ከአማራ ፋኖ በሸዋ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ!
የአማራ ፋኖ በሸዋ 2ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ለአስራ አራት ቀናት ያህል አካሂዷል፡፡ ጉባኤዉ በርካታ ነገሮች የተዳሰሱበት፣ በትግል ሂደት ወቅት የነበሩ ጥንካሬና ድክመቶች የተፈተሹበት፤ የተለያዩ ማሻሻያዎችና እርምቶች የተወሰዱበት በመሆኑ ለሞት ሽረቱ ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት የወሰደ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ይህንን ጉባኤ ለየት የሚያደርገው የአብይ አገዛዝ ከመደናበር ወደ ለየለት ሙሉ ሽንፈት በተንደረደረበት ብሎም አስተዳደሩ ተፈረካክሶ በምትኩ የፋኖ መዋቅር እስከታችኛው እርከን የተዘረጋበት። ከስጋ-ደም ህልውና ወደ አጽመ-ሬሳ አፈርነት የአገዛዙ የህልውና የተሸጋገረበት ወቅት መደረጉ ነው፡፡ በሌላ […]