ሁሉ የፋኖን ግስጋሴ ማስቆም ስላልቻለ ነው። አሁን ደግሞ ኤርትራ ፋኖን እየደገፈ ነው ብሎ ስለጠረጠረ፤ የህወሀትንም የበቀል ስሜት እቀሰቅሳለሁ፣ አማራውና ፣ ብሄረኢትዮጵያዊውም ቀይ ባህር ስለው ልቡ ይከፈላል ብሎ ስለቀይ ባህር ሲያወራ ይውላል። አሁን የተሰጠውን አጀንዳ አንጠልጥሎ የሚባዝነው “ምሁር ነኝ” የሚለው እንጂ አብይ አጀንዳ አይደለም።

በመጨረሻ ይህ ሁሉ እንዳልሰራ ስለተረዳ በየጃን ማሮ ተለማምጦ የኦነግ ጦር አዲስ አበባ ዙሪያ አምጥቶ ምሽግ ይዞ እንዲያልቅለት እየተማጸነ ነበር። ይሁንና የጃን ማሮም ፍላጎት በአብይ ምሽግ ገብቶ ከመሞት በላይ ስለሆነ ድርድሩ ለግዜው አልተሳካም።

አሁን ጃን ማሮ አብይ የሚፈልጋትን ፊርማ ፈርሞ፣ በቴሌቭዥን መግለጫ ሰጥቶ፣ ተስማምቻለሁ እስካላለ ድረስ ከታንዛንያ አይወጣትም። ያለበለዚያም ጃን ማሮ ልወዝወዘው በእግሬን እያንጎራጎረ በደቡብ ሱዳን መግባት አለበት።

የአብይ ይህ መቅበዝበዝ በሜካናይዝድ ጦር እንኳን ድል ማምጣት ባለመቻሉ ነው። አብይ በየቀኑ የፋኖ ቁጥር እየጨመረ የሁለተኛው ዙር ጥቃት እየተቃረበ መሆኑን ስለገባው ደግሞ በድሮንስ ፋኖን አሸንፋለሁ ብሎ ንጹሀንን እየፈጀ ነው። የዚህ ደግሞ መላውን የአማራ ህዝብ እያስሸፍት በር ከፍቷል። ሞትና መታረድ የተፈረደበት አማራ ድሮን ፈርቶ ይገብርና ከዛ ተሰልፎ ይታረዳል የሚል ግምት ትልቅ የቂልነት ነው።

የፋኖ ትግል የመጀመሪያው ምርአፍ በድል ተጠናቋል። ፋኖ የሳተላይት ሬዲዮ የለውም በርቀት የመካናይዝድ ብርጌዱን የሚያስቆምበት የትካሳ ሞርታር ችግር አለበት። ይህ በቅርብ ግዜ ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዛ በአጭር ቀን ሰራዊትቱ መሳሪያውን አስረክቦ ወደ መጣበት ይመለአል። ፋኖ አብይ በላከው በራሱ ታንክ ነው አዲስ አበባ የሚገባው። ይህ አያጠራጥርም ጠብቁን። በክፍል አራት እስካሁን ፋኖ የሄደበት ታክቲክ ይቀርባል። እስከዛው ሁሉም ለትግሉ በሚችለውም መንገድ አስተዋጻኦውን ይቀጥል። ፋኖ ማንንም ነጻ አያወጣም ሁሉም እራሱን ከባርነት ነጻ ሲያወጣ ነጻ ሀገር ይኖረናል። ስለዚህ እጃችሁን አጣጥፋችሁ ፋኖ ነጻ ያወጣናል ብላችሁ የምትጠብቁ ይልቆንም ሀሞታችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ ነጻ ነኝ። የማንም ስርአር ባርያ ሆኔ መኖሩ በቃኝ በሉ። አንባገነን የሚቆመው እሺ አቤት ብሎ የሚገዛ ህዝብ ሲኖር ነው። ከአማራ ገበሬ እንማር።

ክፍል አራት

የፋኖ አካሄድ ወይንም ታክቲክ

ፋኖ ባለፋት አመታት ውስጥ በተናጠል የራሳቸው፤ የቤተሰቦቻችን የሀገራቸው ህልውና አደጋ ላይ ሊወድቅ ነው ብለው የሰጉ የአማራ ልጆች በተለያየ ቦታ መደራጀት የጀመረ ወታደራዊ ንቅናቄ ነው። እንደ ማርክሲስታዊ ድርጅት ሰባት ሰዎች ፓሪስ ላይ ወይም ደደቢት ተሰብስበው ከማርክስ የኮሚኒስት ማንፌስቶና ከአልባንያ ለቃቅመው የሰፉት ጠባብ ጥብቆ አይደለም። በዚህ ጠባብ ጥብቆ ውስጥ ሕዝብ በግድ መግባት አለበት በማለት ሕዝብን
የሚከረክም ድርጅት አይደለም።

ፋኖ የኢትዮጵያ አዲስ ጅማሬ ነው። ኢትዮጵያዊ እሳቤ በፈረንጆቹ በመጽሀፍ ተጽፎ ስለማይገኝ ብዙ ሰው ግራ ቢጋባ አይገርመንም።

ፋኖ ሲጀምር ከላይ ወደታች የተዋቀረ ድርጅት አይደለም። ስለዚህ 7 የኮሚቴ መሪዎች በዚህ ቦታና በዚህ ቀን መሰረቱት የሚባል ነገር የለውም። ሰባት ታላላቅ መሪዋች የሚባሉም እንዲኖሩትም አይፈልግም።

ፋኖ ከታች ወደላይ እንደ ፈራኦኖቹ ፒራሚን እየተገነባ ያለ ድርጅት ነው። ገና ተገንብቶ አላለቅም። ክታች በየ ቡድኑ ጎበዝ፣ ደፋር፣ አርቆ አሳቢ የሆነውን ወንድሙን “ወንድም አለም” አንተ ትሻላለህና ምራን እየተባለ ነው የሚመርጠው። ይህ መሪ ደግሞ አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ ሆኖ ካልተገኘ ሌላ ወንድም ጋሻ ይተካል።

ከዛ ደግሞ የወረዳና የአውራጃ ቡድን ሲያድግ እንዲሁ በመተሳሰብና በተግባር ብቃት ያላቸው ይመረጣሉ። ፋኖ ጀግና መሪ በድምጽ ብልጫ ይፈጠራል ብሎ አያምንም። ፋኖ በኢትዮጵያዊ ስሜት የተዋቀረ ኃይል እንጂ በኮሚኒስቶቹ አወቃቀር የተገነባ አይደለም።

የኮሚኒስቱ አደረጃጀት በኢትዮጵያ ዛሬ የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ግንቦት ሰባት ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ 260 ተዋጊዎች ብቻ ይዞ ባልመጣ ነበር። ዛሬ የምታያቸው እነ መሬ ወዳጆ፣ እነ ሻለቃ አርጋው፣ እነ ሻለቃ ሰፈር፣ እነ ሻለቃ ሲሳይ፣ እነ ኢንጂነር በየነ፣ እነ ሻለቃ ጎበዜ፣ እነ ፋኖ ቴዎድሮስ፣ እነ ፋኖ ማንደፍሮ እነ ዘመነ ካሴ እነ ፋኖ ጥላሁን፣ እነ ፋኖ እሸቱ፣ እነ መንበር አለሙ፣ እነ ኮለኔል ማነበር፣ እነ ሻልቃ አበበ ሙላቱ እና በዚህ ስማቸውን ዘርዝረን
የማንጨርሳቸው “አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ” መሪዎች በዚህ መንገድ ነው የተወለዱት።

ከዚህ በላይ ስማቸው እንዳይጠቀስ በብአዴንና በፌዴራል እስር ቤት ያሉ፣ በዚህ መንገድ ነው የተመረጡት።

ይህ ደግሞ እውነተኛው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሙከራ ነው። ግድ በኮሚኒስቶቹ ኩረጃ መራጭ፣ አስመራጭ፣ ድምጽ ቆጣሪ፣ ሊቀመንበር፣ የቁጥጥር ኮሚቴ ተብሎ እጅ ወጥቶ ተቆጥሮ አይደለም። ጠላትን ለመደምስሰን የተሻለው ስው ማን ነው ብሎ የሚመረጠው። መሪ ተብሎ ስለተመረጠ አንድ ሰው ጀግና አይሆንም ይሁንና በተግባር የተፈተነ ጀግና ግን መሪ ሊሆን ይችላል።

ፋኖ በተግባር የተፈተኑ መሪ እየፈጠረ ያለ ድርጅት ነው። ፕራሚዱ ተገንብቶ አላለቀም። ከላይ የሚመጣም መሪ መቀለጃ እንጂ ተቀባይነት አያገኝም።

አሁን የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ስጋት ያልገባቸው እነ ሻለቃ ዳዊት ለ50 አመት ያልሰራላቸውን መንገድ ከላይ ወደታች ለመቆጣጠር ሲሞክሩ እያየን ነው። ፋኖ ከታች ወደላይ መሪ እየፈጠረ ባለበት ሁኑታ አንደ ኮሚኒስቶቹ 7 ስዎች ተመራርጠው የፖሊት ቢሮ አባላት ቢፈጥር ትግሉን ይገለዋል።

ፋኖ እንደጀመረው በራሱ መንገድ አንድ የሆነና እያደገ ያለ መዋቅር ነው። በየ ሳምንቱ አንዳዲስ ህብረት መፍጠር አያስፈልገውም። የፋኖ ህዝባዊ ግንባር በወረቀት ላይ በሁለት ሰዎች ተመሰረት አንድ ሚሊዮን ዶላር ሰብስቦ ሳያበቃ አሁን ደግሞ ህዝባዊ ኃይል የሚባልን እየመሰረትኩ ነው የሚል ዜና ተሰራጨ።

ምንድነው ይሄ ሁሉ ጭንቀትና ጥድፊያ? ፋኖ የቸገረው 100 የሳተላይት ስልክ እና 100 የትከሻ ሞርተር ነው። ይህንን ዲያስፖራው ማቅረብ ሳይችል መሪ ልላክላችሁ የሚለው ለፋኖ ምን ይጠቅመዋል? ፋኖ ዛሬ ሞርታር ቢታጠቅ የአብይን ሜካናይዝድ ጦር በርቀት አስደንብሮ ከክልሉ ያባርረዋል። እነዚህ መሳሪያዎች ደግሞ ከጎረቤት ሀገሮች በርካሽ የሚገኝ ነው። የተሰበሰበው ዶላርን ለዚህ ከማዋል ይልቅ ፋኖን ለመከፋፈያና አሽከር ለማድረጊያ
ሲውል ያሳዝናል።

አሁን የተያዘው የፋኖን ብር ይዞ የተጀመረው የብልጣብልጦች ጨዋታ ትዝብት ላይ የሚጥል እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት አያጎናጥጽፍም። በትግል ውስጥ እንጂ መሪ የሚወለደው በኮንቴነር ከውጪ አይመጣም። ሀገሩን የሚወድ የአማራ ሰቆቃ ያንገበገበው መጥቶ አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ ሆኖ መሪ መሆን ይችላል።

ብዙ ሰው ስለፋኖ ያልተረዳው

የፋኖ ዐዓላማ የአማራን ሕዝብ ከእልቂት እራሱን የሚያድንበትን የትግል ሜዳ ማደላደል እንጂ ህዝቡን ነጻ አውጥቼ በዚህ ማኒፌስቶ እገዛሀለሁ ለማለት አይደለም። ሻለቃ ዳዊት በፈጠሩት ረብሻ ምክንያት አሁን በየ ብርጌዱ ማኒፌስቶ እየተጻፈ አዳዲስ መሪዎች ነን የሚሉ ብቅ ብቅ እንዲሉ በር እየከፈተ ነው። ምንድነው ሲባሉ ትግላችንን ሊቀሙን ነው የሚል ስጋት ነው። አሁን ትግሉን አቁመን ሽማግሌ በመላክና መምከሩ የሙሉ ግዜ ስራ እየሆነ ነው።

ልንረዳው የሚገንባ ፋኖ ህዝባዊ እንቢተኝነት ነው። ፋኖ የአማራውን ሕዝብ የሰፈረበትን አትችልም ስሜት አፍርሶ እችላለሁ፣ ጫፌን ከነካሀኝ አደባይሀለሁ የሚል መንፈስ መፍጠር ነው። ፋኖ በርካታ የስትራቴጂ ጥናቶች ሰርቷል። በርካታ ችግሩ ምንድነው ብሎ ዘመናዊ የችግር መፍቻ መንገዶቹን ሞክራል (root cause analysis tools such as SWOT, Fish Bone, mindmap, 5 Whys, Pereto) እየተጠቀመ መርምራል?

በተለያየ ሽፋኖች አዋቂዎችንና ምሁራንን እየጋበዘ የአማራ ሕዝብ ችግር ምንድነው የሚለውን ተወያይቷል። የሁሉም መደምደሚያ የአማራ ሕዝብ ስነልቦና ቀውስ ነው የሚለ ነበር።

አማራው በቁጥር በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ብሄረሰ ነው፣ ከበርካታ ብሄረሰቦች ጋር ጋብቻ፣ትስስርና ቁርኝትና ድጋፍ ያለው ነው። በርካታ ብሄረሰቦች የሚወደድ የሚከበርና የሚጠበቅ ነው። በመላው ኢትዮጵያ እሚኖር ነው። የተማረ ሰው አለው፤ ሀብት አለው፣ በአለማቀፍ ትላልቅ ድርጅቶች የሚሰሩ ልጆች አሉት፣ የውትድርና ታሪክ እና ለነጻነት እንቢ ባይነት ታሪክ አለው፣ የአስተዳደር ባህልና ትውፊት አለው ። ታድያ ይህ ማኅበረሰብ ሲታረድ፣ ሲፈናቀል፣ ሲሰደብ፣ ሲዋረድ፣ እንደ አናሳ ብሄረሰብ ማልቀስና በፌስ ቡክ ሻማ መስቀል ለምን ሆነ ምላሹ የሚል ነበር።

እነ አበበ አረጋይ፣ አነአክሊሉ ሀብተወልድን እነ ፕሮፌሰት አስራትን የወለደው ማኅበረሰብ የት ደረሰ? አማራን ምን በላው የሚሉ ጥያቄዎች ለረጅም ግዜ ያከራከሩ ነበሩ።

የመጨረሻው ድምዳሜ አማራው የስነልቦና ቀውስ እንጂ የአቅም ችግር የለውም። አቅም እያለ እንደሌለው፣ መብት እያለው እራሱን እንደወንጀለኛ፤ ህይወቱን ገብሮ 80 ብሄረሰቦችን ከቅኝ ገዚዎች በማዳኑ ቅኝ ገዢ ተባለ፣ ወር ተራ የራሱን ጭብጦ ይዞ ወጥቶ በበረሀ ዳር ድንበር እየጠበቀ በወባና በንዳድ እንላለቀ እንደ ወራሪ ተባለ። አኩሪ ታሪክ እያለው እንዲሸማቀቅና ይቅርታ እንዲጠይቅ የሚያስገድድ ስርአት ባለፉት ሀምሳ አመት ተጭኖበታል በራስ
መተማመኑን አጣ። የራሱን ስሪት እምነት ፊደል እውቀት ባካፈለ እንደ ጨቋኝ ታየ። በእርግጥ አማራ ያጠፋው ፊደል? ያጠፋው ቤተ መቅደስ? ያጠፋው መንግስት እና ስነጽሁፍ አለን? ታድያ የራሱን የኛ የኢትዮጵያ ብሎ በማካፈሉ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ሊሸማቀቅ ሊያፍርና እንዲቀጣ ሲደረግ ዝም አለ የሚሉ መከራከሪያ ውይይቶች ተካሂደዋል።

እነ አክሊሉ ሀብተወልድን የፈጠራ ማኅበረሰብእ እንደ አገኘት ተሻገር፣ ይልቃል ከፍያለ፣ ደመቀ መኮንን ያሉ ለመኪናና ለቪላ ቤት ብለው እናታቸውን የሚገርፉ ከየት መጡ ተብሎ በነጭ ቦርድ ላይ በርካታ መላ ምቶች ተሰርተዋል።

ስለዚህ አማራ መጀመሪያ ነጻ መውጣት ካለበት ከጭቆና ሳይሆን ከራሱ የስነልቦና ቀውስ ነው ተብሎ ተደምድሞ በርካታ ሴሚናሮች በወጣቶች ላይ ተካሂዳል። ወጣቱ ገበሬው ሴቱ ወንዱ ተቀይሮ እውነተኛ አምሐራ ተፈጥሯል።

ይሁንና አሁንም በባርነት ስለንቦና የታሰረ የአማራ ባለሀብት፣ ምሁር ወታደር፣ የሀይማኖት አባት፣ ቢሮክራሲ እና ፓለቲካኛ አለ። እራሱን ባህሉን ታሪኩን በመዝለፍ ወገኑብ በጉቦ በመዝረው ወሬ በማቀበል በማሰር በመግደል ሆዱን ሞልቶ ላማደር የሚጣጣት ብዙ ነው። በዚህ ባባርነት የበታችነት መንፈስ ውስጥ ታስሮ እራሱን ነጻ ያላወጣና ነጻ አውጪ ጠባቂ የሆነው ብዙ ሚሊዮን ነው። ይህ ሰው ከተጫነበት የበታችነት ስሜት የወጣ ቀን መብቱን
ያስከብራል። ይሄንን ሀሳብ ይዘው በርካታ ምሁራን፤ የሀይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች እንዲያስተምሩ እየተደረገ ነው። ፋኖዎች በደረሱበት ባደሩበት ሁሉ የሚያስተምሩት ሁሉም እራሱን ከባርነት አውጥቶ አምሐራ (ነጻ ሰው) እንዲሆን ነው።ፋኖ የዚህ ውጤት ነው። ይሄንን ለማሳካት ስራቸውን አቁመው ከገጠር ገጠር እየዞሩ፣ አፈር ላይ እየተኙ ይሄንን ጽንሰ ሀሳብ ወጣቱ እንዲቀበልና በራሱ እንዲተማመን የጣሩ ጊዜው ሲደርስ ይመሰገናሉ። ይህ ጽንሰ
ሀሳብና በራስ መተማመን ነ ስጋ ለብሶ ነው ፋኖ የሆነው። ለዚህ ነው አማራው ለ50 አመት የተጫነበትን የወንጀለኛነት ስሜት ከራሱ ላይ ሲያወርድ እንደ አንበሳ የሚያስፈራ ኃይል እየሆነ የመጣው።

በተሾመ ምትኩ ቼ በለው በሚለው ዘፈኑ አሉ ጋደም ጋደም አሉ ጎንበስ ጎንበስ አውሬ መስያቸው
ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው

 

 

ቼ በለው ቼበለው ቼበለው እረ ቼበልው
ቦንብም ወረወሩ መትረየስ ደቀኑ

አሉ ጋደም ጋደም አሉ ጎንበስ ጎንበስ

አውሬ መስያቸው

ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው
ቆርጬ ስነሳ፣ ቆርቼ ስነስ፣ ለበነን ሳነሳ
ይፈሩኝ የለም ወይ እንደ ዳልጋ አንበሳ

ይህ ነው የአማራ ነጻነት እወጃ። የአማራው ችግር አቅሙን እንዳያውቅ ስለተደረገ ነበር። አሁን እንደምናየው ከነጻ አውጪ አዚም ሲላቀቅ የአማራው አቅሙ ተረዳ ስለዚህ “ይፈሩት ጀመሩ እንደ ዳልጋ አንበሳ”።

ካሁን ወድያ አማራን ገድዮ እኖራለሁ፣ አማራን አስገድዬ ቪላና V8 ይሰጠኛል ብሎ የሚያስብ ሰው በኢትጵያ ውስጥ አይኖርም። በገባበት ገብቶ ጥይት ያለ ውሀ ያስውጠዋል።

የአማራ ነጻነት ይህ ነው። መንግስት ይመጣል መንግስት ይሄዳል። በራሱን መተማመን የፈጠረ ሕዝብ ማንም ይምጣ ማንም ይሂስ ከትውልድ ትውልድ በነጻነት ይቀጥላል።

ታድያ አሁንም እንደግፍሀለን ብለው መጥተው ትግሉን በነጻ አወጣሀለሁ ትርክት እጁን በድጋሚ እንዲያጣጥፍ የሚወተውቱ አሉ። እባካችሁ አልገባችሁም ሊገባችሁም አይችልምና አደብ ግዙ ተብሎ ተጽፎላቸዋል ይሁንና ምንም አልሰሙም። ትንሽ ሃሳብ ይዘው ትልቅ ስራ መስራት የሚቻል የመሰላቸው ብቅ ብቅ እያሉ ነው። በብር የፋኖን እምነትና ክብር መግዛት የሚቻል የመሰላቸው ደካሞች በርካታ ናቸው።

የአማራ ጠላት መንግስቱ ኃይለማርያም፣ መለስ ዜናዊ ወይንም አብይ አይደለም። የአማራ ጠላት በደንብ ተቀምሞ ለ50 አመት በፈረንጅ ማደጎ ያደጉ የበታችነት ስሜት በጥብጠው ያጠጡት በራሱ ልጆች ናቸው። በራሱ እንዳይተማመን፣ ለራሱ መብት እንዳይቆም፤ ጨቋኝ እንደሆነ፣ መጥፎ እንደሆነ፣ አቅም እንደሌለውና ነጻ አውጪ እንዲጠበቅ መደረጉ ነው። በዚህም ስነልኖና በየቀኑ ተሰልፎ እንዲታረድ ያደረገው ትርክት የፈጠሩ አማራ ነን
ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ የፈረንጅ አጀንዳ አስፈጻሚ ማደጎዎች ናቸው። የአማራን አርበኞች፣ ሀገር ወዳዶች፣ ምሁራን አስረው ገለው አዋርደው የቀበሩ ማደጎዎች ናቸው።

አሁንም አማራ ታላቁ መሪን ፈላጊ እንዲሆን፣ ወደ ገነት የሚያስገባው የ7 ኮሚኒስቶች አደረጃጀት ትርክት ይዘው በድጋሜ ብቅ ያሉ ያሉ አሉ። ሻሬም ማርክስን፣ ማኦን፣ ካስትሮን ስንጠቅስ ቁጭ ብላችሁ አዳምጡብ የሚሉ ጥራዝ ነጠቆች አሉ።

አማራ ነጻ አውጪ ጠባቂነትን መሆን የለበትም። እራሱን ነጻ ያላወጣ አማራ ብቻ ነው “አም’ሐራ” የሚሆነው። “አም’” ማለት ህዝብ ሲሆን “ሐራ” ደግሞ ነጻ ማለት ነው። ነጻ ያልሆነና ባርነትን የመረጠ “አም’ሐራ” ነኝ ማለት አያስችለም። ስለዚህ ለራሱ ነጻነት ዋጋ መክፈል ያልፈለገና ነጻ አውጪ ጠባቂ ለትግሉ ሸክም እንዲ ደጋፊ አይደለም ብሎ ፋኖ ያምናል።

ፋኖ በደሴ በጎንደር ህወሀት ከመውረሩ በፊት ወጣቶችን በታይኳንዶና በአካል ብቃት (self-defense) ያሰለጠናቸው ወደ 400 የሚገመቱ ወጣቶች ነበሩ። የፋኖ ስህተት እነዚህን ወጣቶች ሰለ “አም’ሐራ” ነት አላስተማራቸውም ነበር። የአካል ብቃት ቢገነቡም ጭንቅላታቸው የበታችነት እንጂ “አም’ሐራ”ነት አልነበረም።

እነዚህ ወጣቶችን ቴዎድሮስ የሚባለው ንጉስ እየመጣ ነው ብለው አሳምነው ቀለበት እንዲያሰሩ በጣታቸው ላይ አድርገው ከትግሉ ወጥተው ተአምር ጠባቂ እንዲሆኑ ጥቂት ሰዎች አሳመኗቸው። ጥቂቶቹን ልጆች ባልተጠና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የቴዎድሮስን መምጣት በአደባባይ እናውጃለን ብለው ወጥተው በብአዴን ቅጥረኞች ተገደሉ። እንዲህ አይነቱን ተስፈኝነት ነው ፋኖ የሚዋጋው እያጠፋ ያለውም።

የፋኖ ትግል ለነጻነቱ ማንም እንደማይመጣለትና ለራሱ ነጻነት እራሱ ብቻ መቆም እንዳለበት ማሳመን ነበር። አሁን እውን ሆንዋል። ፋኖ የአም’ሐራ የሆኑ የነጻ ሰዎች ስብስብ ነው።

አማራው የሀምሳ አመቱን አፍዝ አደንግዝ የኮሚኒስቶችና የብሄረተኞች ድግምት ተላቆ አም’ሐራ ነኝ ስላለ ነው ውጤት ያመጣው።

አማራን ነጻ እናወጣሀለን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻ እናወጣህና ህገመንግስት ማኒፌስቶ ሰጥተን እንገዛሀለው በሚለው የሕዝብ ንቀት ስሜት ላይ አይደለም ፋኖ የተመሰረተው። ይሄንን ለማፍረስና ከላይ ወደታጅ እንዘዘው የሚለውን የነሻለቃ ዳዊት እና የነሀብታሙን ቁጣ አልሰማም የሚለው።

በስሙ የተለመነውን ብር ሳይቀር እንደ መግዣ እየተጠቀሙበት ስናይ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጎዳም’ ለማለት ተገደናል።

ፋኖ እየተገነባ እንደ ፒራሚድ እንጂ ያለቀ ጠባብ የኮሚኒስቶችና የጥራሽ ነጥውቆች ጎጆ አይደለም። ተጣድፎ በኮሚኒስቱ አካሄድ ማኒፌስቶ ጽፎ ድርጅት መሰረትኩ ብሎ፣ ተሽቀዳድሞ የፖሊት ቢሮ ሰይሞ፣ በጠባብ ጥብቆ አልገባ ያለውን ህዝብ ደግሞ ይከረከማል ማለት አንፈልግም።

ሻለቃ ዳዊት የእስክንድር ነጋን በጎ ስም እንደ ጓንት ተጠቅመው፤ ጓደኞቻቸውንና ጭፍሮቻቸውን በፖሊት ቢሮ ሞልተው፣ በኤርትራ ህዝባዊ ሀርነት ግንባር አምሳያና ህዝባዊ ግንባር የሚል በማቋቋም ድርጅቱን ለመቆጣጠርና ለ50 አመት የተሽነፉበትን መንገድ መቀበል ያልፈለግነው።

ክፍል አምስት ይቀጥላል

Related: የፋኖ አhttps://fanolisan.org/31/ንድነት ምክር ቤት አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ ክፍል 1

Related: የፋኖ አንድነት ምክር ቤት አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ ክፍል 2